እግር ኳስ ያለደጋፊ አያምርም
ሚያዚያ 11, 2007

  • “በዚህ ወቅት አሰልጣኝ ጥላሁን መንገሻን ማጣታችን የሚያሳዝን ቢሆንም  ቡድናችንን አሸናፊ ሆኖ እንዲወጣ የቻልነውን ሁሉ እናደርጋለን” የቡናው አሰልጣኝ አንዋር ያሲን   ለEBC

  • “በዚህ ዓመት በበርካታ ጨዋታዎች ያጣነው ነጥብ የሚያስቆጨን ቢሆንም ቡድናችን ልምድ ባላቸውና በወጣቶች የተሞላ በመሆኑ የነገውን ጨዋታ በማሸነፍ ወደ መሪዎቹ ለመጠጋት እንጫወታለን”።  ዳዊት እስጢፋኖስ ለኢትዮ ፉትቦል
  • “ኳስ ያለደጋፊ አያምርም ስለዚህ ደጋፊው ጨዋታውን በጥሩ ስነምግባር እንዲከታል ጥሪዬን  አቀርባሉ።” የቅዱስ ጊዮርጊስ በረኛ  ሮበርት ኦዶንኳራ  ለEBC

ታላቁ የሸገር ደርቢ  ለቡና ከውድቀት ለመነሳት ፈረሰኞቹ ደግሞ ለዋንጫ መንገዳቸውን ለማቅናት   የሚጫወቱበት እንደሚሆን እየተገለጸ ነው።
Sheger Derbi Coffee Vs St.George

ነገ ከቀኑ አስር ሰዓት ካምቦሎጆ ትንፋሽ እስኪያጥራት ድረስ በተመልካች ትሞላለች። ካምቦሎጆን የሚያጨናንቀውን የተመልካች ብዛት የሚያሰባስበው ደግሞ የ2007 ዓ.ም 19ኛ ሳምንት የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ቡናን እና ጊዮርጊስን ስለሚያገናኝ ነው። በዚያ ጨዋታ ላይ ለመታደም የሚሰባሰበው የአዲስ አበባ ከተማ እግር ኳስ አፍቃሪ ህዝብ ከቡድኖቹ አንዳች ነገር ይዞ መመለስ ይፈልጋል። የሚደግፈው ቡድን አሸናፊ ሆኖ ማየት። በዚህ ጨዋታ ዙሪያ የሁለቱም ቡድኖች አሰልጣኞችና ተጫዋቾች ከተለያዩ መገናኛ ብዙሃን በተለይም ከኢትዮጵያ ብሮድካስትንግ ኮርፖሬሽን ጋር ያደረጓቸውን ቃለ ምልልሶችና ለኢትዮ ፉትቦል ዶትኮም የሰጧቸውን ማብራሪያዎች ከዚህ በታች እናቀርባለን። 

በኢትዮጵያ ቡና በኩል 

የነገው ጨዋታ ሜዳው የኢትዮጵያ ቡና ነው። አንድ ሜዳ ለጋራ የሚጠቀሙት የአዲስ አበባ ክለቦች የራሳቸው ሜዳ የሌላቸው ቢሆንም ነገ ባለሜዳ ሆኖ የሚገባው ቡና በመሆኑ “ባለሜዳው” ብለን እንጠራዋለን። በመሆኑን የአስተያየት ሰጭዎችን ሃሳብ ቀድመን የምናቀርበውም የባለሜዳውን ይሆናል። 

የቡናው አሰልጣኝ አንዋር ያሲን ወይም ታላቁ አንዋር “በዚህ ወቅት አሰልጣኝ ጥላሁን መንገሻን ማጣታችን የሚያሳዝን ቢሆንም  ቡድናችንን አሸናፊ ሆኖ እንዲወጣ የቻልነውን ሁሉ እናደርጋለን” ብሏል። እንደ ሚካኤል በየነ እና ደረጀ ሀይሉ አይነት ተጫዋቾቹ በጉዳት የነገው ጨዋታ እንደሚያልፋቸውም ተናግሯል። የአሰልጣኙን ሃሳብ የሚጋራው አምበሉ ዳዊት እስጢፋኖስ በበኩሉ “ቡድናችን ልምድ ባላቸውና በወጣቶች የተሞላ በመሆኑ የነገውን ጨዋታ በማሸነፍ ወደ መሪዎቹ ለመጠጋት እንጫወታለን” ብሏል። ዳዊት አያይዞም ክለቡ በዚህ ዓመት በበርካታ ጨዋታዎች የጣለው ነጥብ እንደሚያስቆጨው ተናግሯል። 

በቅዱስ ጊዮርጊስ በኩል 

የመሃል ተጫዋቹ ምንተስኖት አዳነ በዛሬው እለት በሰጠው አስተያየት “ታላቁ ደርቢ ተናፋቂ ነው። በተለይ በታላቁ የሸገር ደርቢ  እኔም እንደ ተጫዋች ተሳታፊ በመሆኔ ደስታኛ ነኝ።”

የቅዱስ ጊዮርጊስን በር ሁሌም ጠንቅቆ ለመጠበቅ የማይታክተው ሮበርት ዶንካራ በበኩሉ “ኳስ ያለደጋፊ አያምርም ስለዚህ ደጋፊው ጨዋታውን በጥሩ ስነምግባር እንዲከታተለው ጥሪዬን አቀርባሉ።”  ብሏል።

ሁሌም በአዲስ አበባ እግር ኳስ ተመልካች በታላቅ ጉጉት የሚጠበቀው የነገው ጨዋታ ከአላስፈላጊ ውዝግብ  የነጻ ጥሩ ፉክክር የሚታይበት እንደሚሆን ይጠበቃል። በተለይ በተለይ ስፖርታዊ ጨዋነት በተጫዋቾችም ሆነ በተመልካች ዘንድ የሚንጸባረቅበት እንደሚሆን ተስፋ እናደርጋለን።

ኢትዮ ፉትቦል

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
ታኖ [1007 days ago.]
 ስለ ስፖርታዊ ጨዋነት ተጫዋቾች ያስተላለፉት መልእክት አሪፍ ነው። በአፍ ብቻ ሳይሆን በሜዳ ላይም ይተግበር። ብዙ ጊዜ የምናየው ከዳኛ ጋር ንትርክ አርቲፊሻል የሆነ ድክመትን ለመሸፈን የሚደረግ ማደናገሪያ የተጫዋቾች ግርግር ይደብራል ጨዋታውን ያቆረፍደዋል። ዳኛው ፊሽካና ቢጫ ላለማብዛት ቀይና ፔናሊቲ ፍጹም አግባብነት ካሌለው ላለመስጠት ወደሜዳ ከመግባቱ በፊት ለራሱ ቢጫ ካርድ ማሳየት አለበት። ደጋፊው ውስጥ ኳስ የማይገባው አሪፍ ለመባል አፉን የሚከፍት ባይጠፋም የሳንጃውም ሆነ የቡና ደጋፊ ኳስ አንከባለው ያደጉ የሸገር ያራዳ ልጆች ናቸው። ያራዳ ልጅ ደግሞ ኳስ ይወዳል። አሪፍ ኳስ ካየ ውጤቱ ምንም ይሁን ምን ይቀበላል። አፉን ዝም ብሎ አይከፍትም። ከጥሩ ጨዋታ ጋር ድል ለቡና ገበያ!!!

mebrate markos [1007 days ago.]
 sidama bunna 1-0 dedebt(13 erik murenda

mebrate markos [1006 days ago.]
 sidama bunna 2-0 dedebt(13,56, erik murenda

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!