ሊዲያ ታፈሰ በ2015ቱ የካናዳው የሴቶች የዓለም ዋንጫ በዋና ዳኝነት ጨዋታዎችን ትመራለች።
መጋቢት 22, 2015

የኢት.እግ.ኳስ.ፌዴ ዛሬ በላከልን መረጃ መሰረት ኢንተርናሽናል ዳኛ ሊዲያ ታፈሰ ካናዳ ላይ  በሚዘጋጀው የ2015ቱ የሴቶች የዓለም ዋንጫ በዳኝነት ጨዋታዎችን እንዲመሩ ከአፍሪካ ከተመረጡ  ሶስት ዳኞች አንዷ ለመሆን በቅታልች። ፊፋ በአጠቃላይ 22  ዋና ዳኞችን 7 ደጋፊ ዳኞችን እንዲሁም 44 ረዳት የመስመር ዳኞችን ለውድድሩ ከ49 ሀገራት መርጧል።  ከአፍሪካ ለዋና ዳኝነት ኢትዮጵያ፣ታንዛኒያና ካሜሩን ሲያስመርጡ  ለረዳት ዳኝነት ቶጎ፣ማላዊ፣ሞሮኮና ማዳጋስካር  እያንዳንዳቸው አንድ አንድ ረዳት ዳኞችን ለማስመረጥ ችለዋል።
Lidya Tafesse

ለአፍሪካ ከተሰጠው ጠባብ እድል አንጻር ኢትዮጵያዊቷ ሊዲያ ታፈሰ ለዚህ ታላቅ የእግር ኳስ ውድድር ዳኝነት በብቃት መመረጧ  ለሀገራችን የሴቶች እግር ኳስ ዳኝነት እድገት እንዲሁም በአለም አቀፍ ደረጃ ተሰሚነትንና እውቅናን ለማግኘት ያስቻለ በመሆኑ ዋና ዳኛ ሊዲያን እንዲሁም በሴቶች እግር ኳስ ዙሪያ በአለም አቀፍ ደረጃ ውጤት ለማምጣት ጥረት እያደረጉ ያሉትን አካላት ሁሉ የሚያስመሰግንና እንኳን ደስ ያላችሁ የሚያስብል ነው። ወደፊትም በይበልጥ በመስራት በርካታ ዳኞችን ወደ አለም አቀፉ መድረክ ብቅ እንዲሉ በፌዴሬሽኑ በኩል እየተደረገ ያለው ጥረት ይበርታ ይቀጥል እንላለን። 

በሌላ ዜና የሴት ወጌሻዎች ስልጠና በባህርዳር ከተማ መሰጠት መጀመሩን ፌዴሬሽኑ አስታውቋል።  ስልጠናው  በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እና በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መስተዳድር እግር ኳስ ፌዴሬሽን የተዘጋጀ ሲሆን ከመጋቢት 21 ቀን 2ዐዐ7 ዓ.ም እስከ መጋቢት 30 በባህርዳር ከተማ እንደሚካሄድ ታውቋል። 

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!