በአሰቃቂው የዜጎች ሞት ክለቦች ሃዘናቸውን ገለጹ
ሚያዚያ 16, 2007

በቅርቡ በየመን፣ በደቡብ አፍሪካ እና በሊቢያ ኢትዮጵያውያን ወንድሞቻችንና እህቶቻችን በአሰቃቂ ሁኔታ ለሞት መዳረጋቸ ይታወሳል። በተለይ በሊቢያ አይ ኤስ የተባለው አሸባሪ ቡድንና በደቡብ አፍሪካ ዙሉ ግዛት በዜጎቻችን ላይ ያደረሱት አሰቃቂ ግድያዎች መላ ኢትዮጵያውያንን ያሳዘነና እምባ ያራጨ ክስተት ነው። በኢትዮጵያውያኑ ላይ በደረሰው አደጋ ሁሉም ኢትዮጵያውያን በአንድ ልብ ሀዘናቸውን የገለጹትን ያህል በርካታ ድርጅቶችም በክስተቱ የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን እየገለጹ ይገኛሉ። 

St.George and Ethiopian Coffee Condolence Message


ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለቦች ሃዘናቸውን ከገለጹ ተቋማት መካከል ይገኙበታል። የቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ በድረገጹ “በዜጎቻችን ሞት ክለባችን ጥልቅ ሃዘን ተሰምቶታል። ምንጊዜም በልባችን ውስጥ እየታወሱ ይኖራሉ” ሲል አስነብቧል። ኢትዮጵያ ቡና እግር ኳስ ክለብ በበኩሉ “በዜጎቻችን አሰቃቂ የሞት አደጋ ክለባችን ጥልቅ ሃዘን ተሰምቶታል” ብሏል። ሁለቱም ክለቦች ለመላው ኢትዮጵያውያንና ለሟቾች ቤተሰቦች መጽናናትን ተመኝተዋል። 

ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በሊቢያ አይ ኤስ ያደረሰውን አሰቃቂ ግድያ “ፍጹም ሰብአዊነት የጎደለው” ሲል ያወገዘ ሲሆን በደረሰው አደጋም ጥልቅ ሃዘን እንደተሰማው ገልጿል። ፌዴሬሽኑ በቀጣዩ ሳምንት የሚካሄዱ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ሟች ወገኖቻችንን በህሊና ጾለት አስበው እንደሚጀመሩ አስታውቀል።የኢትዮ ፉትቦል ባልደረቦች በዜጎቻችን ላይ በደረሰው አሰቃቂ ግድያና መፈናቀል የተሰማንን ጥልቅ ሃዘን አሁንም በድጋሚ እየገለጽን የድረ ገጻችንን ዋና መግቢያ ገጽ ለ7 ቀናት  እስከ መጪው ሰኞ ድረስ  እይታው በጥቁር ስክሪን እንዲደበዝዝ ማድረጋችንን እንቀጥላለን። ለመላው ኢትዮጵያውያን በተለይ ሀዘኑና ጉዳቱ ለደረሰባቸው ወገኖቻችን ቤተሰቦች እግዚአብሄር መጽናናትን እንዲሰጥልን እንመኛለን ።


ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!