ኢትዮጵያ ቡና አሰልጣኝ ጥላሁን መንገሻን አሰናበተ
ሚያዚያ 06, 2007

ኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ አሰልጣኝ ጥላሁን መንገሻን አሰናብቶ በምትኩ ምክትል አሰልጣኙን የቀድሞው የቡና ተጫዋች የነበረውን አኑዋር ያሲንን  በዋና አሰልጣኝነት እንዲያሰለጥን መሾሙን ለዝግጅት ክፍላችን ከክለቡ ምንጮቻችን የደረሰን ዜና ያስረዳል።
Tilahun Mengesha Fired From his Ethiopian Coffee Head Coach Post


በተያያዘ ዜና ዳሽን ቢራ ዋና አሰልጣኙን ሳምሶን አየለን ማሰናበቱ ታውቋል።  በሳምሶን ምትክም እስከ አመቱ መጨረሻ በምክትል አሰልጣኝነት ቡድኑን እያገለገለ የነበረውን ካሊድ መሃመድን መሾሙን አስታውቋል። 

ካሊድ መሀመድ የቀድሞ ቡና ተጫዋች ሲሆን በአምናው የውድድር አመት በተመሳሳይ ዳሽን ቢራ ዋና አሰልጣኙን ሲያሰናብት ቡድኑን ይዞ ከመውረድ እንዲድን አድርጓል። ከሶስት አመት በፊት ኢትዮጵያ ቡና በጸጋዬ ኪዳነማርያም ሲሰለጥን በምክትል አሰልጣኝነት እስከግማሽ አመቱ ከአገለገለ በኋላ ጸጋዬ ኪዳነማርያም ለስልጠና ወደ ሀንጋሪ  በመጓዙ ካሊድ ቡድኑን በዋና አሰልጣኝነት በመያዝ የውድድር አመቱን ሁለተኛ ሆኖ እንዲጨርስ ማስቻሉ ይታወሳል። 

ፈለቀ ደምሴ
ኢትዮ ፉትቦል


ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
abebe [1010 days ago.]
 A right decision, because it not fair to lose to Arbaminch.

zemedu [1009 days ago.]
 zemedu

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!