ዋልያ ቢራ ከዋልያዎቹ ጋር ለአራት ዓመታት አብሮ ይዘልቃል
መጋቢት 11, 2007

  የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድንን  ላለፉት ሁለት ዓመታት በዋናነት ስፖንሰር ሲያደርጋቸው የቆየው በደሌ ቢራ ኮንትራቱን ማጠናቀቁን ተከትሎ  ዋልያ ቢራ ለቀጣይ አራት ዓመታት የሚዘልቅ የሃምሳ ስድስት ሚሊየን ብር ስፖንሰር ሺፕ ተፈራርሟል። 
WALIA BEER OFFICIAL ETHIOPIAN MEN NATIONAL TEAM SPONSOR

ከትላንት በስቲያ በሂልተን ሆቴል በተካሄደው የስፖንሰርሺፕ ስምምነት በሄኒከን ኢንተርናሽናል ስር የሚተዳደረው ዋሊያ ቢራ ለዋልያዎቹ በዓመት አስራ አራት ሚሊየን ብር ስፖንሰር እንደሚያደርግ ነው የተገለፀው።
  
ቀደም ሲል በ24 ሚሊየን ብር ስፖንሰር በመሆን ሁለት ዓመታትን ከብሄራዊ ቡድኑ ጋይ የቆየው በደሌ ቢራ በሚገባ ምርቱን ማስተዋወቅ እንደቻለ በእለቱ ተግልጿል።  በኢትዮጵያ የሄኒከን ኢንተርናሽናል ማኔጂንግ ዳይሬክተር ጆሃን ዶዬር ዋልያ ቢራ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድንን ስፖንሰር በማድረጉ ኩራት እንደተሰማቸው በመግለፅ  ረጅም ታሪክ ያለውን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ጋር በሚኖራቸው ቆይታ ቡድኑ በተሻለ ሁኔታ እድገት እንዲያመጣ ድጋፋቸው እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

 ዋልያዎቹን እስከ 2018 የሩሲያው የዓለም ዋንጫ ድረስ ስፖንሰር በማድረግ አብሮ ለመስራት ከፌዴሬሽኑ ጋር ስምምነት ላይ የደረሰው የሄኒከን ኢንተርናሽናል  ልዩ ምርት የሆነው ዋልያ ቢራን ቡድኑ በሃገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጪ በሚያደርገው ጨዋታ ያስተዋውቃል። 

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ምከትል ፕሬዝዳንት አቶ ተክለወይኒ አሰፋ በበኩላቸው ዋልያዎቹን በዋልያ ቢራ ስም ስፖንሰር በማድረጉ መደሰታቸውን ገልጸዋል። ለመጪዎቹ አራት ዓመታት የዋሊያዎቹ ዋና ስፖንሰር እንደሚሆን የተገለጸው ዋልያ ቢራ በስፖንሰርነት ካቀረበው ክፍያ በተጨማሪ  ለፌዴሬሽኑ ተጨማሪ ጥቅማጥቅሞችን እንደሚሰጥም ይጠበቃል። ኩባንያው ዋሊያዎቹን ስፖንሰር ለማድረግ የወሰነው የኢትዮጵያ ህዝብ ስፖርትን በተለይ እግር ኳስን በእጅጉ አፍቃሪ ህዝብ እንደመሆኑ መጠን ምርቶቹን ለማስተዋወቅ ትልቅ እድል ይፈጥርልኛል ብሎ በማሰብ እንደሆነ ከኩባኒያው ሀላፊዎች በኩል ተገልጿል፡፡

የገንዘብ አቅም ውስንነት ለሚፈታተነው እግር ኳስ ፌዲሬሽን ይህ ከዋልያ ቢራ በኩል በስፖንሰርሺፕ መልክ የሚገኝ ገቢ ቡድኑን ለማጠናከሪያና ያሉበትን ክፍተቶች ለመሙያ ወሳኝ ሚና እንደሚኖረው ፌዴሬሽኑ ገልጿል ። አሁን ከዋልያ ቢራ ጋር የተደረገው ስምምነት ከወንዶች ብሔራዊ ቡድን ጋር ብቻ ሲሆን ፌዴሬሽኑ ለሴቶእ ብሔራዊ ቡድን ከሌላ ዓለም አቀፍ ኩባንያ ጋር እየተደራደረ መሆኑንና ስምምነት ላይ ሲደርሱ ይፋ እንደሚደረግ አቶ ተክለወይንበመግለጫው ተናግረዋል። 

በካሳ ሀይሉ 

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!