የመጀመሪያው የስፖርት ኤግዚቢሽን እና ባዛር በኢትዮጵያ በደማቅ ስነስርአት ተጠናቀቀ።
መጋቢት 09, 2007

በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ከመጋቢት 5 እስከ 9 ለአምስት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የመጀመሪያው የስፖርት ኤግዚቢሽን እና ባዛር በ ኢትዮጵያ ዛሬ በተደረገ ደማቅ ስነስርአት ተጠናቋል።

በኤግዚቢሽኑ በርካታ የስፖርት ክለቦች፣ ማህበራት አንዲሁም የስፖርት ትጥቅ አስመጪዎች ተሳታፊ ሆነዋል።

በዝግጅቱ በይበልጥ ደምቀው ከታዩት  የቅዱስ ጊዮርጊስ፣  የኢትዮያ ንግድ ባንክ፣ የኢትዮጵያ ቡና፣ የደደቢት እንዲሁም የወላይታ ዲቻ ስፖርት ክለቦች ይገኙበታል።በዝግጅቱ ክለቦቹ እስካሁን ያገኟቸውን ሽልማቶች ጨምሮ የየቡድኖቻቸውን ታሪካዊ አመጣጥ የሚወክሉ በፎቶግራፍ የተደገፉ መረጃዎችን ለጎብኚዎች አቅርበው ማብራሪያ ሲሰጡ ቆይተዋል። በዚሁም መሰረት ቡድኖቹ ካቀረቧቸው አንዳንድ መረጃዎች ውስጥ የሚከተሉት ለየት ያሉና የጎብኚዎችን ትኩረት በይበልጥ የሳበ ነበሩ።

ጊዮርጊሶች በ1962 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሻምፒዮን ሆነው ያገኙትን የነሃስ ዋንጫ እንዲሁም አንድ ለየት ያለ የቀንድ ዋንጫ ለትእይንት አቅርበዋል።
St.george Old Tropghy

እነዚህ ዋንጫዎች ቡድኑ በ1969 ዓ.ም. ገደማ በፈረሰበት ወቅት በግለሰብ የቡድኑ ደጋፊዎች ቤት ተጠብቀው የኖሩና ቡድኑ በድጋሚ በተቋቋመት ወቅት ለቡድኑ ከደጋፊዎቹ የተበረከቱ ናቸው። ሌላው አስገራሚ ነገር የቅዱስ ጊዮርጊስ  ቡድን በፈረሰበት ወቅት ተበታትነው ከነበሩ ዋንጫዎች ውስጥ የእስፖርት ኮሚሽን የተረከባቸውን ዋንጫዎች በስሩ ያስተዳድራቸው ለነበሩ ውድድሮች ሽልማት አድርጎ ይሰጥ እንደነበር  የቅዱስ ጊዮርጊስ  ዴስክ አስጎብኚዎች ለጎብኚዎች አስረድተዋል።
St.George
 

ኢትዮጵያ ቡናዎች ዴስካቸውን በቀድሞ ተጫዋቾቻቸው ፎቶዎች ያስዋቡ ሲሆን በተለይ ከደቡብ አፍሪካ ለቡድኑ ደጋፊዎች ስታዲየም ውስጥ ድጋፍ መስጫ እንዲሆን ያስመጡት ትልቅ ነጋሪት ድራም ዴስካቸውን ሰድምቆታል።
Coffe Supporters new Dram

 ድራሙ በአይነቱ የተለየና በሀገራችን ለድጋፍ መስጫነት ለመጀመሪያ ጊዜ የሚውል ይሆናል። ድራሙን በደቡብ አፍሪካ ነዋሪ የሆኑ የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ደጋፊ በስጦታ የላኩት ሲሆን ከጉምሩክ ቀረጡን ከፍሎ ያወጣው የስፖርት ክለቡ መሆኑ ታውቋል።
Coffee Old Team


ደደቢቶች ከተቋቋሙበት ጊዜ ጀምሮ ያገኟቸውን የዋንጫ ሽልማቶች ለእይታ ያቀረቡ ሲሆን በይበልጥ ተመልካችን ከሳቡላቸው ውስጥ አሁን  በአራት ክልሎች በሃረር፣ባህርዳር፣አርባምንጭ አንዲሁም በመቀሌ እያካሄዱ ያሉትን ከ14-16 አመት የታዳጊዎች ፕሮጀክት  እንዲሁም በአዲስ አበባ በክለቡ ሙሉ በሙሉ እየተደፉ ያሉትን 2  ከ21 አመት በታች የተስፋ ቡድን ያሉበትን ሁኔታና እድገት በፎቶግራፍ አስደግው በቃል ለጎብኚዎች ማብራሪያ በሚሰጡበት  ወቅት ነው።
The first youth team

የፕሮጀክቶቹን ውጤታማነት ሲያስረዱ በዋናው ቡድን ከሚጫወቱ በርካታ ከፕሮጀክት ከተገኙ ተጫዋቾች ውስጥ የመሃል ተጫዋቹ ሄኖክ ኢሳያስ ከድሬዳዋ ፕሮጀክት የተገኘ መሆኑን በምሳሌነት ይገልጻሉ።
Henok Esyas


ንግድ ባንኮች ዴስካቸውን የስፖርት ክለቡ እስካሁን በተለያዩ የ ውድድር አይነቶች  ባገኛቸው ዋንጫዎች አሸብርቀው የስፖርት ማህበሩ ወደፊት ሊሰራው ያሰበውን የተለያዩ እቅድ በቃልና በበራሪ ወረቀት አስድፈው ማብራሪያ ለጎብኙዎች ሲሰጡ ተስተውለዋል።
Commercial Bank

ወላይታ ዲቻዎች በበኩላቸው ዴስካቸውን በቡድኑ ማልያና በተጫዋቾቻቸው ትልቅ ፎቶግራፍ አሳምረው አድምቀውታል። በተለይ ቡድኑ በቅርቡ ያስመረቀውን ስታዲየም ስራና አልግሎት ቦቶግራፍ በማስደገፍ ለተመልካች  እያስጎበኙ ይገኛሉ።
Wolayta Dicha

የሰሜኖቹ ዳሽኖች ዴስካቸውን በፎቶግራፍ አሸብርቀው ጎብኚዎችን ስለክለቡ አመሰራረት እና አሁን ስላለለበት ደረጃ ማብራሪያ ሲሰጡ ታይተዋል።

በኤግዚቢሽኑ የኢትዮጵያ ቡና፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ደደቢትና ወላይታ ዲቻ የክለብ ማሊያዎቻቸውን ለደጋፊዎቻቸው ለሽያጭ አቅርበዋል።  ኢትዮጵያ ቡና እና ቅዱስ ጊዮርጊስ በተጨማሪ አዳዲስ ደጋፊዎች የአባልነት ምዝገባ አካሂደዋል።

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ከአመሰራረቱ እስካሁን ድረስ የደረሰበትን  ሂደት የሚያስቃኝ የፎት ትእይን በስፋት አቅርቧል። በፎቶ ከቀረቡ መረጃዎች ውስጥ በሶስተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ሻምፒዮን የነበረውን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ቡድን ያካተተ ሲሆን የቀድሞው ንጉስ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ በጊዜው የነበሩትን የፊፋ ፕሬዚዳን ሰር ስታንሊ ራውስን ሲቀበሉ የሚያሳይ እንዲሁም  የመጀመሪያው የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት የነበሩትን ሜ.ጀ. ከበደ ገብሬን ፎቶ ለእይታ አቅረቧል።
Ethiopian National Team After Winning the 3rd Arican Continent Cup
First EFF President
King Hailesselassie recieving the FIFA the  president

በሌላ የስፖርት አይነቶች የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የአበበ በቂላን የቀኝ እግር ምሳሌ አድርጎ በብር የተቀረጸ ቅርጽ ለእያታ አቅርቧል ፣ የኢትዮጵያ  ግሬት ራን አዘጋጆች በበኩላቸው እስካሁን በውድድሩ ያስገኙትን  ውጤት  የሚያሳይ በፎቶግራፍና በበራሪ ወረቀት የተደገፈ ማብራሪያ ለጎብኚዎች ሰጥተዋል።
Abebe Bekila Right Foot in Silver

በአጠቃላይ ዝግጅቱ ደማቅና ጥሩ የነበረ ሲሆን በበርካታ ጎብኚዎች ላለፉት አምስት  ቀናት ተጎብኝቷል። 

ይህ ኤግዚቢሸን ለኢትዮጵያ ስፖርት እድገት ካለው ቀላል ከማይባል አስተዋጽዎ አንጻር ኢትዮ ፉትቦል ይህን ሀገር አቀፍ የስፖርት ኤግዚቢሽን አዘጋጅተው ላቀረቡት አዘጋጆች አድናቆቱን ለመግለጽ ይወዳል። ወደፊት በሚያዘጋጁት ኤግዚቢሽን የበለጠ ስኬትን እንዲያገኙም ይመኛል።


ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
ተስፋዬ የምሩ [827 days ago.]
 አሪፍ ነዉ በዚሁ ቀጥሉበት

Aliyas Alene [774 days ago.]
 ጨዋተው በጣም ደስ ብሎናል:እናመሰግናለን"

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!