ፊፋ ለአሰልጣኞች የአካል ብቃት ስልጠና መስጠት መጀመሩን የኢት.እግ.ኳስ.ፌዴ. አስታወቀ
መጋቢት 16, 2007

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከአለም አቀፍ የእግር ኳስ ማህበራት ፌዴሬሽን/ፊፋ/ ጋር በመተባበር የአዘጋጀው የአሰልጣኞች የአካል ብቃት ኮርስ ትናንት መጀመሩን አቶ ወንደምኩን አላዩ በኢሜይል በላኩልን መረጃ አድርሰውናል። በኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ትናንት በተጀመረውና እስከ መጋቢት 19/2007 ዓ.ም በሚቆየው ስልጠና ኢንስትራክተሮች እንዲሁም ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እና ከክልል መስተዳድሮች የተውጣጡ ከ20 በላይ አሰልጣኞች ተካፋይ ሆነዋል፡፡
FIFA training for Ethiopian football coachs

 ስልጠናው በዓይነቱ የመጀመሪያው ሲሆን ለውጥ ለማምጣትና የተፎካካሪነትን ደረጃ ለማሳደግ እንደሚረዳ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በተግባር እና በንድፈ ሃሳብ እንዲሁም በተለያዩ የጽሁፍና የምስል መርጃዎች የተደገፈውን  ዘመናዊና ከወቅቱ ጋር የሚሄደውን ስልጠና የሚሰጡት በሙያው በቂ ልምድ ያላቸው የፊፋው ኢንስትራክተር ፈረንሳዊው ፒር ባርዩ ናቸው፡፡

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!