ቅዱስ ጊዮርጊስ ከመከላከያ የሳምንቱ ታላቅ ጨዋታ
መጋቢት 25, 2007

አሉላ ግርማና  ዳዋ ሁጤሳ ከጉዳታቸው አገግመው ልምምድ ሰርተዋል። ጨዋታውን አሸንፈን ለመውጣት የሚያስችል ዝግጅት አድርገናል። ከቅዱስ ጊዮርጊስ ዋና አሰልጣኞች አንዱ የሆነው ዘሪሁን ሸንገታ ከኢትዮ ፉትቦል 

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 16ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ነገ ቅዱስ ጊዮርጊስ መከላከያን የሚያስተናግድበት ጨዋታ ትልቅ ትኩረት ያገኘ ጨዋታ ሆኗል። ፈረሰኞቹ ብራዚላዊውን አሰልጣኝ ኔይደር ዶሳንቶስን ካሰናበቱ በኋላ በሁለት ኢትዮጵያውያን አሰልጣኞች እየተመሩ በጥሩ የራስ መተማመን ላይ መሆናቸው እየተነገረ ሲሆን የገብረመድህን ሀይሌ ቡድን መከላከያ ደግሞ ሁሉተኛውን ዙር በድል የጀመረ መሆኑ ጨዋታውን እንዲጠበቅ ያደርገዋል። በተለይ በቅዱስ ጊዮርጊስ በኩል ከአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ በጊዜ መሰናበቱ እና አዲሱ የዋንጫ ተቀናቃኝ ሆኖ ብቅ ያለው ሲዳማ ቡና የፕሪሚየር ሊጉን መሪነት የተቆጣጠረ በመሆኑ በነገው ጨዋታ መከላከያን አሸንፈው ወደ መሪነቱ በመመለስ ለቀጣይ ዓመት የአህጉራዊ ውድድር ተሳታፊነት የሚያረጋግጥለትን የሊጉ ዋንጫ ባለቤት መሆኑን ለማረጋገጥ ይጫወታል። 
Defence Force Vs St.George

ከቅዱስ ጊዮርጊስ ዋና አሰልጣኞች አንዱ የሆነው ዘሪሁን ሸንገታ ከኢትዮ ፉትቦል ዶትኮም ጋር በስልክ ባደረገው ቃለ ምልልስ በነገው ጨዋታ አሸናፊ ለመሆን የተዘጋጀ ቡድን መገንባቱን ተናግሯል። አሰልጣኝ ዘሪሁን ጉዳት ላይ የቆዩት ዳዋ ሁጤሳ እና አሉላ ግርማ ልምምድ የጀመሩ መሆናቸውን ገልጾ እስከ ነገ ድረስ ልጆቹ የሚኖራቸው ማች ፊትነስ ታይቶ ሊሰለፉ እንደሚችሉ ተናግሯል። “ነገር ግን ሁለቱ ልጆች ተሰለፉም አልተሰለፉም ቡድናችን ጥሩ ዝግጅት ያደረገ በመሆኑ ጨዋታውን አሸንፈን ለመውጣት የሚያስችል ዝግጅት አድርገናል። የቡድኑ ስብስብም ሆነ የተጫዋቾች ስነ ልቦና ዝግጁነት ጥሩ ነው” ሲል ተናግሯል። 

በተያያዘ ዜና የቅዱስ ጊዮርጊሱ አማካይ ምንያህል ተሾመ በ15ኛ ሳምንት የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስና ወላይታ ድቻ ሲጫወቱ በቀይ ካርድ መባረሩ ይታወሳል። ከቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ በደረሰን መረጃ መሰረት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዲስፕሊን ኮሚቴ ምንያህል ተሾመን ስድስት ጨዋታ እንደቀጣው ታውቋል። ቅጣቱም ነገ ፈረሰኞቹ ከመከላከያ ከሚያደርጉት ጨዋታ ጀምሮ ተፈጻሚ እንደሚሆን የተነገረ ሲሆን ክለቡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ግን ውሳኔውን ተቃውሞ ይግባኝ እንደሚጠይቅ ገልጿል። 

በሌላ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ትናንት ወልድያ ላይ ሁለቱ ያለፈው ዓመት የብሔራዊ ሊግ የፍጻሜ ተፋላሚዎች ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል። ሁለቱ ቡድኖች በመጀመሪያው ዙር የፕሪሚየር ሊግ ግንኙነታቸው አዳማ ላይ ባለሜዳው አዳማ ከነማ ሶስት ለአንድ አሸንፎ እንደነበረ የሚታወስ ነው። 

ፕሪሚየር ሊጉን ሲዳማ ቡና በ17 ጨዋታዎች 32 ነጥብና ሰባት ተጨማሪ የጎል ክፍያ ይዞ ሲመራው ፈረሰኞቹ አንድ ተስተካካይ ጨዋታ እየቀራቸው ከመሪው በአንድ ነጥብ ዝቅ ብለው ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። ኢትዮጵያ ቡና እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደግሞ ሶስተኛና አራተኛ ደረጃን ይዘዋል። ወራጅ ቀጠናውን ሃዋሳ ከነማ፣ ሙገር ሲሚንቶ እና ወልድያ ከነማ ይዘውታል።

ካሳ ሀይሉ
ኢትዮ ፉትቦል 

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
Mali [1055 days ago.]
 come on Sanjeye enbelawallen Mengizem Giyorgis !!! VVVVVVVVVVVVVVVVVVV !!!

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!