ወልድያ ከነማ እግር ኳስ ክለብ ከውጤት ቀውስ በተጨማሪ የዲሲፒሊን ቅጣትም እያጋጠመው ነው
መጋቢት 19, 2007

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ባደረሰን መረጃ መሰረት ወልድያ ከነማ እግር ኳስ ክለብ መጋቢት 13 ቀን 2007 ዓ.ም ከደደቢት እግር ኳስ ክለብ ጋር በወልደያ ከተማ  ጨዋታቸውን በአካሄዱበት ወቅት የተፈጸመውን ከስፖርታዊ ጨዋነት የወጣ ህገወጥ ድርጊት በተመለከተ ከዳኞችና ከታዛቢ የቀረቡለትን ሪፖርቶች ከመረመረ በኋላ የፌዴሬሽኑ ዲስፕሊን ኮሚቴ የወልደያ ከተማ እግር ኳስ ክለብን በ5000 ብር እንዲቀጣ ወስኗል፡፡
Woldya City

ከፌዴሬሽኑ ኅዝብ ግንኙነት ክፍል የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው የሁለቱን ክለቦች ጨዋታ የመሩት  ዳኞች እና ታዛቢው ባቀረቡት ሪፖርት መሰረት አንድ የወልደያ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ተጨዋች በ50ኛው ደቂቃ በሁለተኛ ቢጫ ካርድ ከሜዳ መወገዱን ተከትሎ የወልደያ ከተማ  እግር ኳስ ክለብ ደጋፊዎችና ተመልካቾች ወደ ሜዳ በመግባት የፕላስቲክ ጠርሙሶች እና ድንጋይ በመወርወር ከስፖርታዊ ጨዋነት ተጻራሪ የሆነ ጥፋት ፈጽመዋል፡፡ በእዚህም ምክንያት ጨዋታው ለ19 ደቂቃዎች እንዲቋረጥ አስገድዷል፡፡ በተጨማሪም በ86ኛው ደቂቃ ረዳት ዳኛው ባሳዩት ምልክት ከጨዋታ ውጭ በሆነ የወልደያ ከተማ ተጨዋች ምክንያት ዳኛው የፊሽካ ድምጽ በማሰማት ጨዋታው በቅጣት ምት እንዲቀጥል ውሳኔ በመስጠት ላይ እያሉ የተመታ ኳስ  መረብ ውስጥ ማረፉን ተከትሎ በድጋሚ ተመሳሳይ ረብሻና ሁከት በመቀስቀሱ ጨዋታው እነደገና ለ12 ደቂቃዎች ተቋርጧል፡፡ 

የዲስፕሊን ኮሚቴው በቅጣት ውሳኔው ላይ እንዳሰፈረው ጨዋታው ደጋፊዎች እና ተመልካቾች በቀሰቀሱት ረብሻ ምክንያት ሁለት ጊዜ ቢቋረጥም የወልደያ ከተማ እግር ኳስ ክለብ የአመራር አባላት የፀጥታ ሃይሎች እና ተጨዋቾች ተመልካቹን ለማረጋጋት ያደረጉት ጥረት እና ተበባሪነታቸው የምስጋና ደብዳቤ የሚያሰጣቸው ሆኖ ተገኝቷል፡፡ የዲስፕሊን ኮሚቴው በወልደያ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ላይ የ5000 ብር የቅጣት ውሳኔ ያሰተላለፈው የክለቡ ተጨዋቾች የአመራር አባላት እና የጸጥታ ሃይሎች ደጋፊዎችን ለማረገጋት ያድረጉትን አስተዋጽኦ ከግምት ውስጥ በማስገባት እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ክለቡ የተላላፈበትን የገንዘብ ቀጣት ወሳኔ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ መክፈል ይኖርበታል፡፡ ሲል የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የላከልን መረጃ ገልጿል፡፡ 

በተያያዘ ዜና ወልድያ ከነማ ትናንት በአዲስ አበባ ስታዲየም ከኢትዮጵያ ንግድ ባነክ ጋር ተጫውቶ ሶስት ለአንድ በመሸነፉ ከወራጅ ቀጠና ለመውጣት እያደረገ ያለውን ጥረት አስቸጋሪ አድርጐታል።

ኢትዮ ፉትቦል

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
Ayele Girma [993 days ago.]
 endezih Aynet Ye Football Beteseb bedenb Ktat Yasfelgewal. Tegbarawi Adirgu.

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!