የኢ.እግ.ኳስ.ፌዴ አሰልጣኝ ማሪያኖ ባሬቶን ማሰናበቱን ይፋ አደረገ
ሚያዚያ 10, 2007

አሰልጣኝ ማሪያኖ ባሬቶ ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝነታቸው መነሳታቸውን ኢትዮ ፉትቦል ከሁለት ሳምንት በፊት ከውስጥ አዋቂዎች ባገኘው መረጃ ማስነበቡ ይታወሳል። ነገር ግን የኢት.እግ.ኳስ.ፌዴሸን ጉዳዩን በይፋ እስካሁን ሳያሳውቅ ቆይቶ ነበር። 

Mariano Bareto Saying Good Bye!

 ዛሬ  ከፌዴረሽኑ ህዝብ ግንኙነት  በደረሰን መረጃ መሰረት አሰልጣኝ ማሪያኖ ባሬቶ እና ፌዴሬሽኑ  ለሁለት አመት እንዲቆይ ተፈራርመው የነበረውን ውል በጋራ ስምምነት ማፍረሳቸውን አስታውቋል። ከፌዴሽኑ የደረሰንን ሙሉ መረጃ እንደሚከተለው አቅርበነዋል።


የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እና አሰልጣኝ ማሪያኖ ባሬቶ
 የተፈራረሙት ውል በስምምነት እንዲቋረጥ ተደረገ
 
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንና አሰልጣኝ ማሪያኖ ባሬቶ እ.ኤ.አ በኤኘሪል 22 ቀን 2014 የተፈራረሙት የሁለት ዓመታት የኮንትራት ውል ሁለቱ ተዋዋይ ወገኖች በደረሱበት የጋራ ስምምነት መሠረት እ.ኤ.አ ከኤኘሪል 30 ቀን 2015 ጀምሮ እንዲቋረጥ ተደርጓል፡፡

የውል ስምምነቱ በዚህ መንገድ እንዲቋረጥ የተደረገው ፌዴሬሽኑና አሠልጣኙ ከላይ በተጠቀሰው ቀን ተፈራርመው የነበረውን የውል ስምምነት መሠረት በማድረግ ሲሆን ለዚህም ሃሣብ መነሻው በጋራ መግባባትና የመከባበር ስሜት እንዲሁም በሠለጠነ አግባብ ውሉን ማቋረጥ ሊከሰት የሚችለውን ውጣ ውረድ ለማስወገድ ወደፊት በትብብር  ለመሥራት የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ነው፡፡

በዚህ አግባብ የውል ስምምነቱ መቋረጡን ተከትሎ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለአሠልጣኝ   ማሪያኖ ባሬቶ የሦስት ወር ደመወዝ ይከፍላል፡፡

በመሆኑም ፌዴሬሽኑና አሠልጣኙ ተፈራርመው የነበረውን የውል ስምምነት በፍፁም የመተማመንና የመከባበር ስሜት በዚህ ዓይነት ሁኔታ እንዲቋረጥ ያደረጉ ሲሆን፤ ቀጣይ ሁኔታዎችን በተመለከተም ሁለቱ አካላት በተተኪ ወጣቶች ላይ የተጀመረው የእግር ኳስ ልማት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ለማድረግ በመተባበር መንፈስና በጋራ ለመሥራት ተስማምተዋል፡፡ በዚህ መሠረት አሠልጣኙ ወጣት ተጫዋቾች ከፍተኛ ሥልጠና እንዲያገኙ ለማድረግ የጀመሩትን ጥረት አጠናክረው ለመቀጠል ቃል የገቡ ሲሆን ፌዴሬሽኑም ሁኔታዎችን ለማመቻቸት ተስማምቷል፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
mekonnen [1006 days ago.]
 congra!!!!!!!!!! ejigi betiam desi yilala

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!