ደደቢት እግር ኳስ ክለብ በፎርፌ ወደ ቀጣዩ ዙር ሊያልፍ ይችላል ተባለ
መጋቢት 23, 2007

የደደቢት እግር ኳስ ክለብ በአፍሪካ ክለቦች ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ እየተወዳደረ መሆኑ ይተወሳል። ከ15 ቀን በፊት በናይጄሪያ የመጀመሪያ ጨዋታውን አድርጎ ሁለት ለባዶ ተሸንፎ የተመለሰው ደደቢት የፊታችን እሁድ በባህር ዳር የመልስ ጨዋታውን እንደሚያካሂድ እየተጠበቀ ባለበት ወቅት የናይጄሪያው ክለብ በበጀት እጥረት ምክንያት ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ መጫወት እንደማይችል እየተገለጸ ነው።
Dedebit FC
 
እስከ ትናንት እኩለ ቀን ድረስ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጣበትን የአውሮፕላን ትኬት እንዳልቆረጠ የተገለጸው ዎሪ ዎልቭስ ለጉዞና ለሆቴል የሚያስፈልገውን ወጭ የሚሸፍንለት ገንዘብ የማያገኝ ከሆነና ወደ ኢትዮጵያ የማይመጣ ከሆነ ደደቢት በፎርፌ ወደ ቀጣዩ ዙር የሚያልፍ ይሆናል። ሁለቱ ቡድኖች በመጀመሪያ ጨዋታቸው ናይጄሪያ ላይ ባለሜዳው ቡድን ሁለት ለባዶ ማሸነፉ የሚታወስ ሲሆን ዎሪ ዎልቭስ ፎርፌ የሚሰጥ ከሆነ ደደቢት በድምር ውጤት ሶስት ለሁለት በሆነ ውጤት ወደ ቀጣዩ ዙር የሚያልፍ ይሆናል ማለት ነው።  

በሌላ ዜና ደግሞ የደደቢት እግር ኳስ ክለብ ከዎሪ ዎልቭስ ጋር የፊታችን እሁድ ላለበት የመልስ ጨዋታ ቡድኑ ትናንት ባህር ዳር መግባቱ ተገልጿል። ዎሪ ዎልቭስ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጣ ከሆነና የመልስ ጨዋታው የሚካሄድ ከሆነ ደደቢት ወደ ቀጣዩ ዙር ለማለፍ በቡድኑ በኩል ዝግጅቱን ማጠናቀቁን የክለቡ አሰልጣኝ ተናግረዋል። ጉዳት የነበረው ተከላካዩ ስዩም ተስፋዬ በእሁዱ ጨዋታ የሚሰለፍ መሆኑንም አሰልጣኝ ዮሃንስ ሣህሌ ተናግረዋል። 

ኢትዮ ፉትቦል

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!