መሪዎቹ አሁንም በጎል ክፍያ ብቻ እንደተበላለጡ ቀጥለዋል
ሚያዚያ 12, 2007

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 19ኛ ሳምንት መርሃ ግብር የሊጉ መሪዎች ቅዱስ ጊዮርጊስና ሲዳማ ቡና ተጋጣሚዎቻቸውን አሸነፉ። ሁለቱ ክለቦች ፕሪሚየር ሊጉን በተመሳሳይ ነጥብ በጎል ክፍያ ተበላልጠው የሚመሩ ሲሆን በትናንቱ ጨዋታዎቻቸውም ተጋጣሚዎቻቸውን በማሸነፋቸው ልዩነቱ እንደተጠበቀ ቀጥሏል።
St.George and Sidama Buna 19th week

ትናንት አዲስ አበባ ስታዲየም ላይ የተካሄደውን ታላቁን ሸገር ደርቢ ቅዱስ ጊዮርጊስ በብሪያንና በሀይሉ አሰፋ ሁለት ጎሎች ኢትዮጵያ ቡናን ሁለት ለባዶ ማሸነፍ ችሏል። በርካታ ተመልካች በስታዲየም ተገኝቶ የተከታተለውን ጨዋታ ፈረሰኞቹ በማሸነፋቸው ደረጃቸውን እንዳስጠበቁ እንዲቀጥሉ አስሏቸዋል። 

ከአዲስ አበባ ውጭ ከተካሄዱት ሁለት ጨዋታዎች መካከል ይርጋዓለም ላይ ሲዳማ ቡና እና ደደቢት ያካሄዱት ጨዋታ ይገኝበታል። ሁለቱ ቡድኖች ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደረጉ ሲሆን ባለሜዳዎቹ ሲዳማ ቡናዎች ከሳምንት በፊት በፈረሰኞቹ የደረሰባቸው የሁለት ለአንድ ሽንፈት በደደቢት ላይ ያወራረዱበትን ውጤት አስመዝግበዋል። ሁለቱ ቡድኖች በመጀመሪያው ዙር ጨዋታቸው አዲስ አበባ ላይ ሲዳማ ቡና ሁለት ለባዶ ማሸነፉ አይዘነጋም። 

በሌላ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ አሰላ ላይ ሙገር ሲሚንቶና በቅርቡ አሰልጣኝ ሳምሶን አየለን አሰናብቶ በምክትሉ ካሊድ መሃመድ የሚሰለጥነው ዳሽን ቢራ ያደረጉት ጨዋታ ባዶ ለባዶ ተጠናቋል። ውጤቱን ተከትሎ ዳሽን ቢራ ነጥቡን 19 በማድረስ ከወራጅነት ስጋት በመጠኑም ተንፈስ ማለት የቻለ መስሏል። 

ከትናንት በስቲያ በተካሄደ አንድ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ በቅርቡ አማካይ ተከላካዩን በመኪና አደጋ በሞት የተነጠቀው መከላከያ በአዳማ ከነማ ሁለት ለአንድ ተሸንፏል። መከላከያ በመሸነፉ ከነበረበት አምስተኛ ደረጃ ወደ ስድስተኛ ሲንሸራተት አዳማ ከነማ በበኩሉ ከስምንተኛ ደረጃ ተወርውሮ አምስተኛ ደረጃን ከመከላከያ ላይ መንጠቅ ችሏል። ሁለቱ ቡድኖች በሊጉ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታቸው በአዳማው አበበ ቢቂላ ስታዲም ተጫውተው ባዶ ለባዶ ተለያይተው ነበር። 

ፕሪሚር ሊጉን ፈረሰኞቹ 38 ነጥብ በመያዝ ከተጨማሪ 15 ጎሎች ጋር የደረጃውን መሪነት ሲቆናጠጡት ሲዳማ ቡና ደግሞ በተመሳሳይ ነጥብ በዘጠኝ ንጹህ የጎል ክፍያ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል። 32 ነጥብ እና 11 ተጨማሪ የጎል ክፍያ ያለው ንግድ ባንክ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ወልድያ ከነማ እና ሀዋሳ ከነማ 14ኛ እና 13ኛ ደረጃን ይዘዋል። ሊጉ ነገም ቀጥሎ ሶዶ ላይ በደቡብ ደርቢ ወላይታ ድቻ ከሀዋሳ ከነማ ሲጫወቱ አዲስ አበባ ላይ የግርጌው ደርቢ በኤሌክትሪክና ወልድያ ከነማ መካከል ይካሄዳል። 

ካሳ ሀይሉ 
ኢትዮ ፉትቦል

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
t [1035 days ago.]
 ene yayenewu betame sidama bunna nna kedusi goriges mefokakeru turuno gine yami hono yihe sidama bunna andegn wode bota yemetalech beye amenalehu melikame chawota .

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!