የመሪዎቹ ፍልሚያ በፋሲካ ዋዜማ
ሚያዚያ 02, 2007

ቅዳሜ ከቀኑ አስር ሰዓት አንጋፋው አዲስ አበባ ስታዲየም አንጋፋውን ቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ እና የፕሪሚየር ሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን ያገናኛል። 

St.George Vs Sidama Coffee

ሁለቱ ቡድኖች በፕሪሚየር ሊጉ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጡ በመሆናቸው የነገውን ጨዋታ አጓጊና ተጠባቂ እንዲሆን አድርጎታል። በፕሪሚየር ሊጉ ታሪክ የዋንጫውን ጆሮ ጨብጦ የማያውቀው ሲዳማ ቡና በዚህ ዓመት የዋንጫውን ድል በማግኘት ደጋፊዎቹን ለማስፈንደቅ ቆርጦ የተነሳ መስሏል። ፈረሰኞቹ በበኩላቸው ዋንጫውን ለ11 ጊዜ በማንሳት ከሁሉም የአገሪቱ ክለቦች የላቀ ታሪክ ቢኖራቸውም አሁንም ለድል የተራበ ቡድን እንዳላቸው እየገለጹ ይገኛሉ። 

በተደጋጋሚ ጊዜ አህጉራዊ ውድድሮችን በመሳተፍ ልምድ ያላቸው ፈረሰኞቹ በዚህ ዓመት ከውድድሩ በጊዜ የተሰናበቱ ሲሆን በቀጣዩ ዓመት ለመሳተፍ ደግሞ የፕሪሚየር ሊጉን ወይም የጥሎማለፉን ዋንጫ ማንሳት ግድ ይላቸዋል። የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ እንዳያነሱ ስጋት የሆነባቸው ደግሞ እንደ ቀድሞው መብራት ኃይል ደደቢት ኢትዮጵያ ቡና እና ሃዋሳ ከነማ አይነት ታላላቅ ክለቦች ሳይሆኑ የነገ ተጋጣሚያቸው ሲዳማ ቡና ነው። በአሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው ወይም ሞሪንሆ የሚሰለጥኑት የሲዳማ ዞን ተወካዮቹ ፕሪሚየር ሊጉን ከቅዱስ ጊዮርጊስ በሶስት ነጥብ ከፍ ብለው እየመሩት ሲሆን በነገው ጨዋታ ሜዳ ላይ ቢያንስ አንድ ነጥብ ይዘው መውጣት ከቻሉ በፈረሰኞቹ የሊጉ አሸናፊነት ምኞት ላይ ከባድ ፈተና ይጥሉባቸዋል። በአንጻሩ በሊጉ ሁለተኛ ዙር ላይ ጎልተው በመውጣት ተለይተው የሚታወቁት ፈረሰኞቹ እንግዳውን ቡድን አሸንፈው ከሸኙት የሊጉን መሪነታቸውን ከመቀበላቸውም በላይ የዋንጫውን ጆሮ ለመጨበጥ የተሻለ ተስፋ ይይዛሉ። 

ሁለቱ ቡድኖች በመጀመሪያው ዙር ግጥሚያቸው ይርጋዓለም ላይ ፈረሰኞቹ ሁለት ለባዶ ማሸነፋቸው የሚታወስ ነው። የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ቀደም ሲል ፕሮግራም ተይዞለት የነበረው እሁድ ሚያዝያ አራት ቀን ቢሆንም ባልታወቀ ምክንያት ጨዋታው ወደ ነገ መዛወሩን ፌዴሬሽኑ ገልጿል። ይህንን ጨዋታ ኢትዮፉትቦል ዶትኮም ከቀኑ 9፡30 ጀምሮ በቀጥታ የሚያስተላልፍ መሆኑን ይገልጻል። 

በተያያዘ ዜና በህዳሴው ግድብ አራተኛ ዓመት ክብረ በዓል እና ደደቢት በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን የመልስ ጨዋታ ምክንያት ለሌላ ቀን የተላለፈው 17ኛ ሳምንት የፕሪሚየር ሊጉ ቀሪ ጨዋታ ዛሬ እንደሚካሄድ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ፕሪሚየር ሊጉን ከላይ ሲዳማ ቡና ከፈረሰኞቹ በሶስት ነጥብ ከፍ ብለው ሲመሩት ከታች ደግሞ ወልድያ ከነማ ያለማንም ጣልቃ ገብነት የግርጌው ቋሚ ተሰላፊ ሆኖ ቀጥሏል። ቢኒያም አሰፋ እና ፍሊፕ ዳውዝ በ13 እና 11 ጎሎች የሊጉን ኮከብ ጎል አግቢዎች ደረጃ ተቆጣጥረውታል። ኤሌክትሪክ ክለብ በሊጉ ሁለተኛ ዙር ያደረጋቸውን አራት ጨዋታዎች በሙሉ በመሸነፍ ወደ ታችኛው ቀጠና በፍጥነት እየተጓዘ ሲሆን ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አራቱንም አሸንፎ ደረጃውን በአስገራሚ ፍጥነት ሲያሻሽል፤ ሃዋሳ ከነማ ደግሞ በሶስት ጨዋታ ሰባት ነጥብ በመሰብሰብ የወራጅነት ስጋቱን መቀነስ ችሏል። ሙገር ሲሚንቶም ለወራት ከቆየበት የግርጌው ቀጠና ኤሌክትሪክን በማሸነፍ ወደ 11ኛ ከፍ ማለት ችሏል። 

ካሳ ሀይሉ 
ኢትዮ ፉትቦል

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
mebrate markos [981 days ago.]
 ካሳ ሀይሉ betam stupid journalistsibza dedeb neh ish antem bilo gazetegn

ZAK [979 days ago.]
 BERTU

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!