አሰልጣኝ ኔይደር ዶስ ሳንቶስ ከቅዱስ ጊዮርጊስ አሰልጣኝነት ተሰናበቱ
መጋቢት 12, 2007

ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ብራዚላዊው አሰልጣኝ ኔይደር ዶስ ሳንቶስን  ከአሰልጣኝነት ማንሳቱን አስታወቀ። ክለቡ ለአሰልጣኙን መማንሳት የተገደደው የክለቡ ስራ አመራር ቦርድ ያስቀመጠውን የ2007  በተለይ በአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ ውድድር ስምንት ውስጥ የመግባት ግብ ማሳካት ሳይችሉ በመቅረታቸው ነው ብሏል።  ክለቡ ያደረሰንን የመግለጫውን ሙሉ ጽሁፍ ከዚህ በታች አቅርበናል።

የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ባለው ራዕይ እና በነደፈው እቅድ በአፍሪካ ከሚገኙት ታላላቅ ክለቦች አንዱ ለመሆን እና በውድድር ተሳትፎም በአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ ስምንት ውስጥ ለመግባት በማሰብ ፋና ወጊ ሆኖ የውጪ ሀገር አሰልጣኝ በማምጣት ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

ይህንን መሰረት በማድረግ ብራዚላዊው አሰልጣኝ

ኔይደር ዶስ ሳንቶስን
በመቅጠር በአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ ከዚህ በፊት ከነበረን ተሳትፎ የላቀ ውጤት ለማምጣት እና የተሻለ ደረጃ እንዲያደርሱን በማሰብ ስምምነት ላይ ደርሰን ቀጥረናቸው እንደነበር አይዘነጋም፡፡ሆኖም በዘንድሮው የሻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፏችን በመጀመሪያው ዙር ለመውጣት ተገደናል፡፡አሰልጣኙ ቢጥሩም የክለቡ ስራ አመራር ቦርድ ያስቀመጠውን ግብ ማሳካት ሳይችሉ ቀርተዋል፡፡ በ2007 ዓ.ም  እየተደረገ በሚገኘው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሻምፒዮናም እየታየ ያለው እንቅስቃሴ የዋዠቀ እና ተስፋ ሰጪ ሆኖ ባለመገኘቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ ስራ አመራር ቦርድ ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ አሰልጣኝ ኔይደር ዶስ ሳንቶስ ከመጋቢት 11/ 2007 ዓ.ም ጀምሮ እንዲሰናበቱ ወስኗል፡፡

ኔይደር ዶስ ሳንቶስን በመተካትም ምክትል አሰልጣኞቻቸው የነበሩት ፋሲል ተካልኝ እና ዘሪሁን ሸንገታ በዋና አሰልጣኝነት ቅዱስ ጊዮርጊስን የሚያሰለጥኑ ይሆናል፡፡


Fasil and Zerhun St.George promoted coachsአሰልጣኝ ኔይደር ዶስ ሳንቶስ በቆይታቸው ወቅት ላደረጉት ጥረት ከልብ እያመሰገንን በሚሄዱበት ሁሉ መልካም እድል እንዲገጥማቸው እንመኛለን፡፡

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
abebe [1068 days ago.]
 No stupid team like your Saint Georgis.They have long been salivating for African trophy,but achieved nothing for the last ninety years.I think better teams are now emerging from the South.

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!