ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር የ80ኒያኛ ክብረ በዓል ማድመቂያ ሎጎውን አስመረቀ
መጋቢት 27, 2007

ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር በሚቀጥለው አመት ለሚያከብረው የ80ኒያኛ ክብረ በዓል ማድመቂያ እንዲሆን  አስቦ ያሰራውን አዲስ ሎጎ በዛሬው እለት በስፖርት ማህበሩ ጽቤት አስመርቋል። በስነስርአቱ ላይ የስፖርት ማህበሩ ፕሬዚዳንት አቶ አብነት ገብረመስቀል እንዲሁም የቦርድ አባላትና የክለቡ ደጋፊዎች ተገኝተዋል። 
St.George 80th Anniversary Logo

በስነስርአቱ ላይ በክብረ በዓሉ ዙሪያ ስለሚደረጉ ዝግጅቶችና እቅዶች በአዘጋጅ ኮሚቴው ቀርበዋል። በዚሁም መሰረት የ80ኛ ዓመት ክብረ በዓሉ ከመጪው ሚያዚያ 10 ጀምሮ በተለያዩ ዝግጅቶች መከበር እንደሚጀመር ታውቋል።  

በዚሁ ዛሬ በተደረገው የሎጎ ማስመረቂያ ስነስርአት ላይ በተደረገ ሌላ ሴርሞኒ ባለፈው አመት የዋንጫ ሽልማት ላገኘው የክለቡ የታዳጊ ቡድን አባላት የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። ሽልማቱ በውድድሩ ኮከብ አሰልጣኝ ኮከብ በረኛና ኮከብ ተጫዋች ሆነው ለተመረጡት 3,500 ብር ሲሆን ለተቀሩት የቡድኑ አባላት 3,000 ብር መሆኑነን የክለቡ ሥራ አስኪያጅ አቶ ሶሎሞን በቀለ ነግረውናል። 

ፈለቀ ደምሴ


 

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
Nati [983 days ago.]
 Bravooooooo Sanjaweeeeeeeee

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!