ዋልያዎቹና ዋልያ ቢራ ለሶስት ዓመታት ሊጣመሩ ነው
መጋቢት 09, 2007

የኢትዮጵያ ወንዶች ብሔራዊ ቡድን ወይም ዋልያዎቹ ለቀጣዮቹ ሶስት ኣመታት በቋሚነት ስፖንሰር የሚያደርጋቸው ባለጸጋ አግኝተዋል። ዋልያዎቹን እስከ 2018 የሩሲያው የዓለም ዋንጫ ድረስ ስፖንሰር በማድረግ አብሮ ለመስራት ከፌዴሬሽኑ ጋር ስምምነት ላይ የደረሰው በሄኒከን ኢንተርናሽናል ስር ምርቱን ለገበያ እያቀረበ ያለው ዋልያ ቢራ ነው። የፌዴሬሽኑ ከፍተኛ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ወንድምኩን አላዩ ለዝግጅት ክፍላችን በስልክ እንደገለጹት የሁለቱ አካላት ስምምነት ሁለቱንም ወገን ተጠቃሚ ያደረገ ነው። አቶ ወንድምኩን ዋልያ ቢራ በምን ያህል ገንዘብ ስፖንሰር ለማድረግ እንደፈለገ የገንዘቡን መጠን ከመግለጽ የተቆጠቡ ሲሆን ዛሬ በሂልተን ሆቴል በሚደረግ ጋዜጣዊ መግለጫ ይፋ ይሆናል ብለዋል።

ዋልያዎቹ ከ31 ዓመታት ቆይታ በኋላ በአፍሪካ ዋንጫ መሳተፍ በጀመሩበት በ2013 እ.ኤ.አ ጀምሮ ላለፉት ሁለት ዓመታት በዋናነት ስፖንሰር ሲያደርጋቸው የቆየው በደሌ ቢራ መሆኑ ይታወሳል። በደሌ ቢራ በሄኒከን ኢንተርናሽናል ስር የሚተዳደር መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን ከዋልያዎቹ ጋር በሚደረገው አዲሱ ስምምነት ለምን በዋልያ ቢራ ስም ስፖንሰር ማድረግ ፈለገ ስንል አቶ ወንድምኩንን ጠይቀናቸው ነበር። አቶ ወንድምኩን ሄኒከን ኢንተርናሽናል በአሁኑ ሰዓት ስፖንሰር ለማድረግ የፈለገው ዋልያዎቹን ብቻ ነው። ዋልያዎቹን በዋልያ ቢራ ስም ስፖንሰር ለማድረግ የፈለገው በአሁኑ ወቅት በመላው የአገሪቱ ክፍል ከፍተኛ ተወዳጅነትን ባተረፈው የቢራ ምርቱ ስም ነው ሲሉ መልሰዋል። ዋልያ ቢራና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለቀጣዮቹ ሶስት ዓመታት የሚያቆያቸውን ስምምነት ዛሬ ከአመሻሹ 11፡30 በሂልተን ሆቴል ይፈራረማሉ ተብሎ ይጠበቃል። 
EFF Signed Sponsorship Agreement With WALIA Beer

በተያያዘ ዜና የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ሉሲዎቹ የፊታችን መሥከረም አጋማሽ ጀምሮ በኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ለሚዘጋጀው 12ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች ለማለፍ የፊታችን ቅዳሜ ከቀኑ አስር ሰዓት ከካሜሩን አቻው ጋር ይጫወታል። ቡድኑ በአሰልጣኝ በሀይሏ ከበደ እየተመራ 26 ተጫዋቾችን ይዞ ልምምዱን በኢትዮጵያ ሆቴል እያደረገ መሆኑ ተገልጿል።

ካሳ ሀይሉ
ኢትዮ ፉትቦል

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
tes sis gem [762 days ago.]
 ከዋሊያ ብራ ሚፈልገው ነገር ካለ መስቀል ተገሊብጣለቸ ሚባለው እዉነት ነው በትግራይ መጀመርያ ደስ ብሎተ ስዝናናለት ነበር አሁን ይሀ ወሬ ከተናፈሰ ወዲህ ግን ብዙ ሰው ትቶታል

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!