የደደቢትንና የዎሪዎልቭስን ጨዋታ የጊኒ ቢሳው ዳኞች ይመሩታል ኮሚሽነሩ ዩጋንዳዊ ናቸው
መጋቢት 25, 2007

በገንዘብ ችግር የተነሳ ከደደቢት ጋር የሚያደርገውን ጨዋታ ሰርዞታል ተብሎ ሲነገርበት የቆየው የናይጄሪያው ዎሪ ዎልቭስ ክለብ ከነገ በስቲያ ለሚያደርገው ጨዋታ ዛሬ አዲስ አበባ እንደሚገባ ተነገረ። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የህዝብ ግንኙነት ክፍል ለዝግጅት ክፍላችን በላከው መረጃ እንደጠቆመው የናይጄሪያው ክለብ ዛሬ ከምሽቱ 2፡50 ሰዓት አዲስ አበባ ይገባል ተብሎ ይጠበቃል። ቡድኑ ዛሬ ምሽት አዲስ አበባ ከገባ በኋላም ነገ ጠዋት ወደ ባህር ዳር የሚሄድ መሆኑን የገለጸው የፌዴሬሽኑ መረጃ፤ ዳኞቹ ግን ዛሬ ወደ ባህር ዳር ተጉዘዋል ሲል ገልጿል። 
Bahirdar Stadium

ሁለቱ ቡድኖች ከ15 ቀናት በፊት ናይጀሪያ ላይ ዎሪ ዎልቭስ ሁለት ለባዶ ማሸነፉ የሚታወስ ነው። በዚያ ጨዋታ አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ ጨዋታውን የመሩት ዳኛ ፍትሃዊ ያልሆ የዳኝነት ውሳኔ አስተላልፈዋል ሲሉ ቅሬታቸውን ማሰማታቸውም አይዘነጋም። አሰልጣኝ ዮሃንስ በእሁዱ ጨዋታ ክለባቸው ተጋጣሚውን አሸንፎ ወደ ቀጣዩ ዙር ለማለፍ ከፍተኛ ዝግጅት ማድረጋቸውን ከተለያዩ የዜና ምንጮች ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
 


ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!