ቅዱስ ጊዮርጊስ ከኤል ሜሪክ ጋር የወዳጅነት ጨዋታ ሊያካሂድ ነው
መጋቢት 19, 2007

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አሸናፊው ቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ የፊታችን ሰኞ በአዲስ አበባ ስታዲየም ከሱዳኑ ታላቅ ክለብ ኤል ሜሪክ ጋር የወዳጅነት ጨዋታ እንደሚያካሂድ ከክለቡ የደረሰን መረጃ አስታወቀ። ለአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ ውድድር እንዲረዳው ዝግጅቱን እያጠናከረ ያለው ኤል ሜሪክ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ባቀረበው ጥያቄ መሰረት ጨዋታው እንደሚካሄድ መረጃው ጨምሮ ገልጿል። 

ከአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ በጊዜ የተሰናበቱትና ሙሉ ትኩረታቸውን በአገር ውስጥ ውድድሮች ላይ ያደረጉት ፈረሰኞቹ በበኩላቸው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ለ11 ቀናት መቋረጡን ተከትሎ የኤል ሜሪክን ጥያቄ መቀበሉ ተነግሯል። ጨዋታውን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እውቅና እንደሰጠው የገለጸው የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ መግለጫ በእለቱ ለጨዋታው መግቢያ ክፍያም ይፋ አድርጓል። 
St.George 2007/15 main Squad

በዚህም መሰረት ክቡር ትሪቡን 200 ብር፣ ጥላ ፎቅ 100 ብር፣ ከማን አንሼ በወንበር 50 ብር ያለ ወንበር አስር ብር፣ ሲሆን ካታንጋ ሰባት ብር እንዲሁም ዳፍ ትራክና ሚስማር ተራ እያንዳንዳቸው አምስት አምስት ብር መሆኑን ክለቡ ለዝግጅት ክፍላችን በላከው መረጃ አስታውቋል። ጨዋታው ከቀኑ አስር ሰዓት የሚካሄድ ይሆናል።  
Al Merrikh Sudan

የአገር ውስጥ ውድድር ሲቋረጥ እንደዚህ አይነት ዓለም አቀፍ ልምድ በሚሰጡ የወዳጅነት ጨዋታዎች መጠመድ ለክለቦችና ለብሔራዊ ቡድን ጠቃሚ መሆኑ ይታወቃል። በዚህ ሳምንትም ዓለም አቀፉ እግር ኳስ ማህበር ፊፋ እውቅና በሰጠው የአውሮፓ አገራት በአውሮፓ ዋንጫ ማጣሪያና የወዳጅነት ጨዋታዎች ሲጠመዱ አፍሪካውያን አገሮችም ከተለያዩ የአፍሪካና የአውሮፓ አገራት ጋር በመጫወት ራሳቸውን ሲፈትሹ እያየን ነው። ነገር ግን እንደዚህ አይነት ምቹ አጋጣሚ የተፈጠረለትና ከስፖንሰር አድራጊ ድርጅቶች በዓመት ከ14 ሚሊዮን ብር በላይ ማግኘት የቻለው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ብሄራዊ ቡድኑን ለማጠናከር የሚረዱ ልምድ ሊቀሰምባቸው የሚያስችሉ የወዳጅነት ጨዋታዎችን ለማድረግ ገተለያዩ ሀገራት ፌደሬሽኖች ጋር ድርድሮችን ለማድረግ መንቀሳቀስ ይኖርበታል። በዚህ አጋጣሚ የሚደረጉ የወዳጅነት ጨዋታዎች ለብሄራዊ ቡድኑ ወጣትና አዳዲስ ተጫዋቾች ልምድ የመቅሰም አጋጣሚን እንዲያገኙ ይረዳቸዋል። 

በየምክንያቱ መቆራረጥ የማያጣው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ለቀጣዮቹ 11 ቀናት አይካሄድም። የፌዴሬሽኑን ድክመት መድገም ያልፈለገው ቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብም በቀጣዩ ዓመት ለሚኖርበት አህጉራዊ ውድድርና በአገር ውስጥም ላለበት የፕሪሚየር ሊግና ጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ራሱን በሚገባ ለመፈተሽ የሚረዳውን የወዳጅነት ጨዋታ ማካሄዱ የሚያስመሰግነው ነው። የአገር ውስጥ ሊጎች ሲቋረጡ ስፖርት አፍቃሪው ህዝብ እግር ኳስ የመከታተል እድሉ እየተነፈገ መሆኑ ግልጽ ሲሆን፤ የፈረሰኞቹ ደጋፊዎች ግን በአንድ በኩል ክለባቸውን በገንዘብ የሚደግፉበት እድል እያገኙ በሌላ በኩል ደግሞ እስከ መጨረሻው ለሚወዱት ለታመኑለት ክለባቸው ጨዋታ ሲያደርግ በጨዋታው ለመዝናናት እድሉን ስላመቻቸላቸው ክለቡ የሚያስወድስ ስራ ሰርቷል። ጨዋታውን ከዚህ በፊት እንደኖረው ኢትዮጵያዊ ባህላችን የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ደጋፊዎች ብቻ ሳይሆኑ መላው የእግር ኳስ አፍቃሪ በአዲስ አበባ ስታዲየም ተገኝቶ  ጨዋታውን ይከታተለዋል ተብሎ ይጠበቃል።ተመልካቹ ለሀገሩ እግር ኳስ እድገት ያለውን ህብረት እንደዚህ አይነት ባሉ ኢነተርናሽናል ጨዋታዎች አጉልቶ ማሳየት ይጠበቅበታል።

ኢትዮፉትቦል ዶትኮም መልካም ጨዋታ ለሁለቱም ቡድኖች እየተመኘ አያይዞም ለቅዱስ ጊዮርጊስ መልካም እድል እንዲገጥመው ይመኛል!!

ካሳ ሀይሉ 
ኢትዮ ፉትቦል

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
Enyew [992 days ago.]
 Dil le st georgis

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!