መከላከያና ቅዱስ ጊዮርጊስ ነጥብ ተጋሩ
መጋቢት 27, 2007

በፕሪሚየር ሊጉ 17ኛ ሳምንት ትላንት ማምሻውን የተገናኙት መከላከያና ቅዱስ ጊዮርጊስ ሳይሸናነፉ 0ለ0 በመለያየት ነጥብ ተጋርተው ወጥተዋል። ጨዋታው መከላከያ እያሳየ ካለው የሁለተኛው ዙር ውጤታማ አጀማመር እንዲሁም ቅዱስ ጊዮርጊስ የውጭ ሀገር አሰልጣኙን ካሰናበተ በኋላ ባሳየው ውጤታማነት ምክንያት በተመልካች ዘንድ ጥሩ ፉክክል ይታይበታል ተብሎ ግምት የተሰጠው ነበር።  ነግር ግን ጨዋታው በመጨረሻዎቹ 20 ደቂቃዎች በሁለቱም ወገን ተደጋጋሚ የጐል  ሙከራ  ከመደረጉ  በቀር የመጀመሪያዎቹ 70 ደቂቃዎች ባብዛኛው ጨዋታውን አሁንም አሁንም በሚያቋርጥ የዳኛ ፊሽካና  የተጨዋቾች ለተቃራኒ ቡድን ኳስ አሳልፎ የማቀበል ድራማ የታጀበ ነበር።

Defense Vs St.George


 በጨዋታው ጥሩ እንቅስቃሴ በተደረገባቸው በመጨረሻዎቹ  20 ደቂቃዎች በ71ኛውና በ72ኛው መከላከያ እንዲሁም በ75ኛው እና በ77ኛው ደቂቃ ጊዮርጊሶች  ጎል ሊሆኑ የሚችሉ አጋጣሚዎችን አግኝተው ሳይጠቀሙበት ቀርተዋል። በተለይ  በ80ኛው ደቂቃ ላይ መከላከያዎች ያልተጠቀሙበት ምርጥ አጋጣሚ ተከስቶላቸው ነበር። በትላንትናው እለት ለመከላከያ ጥሩ ሲንቀሳቀስ የነበረው 10 ቁጥሩ ፍሬው ሰለሞን በመልሶ ማጥቃት መሃል ላይ የተቀበላትን ኳስ ወደፊት በመግፋት አንድ ተጨዋች አልፎ ለ14 ቁጥሩ ምንይሉ ወንድሙ በሁለት ተጫዋቾች መሃል ቀዶ በማሳለፍ ምንይሉ ወንድሙን ከበረኛ ጋር ቢያፋጥጠውም ምንይሉ ወንድሙ ኳሷን ወደ ጎል ቀጥታ በመምታት ውጤታማ መሆን ሲችል በረኛውን አልፎ ጎል ለማግባት የወሰደው ቅስበታዊ ውሳኔ ምክንያት ውጤታማ ሳይሆን ቀርቷል። ለዚች አስገራሚ ጓስ መክሸፍ የቅዱስ ጊዮርጊሱ በረኛ ሮበርት ኦዶንኮራ ቀድሞ ከጎል ክልሉ በመውጣት  ጎሉን አጥብቦ መሸፈን ከፍተኛ አስታዋጽኦ አድርጓል።  ኦዶንኮራ በጨዋታው የመጀመሪያ ደቂቃ ላይ ከፍጹም ቅጣት ምት መስመር ላይ  ወደግብ የተመታበትን ቅጣት  ምትም በድንቅ ብቃት ተወርውሮ አድኗል። 
Defense Vs St.George

የጨዋታው ማብቂያ ላይ ፊሽካ እንደተነፋ በውጤቱ የተበሳጩ የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች በቡድናቸው ተጫዋቾችና አሰልጣኞች ላይ ቁጣቸውን ሲገልጹ ተስተውሏል። ቁጣቸው ተገቢነት ሊኖረው ቢችልም አንዳንድ ተመልካቾች የተጨዋቾችን ስም እየጠሩ አላስፈላጊ ቃላት መሰንዘራቸው ተገቢነት የለውም የማሊያ ፍቅርንም አያሳይም ሊታረም ይገባል እንላለን። ቡድኑ ውጤት ባጣም ጊዜ ቢሆን ተጫዋቾችን ማበረታትና ወደፊት በጥሩ ዝግጅት እንዲገቡ ማገዝና መደገፍ ሲገባ ተጫዋቾችን መሳደብ በምንም መልኩ ውጤታማነትን አያስገኝም። 

በሌላ ዜና በሁለተኛው ዙር ውጤት እየቀናው የመጣው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ከኢትዮጵያ ኤሌትሪክ ጋር በአዲስ አበባ ስታዲየም 11:30 የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።


ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!