ኢትዮጵያ ቡና ከዳሽን ቢራ ለሁለቱም ቡድኖች ወሳኝነት ያለው ፍልሚያ
መጋቢት 28, 2007

17 ዓመታትን ያስቆጠረው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 17ኛ ሳምንት መርሃ ግብሩን ከትናንት በስቲያ መከላከያና ቅዱስ ጊዮርጊስ ባደረጉት ጨዋታ ተጀምሯል። ሁለቱ ቡድኖች ያለ ግብ መሳ ለመሳ በተለያዩበት ጨዋታ ማግስት ትናንት በአዲስ አበባ ስታዲየም ንግድ ባንክና ኤሌክትሪክ ክለብ ተገናኝተው ንግድ ባንክ ሶስት ለባዶ አሸንፏል። ለንግድ ባንክ የማሸነፊያዎቹን ጎሎች ደረጀ መንግስቱ አንድ እና ናይጄሪያዊው ፍሊፕ ዳውዝ ቀሪዎቹን ሁለት ጎሎች አስቆጥሯል። ዳውዝ ትናንት በቀድሞ ክለቡ ላይ ሁለት ጎሎችን በማስቆጠሩም የፕሪሚየር ሊግ ኮከብ ጎል አግቢነት ደረጃውን ከሚመራው ቢኒያም አሰፋ ጋር የነበረውን ልዩነት እንዲያጠብ አስችሎታል። 
Ethiopian Coffee Supporters

ፕሪሚየር ሊጉ ዛሬም ቀጥሎ ሲካሄድ በአዲስ አበባ ስታዲየም ከቀኑ 11፡30 ላይ ኢትዮጵያ ቡና የአማራ ክልሉን ዳሽን ቢራን ያስተናግዳል። በቅርቡ ከኢትዮጵያ ቡና በውሰት ዳሽን ቢራን የተቀላቀለው ቶጓዊው ኤዶም የጨዋታው ትኩረት ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። ከኤዶም በተጨማሪም የቡናዎቹ ተጫዋቾች አማካዩ ደረጀ ሀይሉና ተከላካዩ ኤፍሬም ወንደሰን የቀድሞ ክለባቸውን የሚገጥሙ ይሆናል። የዳሽን ቢራው ምክትል አሰልጣኝ ካሊድ መሃመድም ቀድሞ የተጫወተለትንና በኋላም አሰልጣኝ ሆኖ ያገለገለውን ኢትዮጵያ ቡናን በሌላ ክለብ የሚፋለምበት ምሽትም ነው። 
Coffee vs Supporters

ሌላው የጨዋታው ልዩ ክስተት የሚሆነው ደግሞ ፕሪሚየር ሊጉ ሲጀመር በተከታታይ ሁለት ጨዋታዎችን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክና ሙገር ሲሚንቶ ተሸንፎ በውጤት ቀውስ ውስጥ የነበረው ቡና የመጀመሪያ ሙሉ ሶስት ነጥቡን ያገኘው ጎንደር ላይ ዳሽን ቢራን በማሸነፍ ነበር። በዚያ ጨዋታ ቡና የመጀመሪያ ሙሉ ሶስት ነጥብ ብቻ ሳይሆን በፕሪሚየር ሊጉ የዓመቱን የመጀመሪያ ጎልም ያስቆጠረው በዳሽን ቢራ መረብ ላይ ነው ጎንደር ላይ። በዚህ የውድድር ዓመት በአንድ ጨዋታ ከአንድ ክለብ ሁለት ተጫዋቾች በቀይ ካርድ የተሰናበቱበት ጨዋታ ዳሽን ቢራ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ያደረጉት ጨዋታ መሆኑ ይታወሳል። በዚያ ጨዋታ ሁለቱን ቀይ ካርዶች የተመለከቱት የቡናዎቹ ተጫዋቾች ተከላካዩ ሮቤል ግርማ እና ግብ ጠባቂው ሙሴ ገብረ ኪዳን ነበሩ። 

ከዚህ ሁሉ በላይ ጨዋታውን ተጠባቂ የሚያደርገው ግን የውጤቱ አስፈላጊነት ነው። ቡና ይህንን ጨዋታ የማያሸንፍ ከሆነ ንግድ ባንክ የወሰደበትን ሶስተኛነት ደረጃ ሊያስመልስ አይችልም።  በሁለተኛው ዙር በፕሪሚየር ሊጉ የዋንጫ ተፎካካሪ እየሆነ የመጣውን ለወትሮው ደረጃ መዳቢው በመባል የሚታወቀው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ  ከመበለጥም በዘለለ እንደ ወላይታ ድቻ አይነት ከስር ከስር የሚከታተሉ ክለቦችም በቀጣዮቹ ጨዋታዎቻቸው ማሸነፍ ከቻሉ ከኢትዮጵያ ቡና በላይ የሚያደርጋቸውን ነጥብ ስለሚሰበስቡ ለዋንጫ እየተጫወተ ያለው ኢትዮጵያ ቡና ከመሪዎቹ በብዙ ማይል ርቆ ከሊጉ ወገብ ላይ እንዲቀመጥ ሊያስገድደው ይችላል።  በመሆኑም ኢትዮጵያ ቡናዎች በዋና የግብ አዳኛቸው ቢኒያም አሰፋ እንዲሁም ፈጣኑ የአማካኝ ተጫዋች አስቻለው ግርማ እንዲሁም የቡድኑ አምበል ዳዊት እስጢፋኖስን በማቀናጀት  የፊት መስመሩን አጠናክረው ሙሉ ነጥብ ይዘው በመውጣት የዋንጫ ተፎካካሪነታቸውን አጠናክረው ደጋፊዎቻቸውን ለማስደሰት  እንደሚጫወቱ የሚጠበቅ ነው።  

በዳሽን ቢራ በኩል ደግሞ በዚህ ጨዋታ ድል ከተነሱ ጎረቤታቸው ወልድያ ከነማና ሙገር ሲሚንቶ በብቸኝነት የተቆጣጠሩትን የወራጅ ቀጠና ምድብ እንዲቀላቀሉ   ያደርጋቸዋል። በዚህም ምክንያት በጨዋታው አሸናፊ ሆኖ ለመውጣት ሁለቱም ክለቦች ጨዋታውን አሸንፎ ለመውጣት በሂሳብ ስሌት የተቀመረ ጨዋታ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።

በጨዋታው በኩል የኢትዮጵያ ቡናው ካሜሩናዊ ተከላካይ ዊልቨር ካጋጠመው መጠነኛ ጉዳት አገግሞ ልምምድ መጀመሩን ከክለቡ የሀዝብ ግንኙነት መረጃው የደረሰን ሲሆን የመሰለፉ ጉዳይ ግን ገና አልተረጋገጠም። ሌሎቹ ተጫዋቾች ግን አምበሉን ዳዊት እስጢፋኖስን ጨምሮ በሙሉ ጤንነት ላይ ይገኛሉ ተብሏል። 
ጨዋታው ነገ ከአመሻሹ 11፡30 ጀምሮ በአዲስ አበባ ስታዲየም የሚካሄድ ሲሆን ኢትዮፉትቦል ዶትኮም ጨዋታውን በቀጥታ ስርጭት Live Score  የሚያስተላልፍ መሆኑን እንገልጻለን። 

ካሳ ሀይሉ
ኢትዮ ፉትቦላ


ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
Muluken Alemayehu [1053 days ago.]
 Bewnet yageren premier league endi sefa bale tintena silakerebachu betam amesegnalhu bertu bezihu ketilu.

Muluken Alemayehu [1053 days ago.]
 Bewnet yageren premier league endi sefa bale tintena silakerebachu betam amesegnalhu bertu bezihu ketilu.

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!