ታላቁ የሸገር ደርቢ ኢትዮጵያ ቡና ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ
ሚያዚያ 09, 2007


  • “ቀሪዎቹን የጨዋታ ጊዜያት በድል በመወጣት ከአዲሱ አሰልጣኛችን ጋር ስኬታማ ጊዜ እንዲኖረን እንሰራለን። ድሉንም በዚህ ጨዋታ እንጀምራለን”  ዳዊት እስጢፋኖስ

  • “ለዋንጫ የምናደርገውን ጉዞ ለማሳመር ይህን ወሳኝ ጨዋታ ለማሸነፍ እንጫወታለን።  ደጋፊዎች በሙሉ ስፖርታዊ ጨዋነት ጨዋታውን እንዲከታተሉ መልዕክቴን አስተላልፋለሁ”   አዳነ ግርማ

የ2007 ዓ.ም ሶስተኛው ታላቁ ሸገር ደርቢ ምን ይዞ መጥቷል?

Ethiopian Coffee Vs St.George

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከሚፋለሙ ክለቦች መካከል ከፍተኛ ደጋፊ ያላቸውና በከፍተኛ የፉክክር ስሜት ታጅቦ የሚካሄደው ጨዋታ የኢትዮጵያ ቡና እና የቅዱስ ጊዮርጊስ ጨዋታ ነው። ሁለቱ ክለቦች ያላቸው የውጤት ተቀናቃኝነት ለውድድር የሚቀርብ ባይሆንም ባላቸው የደጋፊ ብዛት እና የቡድን ስብስብ ጥልቀት የተነሳ ጨዋታው ከፍተኛ ትኩረት የሚደረግበት ጨዋታ ነው። ጨዋታውንም በርካታ ደጋፊ በስታዲየም ተገኝቶ የሚከታተለው ሲሆን የመግቢያ ካርድ በማጣት በካምቦሎጆ ዙሪያ ገባ የሚኮለኮለው ደጋፊ ብዛትም የትየለሌ ነው። ከ30 እስከ 35 ሺህ ተመልካቾችን መያዝ እንደሚችል የሚነገርለት ካምቦሎጆ የፊታችን እሁድም ታላቁን የአገሪቱ ደርቢ በዚህ ዓመት ለሶስተኛ ጊዜ ያስተናግዳል።

በዚህ ዓመት ለሶሰተኛ ጊዜ የሚካሄደው የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ በሁለቱም ክለቦች በኩል የአሰልጣኝ ለውጥ የተደረገበትና ሁለቱም ቡድኖች በቀድሞ ዝነኛ ተጨጫዋቾቻቸው እየተመሩ የሚያካሂዱት ጨዋታ ነው። ፈረሰኞቹ በዘሪሁን ሸንገታ እና ፋሲል ተካልኝ ቡናማዎቹ ደግሞ በአንዋር ያሲን ወይም ታላቁ አንዋር እየተመሩ። በዚህ ዓመት ለመጀመሪያ ጊዜ የተገናኙት በአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ግማሽ ፍጻሜ ላይ ሲሆን መደበኛውን የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ሁለት እኩል ተለያይተው በመለያ ምት ቡናማዎቹ ማሸነፋቸው ይታወሳል። በእለቱ ለአሸናፊዎቹ ቡናዎች ቢነኒያም አሰፋ እና ሻኪሩ ሲያስቆጥሩ ለፈረሰኞቹ ደግሞ ሁለቱንም ጎሎች ወጣቱ አጥቂ ዳዋ ሁጤሳ ማስቆጠሩ ይታወሳል። በዚያ ጨዋታ ቤኒናዊው የቡና አጥቂ ሻኪሩ ለክለቡ ሁለተኛዋን ጎል ካስቆጠረ በኋላ ደስታውን ሲገልጽ ባሳየው ምልክት ምክንያት በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቶ ነበር። የሻኪሩን ድርጊትም በርካታ የስፖርት ቤተሰቡ የተቸው ሲሆን ተጫዋቹም ቆይቶ ይቅርታ ጠይቋል።

ክለቦቹ ለሁለተኛ ጊዜ የተገናኙት በፕሪሚየር ሊጉ የመጀመሪያው ዙር መርሃ ግብር ላይ ነው። በእለቱ የተካሄደው ጨዋታ ሜዳው በቅዱስ ጊዮርጊስ ስም የነበረ ሲሆን አሸናፊ መሆን የቻሉት ደግሞ ቡናዎች ነበሩ በአስቻለው ግርማ ብቸኛ ጎል። በእለቱ ጨዋታውን የመሩት ዳኛ በጨዋታው መጠናቀቂያ ሰዓት ላይ ለፈረሰኞቹ ፍጹም ቅጣት ምት ሰጥተው የነበረ ቢሆንም የፈረሰኞቹ አጥቂ ፍጹም ገብረማሪያም እድሉን ሳይጠቀምበት ቀርቷል። ፍጹም ቅጣት ምቷን በተመለከተ በቡና በኩል ተገቢ ያልሆነ ውሳኔ ነው ሲሉ ተከራክረው የነበረ ቢሆንም ዳኛው በውሳኔያቸው ጸንተው ጥፋት ሰርቷል ያሉትን የቡና አማካይ ጥላሁን ወልዴን በቀይ ካርድ አሰናብተውት ነበር። በዓመቱ ሁለት ጊዜ የተገናኙት ሁለቱ ቡድኖች በሁለቱም ጨዋታ ቡና አሸናፊ ሲሆን ፈረሰኞቹ ደግሞ ሁለት ፍጹም ቅጣት ምት ሲያመክኑ ቡና በበኩሉ ሁለት ተጫዋቾቹን በቀይ ካርድ በማጣት ሪከርድ ይዘዋል።

የፊታችን እሁት በዳግሚያ ትንሳዔው የሚካሄደውን ጨዋታ በአሸናፊነት ለመወጣት በሁለቱም ቡድኖች በኩል ከፍተኛ ዝግጅት መካሄዱን ተጫዋቾቹ ተናግረዋል። በባለሜዳው ቡና በኩል አምበሉ ዳዊት እስጢፋኖስ አሰልጣኝ ጥላሁን መንገሻ በተሰናበተ ማግስት የሚካሄደውን ጨዋታ ቡድናቸው በአሸናፊነት ለመወጣት መዘጋጀታቸውን ገልጾ “ቀሪዎቹን የጨዋታ ጊዜያት በድል በመወጣት ከአዲሱ አሰልጣኛችን ጋር ስኬታማ ጊዜ እንዲኖረን እንሰራለን። ድሉንም በዚህ ጨዋታ እንጀምራለን” ሲል፤ ሁለገቡ የፈረሰኞቹ ተጫዋች አዳነ ግርማ በበኩሉ ጨዋታው ወሳኝ መሆኑን ተናግሮ ቡድናቸው ይህን ጨዋታ አሸንፎ ለዋንጫ የሚያደርገውን ጉዞ እንደሚያሳምር ገልጿል። አዳነ አክሎም “ደጋፊዎች በሙሉ ስፖርታዊ ጨዋነት ጨዋታውን እንዲከታተሉ መልዕክቴን አስተላልፋለሁ” በማለት ተናግሯል።

በጨዋታው በሁለቱም ክለቦች በኩል በጉዳት የማይሰለፍ ተጫዋች መኖሩን ለማረጋገጥ ያደረግነው ሙከራ ባይሳካም የቀድሞው የኢትዮጵያ ቡና የአሁኑ የፈረሰኞቹ አማካይ ምንያህል ተሾመ ግን በቅጣት እንደማይሰለፍ ተረጋግጧል። ኢትዮፉትቦል ዶትኮም በጨዋታው ዙሪያ ተከታታይ ዘገባዎችን እንደምታቀርብ እየገለጽን ጨዋታውንም በቀጥታ እንደምናስተላለፍ ከወዲሁ እንገልጻለን።

በተያያዘ ዜና በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነው ቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ የተመሰረተበትን 80ኛ ዓመት በዓል ለማክበር በዝግጅት ላይ ይገኛል። በዓሉን ለማክበር የተለያዩ ዝግጅቶች እየተካሄዱ መሆኑን የገለጸው የክለቡ የህዝብ ግንኙነት ክፍል ከዝግጀቶቹ መካከል አንዱ የሆነው የሙዚቃ ድግስ ነገ በሚሊኒየም አዳራሽ እንደሚካሄድ አስታውቀል። የሙዚቃ ድገሱን ለመታደም መግቢያ ዋጋው መደበኛ 200 ብር እና ቪአይፒ ደግሞ 500 ብር መሆኑን ከክለቡ የህዝብ ግንኙነት ክፍል ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።  

ካሳ ሀይሉ
ኢትዮ ፉትቦል    

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
kidusyonas [973 days ago.]
 10q

dave [973 days ago.]
 nice info. Have grait game. for ever etho cof.

samuel [972 days ago.]
 if st.gorge choose offensive play , it will be so attractive and we will be a winner. viva San George !!!!!

ዮሀንስ ባንቲሁን [971 days ago.]
 እናመሰግናለን

IBRAHIM [971 days ago.]
 10Q

ኣንደርቢ [581 days ago.]
 ደርቢ ማለት ምን ማለት ነው እስኪ ይነገር። ዝም ብሎ ቃላት መሰንቀር ኣለ እንዴ በፈጣሪ? ኧረ ታሪክን ኣበውን ኣክብሩ። የሸገር ደርቢ ከማለት የሸገር ፍልሚያ ማለት ኣይቀልም። እኔ እንኳ ማይሙ በሰከንድ ውስጥ ይህን ስያሜ ኣመጣሁ። ነው ወይስ የነጮች ባሪያ፥ ኣነፍናፊ ቡችሎች እንድሆን ልንኖር ነው?

ኣንደርቢ [581 days ago.]
 ደርቢ ማለት ምን ማለት ነው እስኪ ይነገር። ዝም ብሎ ቃላት መሰንቀር ኣለ እንዴ በፈጣሪ? ኧረ ታሪክን ኣበውን ኣክብሩ። የሸገር ደርቢ ከማለት የሸገር ፍልሚያ ማለት ኣይቀልም። እኔ እንኳ ማይሙ በሰከንድ ውስጥ ይህን ስያሜ ኣመጣሁ። ነው ወይስ የነጮች ባሪያ፥ ኣነፍናፊ ቡችሎች እንድሆን ልንኖር ነው?

ኣንደርቢ [581 days ago.]
 ኣቶ ካሣ ኃይሉ እባክህ ሁለተኛ «ሸገር ደርቢ» ብለህ ኣትሳሳት። «ሸገር ፍልሚያ» ብለህ ቀይር። እኛ ኣንባቢዎችህም እናከብርሃለን።

ኣንደርቢ [581 days ago.]
 ኣቶ ካሣ ኃይሉ እባክህ ሁለተኛ «ሸገር ደርቢ» ብለህ ኣትሳሳት። «ሸገር ፍልሚያ» ብለህ ቀይር። እኛ ኣንባቢዎችህም እናከብርሃለን።

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!