እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዛሬ ግምገማ ያካሂዳል
መጋቢት 23, 2007

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው በብሔራዊ ሊግ የሚሳተፉ ክለቦችን የውድድር ዘመን ግማሽ ጉዞ በሚመለከት በኢትዮጵያ ሆቴል ግምገማ ያካሂዳል። በግምገማው የፕሮግራም አወጣጥን ጨምሮ በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ እንደሚነሱ ተገልጿል።
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ሊግ ከሚታዩ በርካታ ችግሮች መካከል በቀዳሚነት የሚነሱት የዳኝነት ከአድሏዊ ያልጸዳ ውሳኔ፣ ስፖርታዊ ጨዋነት፣ እንዲሁም ጸጥታና የሜዳዎች ለውድድር ምቹ አለመሆን ይገኙበታል፡፡ በዛሬው ግምገማም እነዚህን ጉዳዮች የግምገማው ተሳታፊዎች እንደሚወያዩባቸው ይጠበቃል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም አዲስ የወጣውን የተጫዋቾች ዝውውር መመሪያም ለውይይት የሚቀርብ አጀንዳ መሆኑን ከፌዴሬሽኑ የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡ ግምገማው ከረፋዱ ሶስት ሰዓት እንደሚጀመርም መረጃው ጨምሮ ገልጿል፡፡ ግምገማውን ሁሉም የስፖርት መገናኛ ብዙሃን ጋዜጠኞች እንዲሳተፉ ተገልጿል፡፡ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ሊግ የሚወዳደሩ ክለቦች ብዛት 82 ናቸው፡፡


ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!