ቅዱስ ጊዮርጊስ ለዋናው ቡድን አዲስ ሆላንዳዊ አሰልጣኝ ቀጠረ
ሚያዚያ 16, 2007

ዛሬ የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ እንዳስታወቀው ለዋናው ቡድን ዋና አሰልጣኝ እንዲሆኑለት ሆላንዳዊውን አሰልጣኝ ማርቲን ኩፕማንን አሰልጣኝ አድርጎ መቅጠሩን አስታውቋል፡፡


ከህዝብ ግንኙነት ክፍሉ የደረሰንን ሙሉ ዜና እንደሚከተለው አቅርበናል።


ቅዱስ ጊዮርጊስ ሆላንዳዊውን አሰልጣኝ ማርቲን ኩፕማንን አሰልጣኝ አድርጎ ቀጠረ
The Signing Cermony

ቅዱስ ጊዮርጊስ በቀጣይ አመት ለሚጠብቁት የአህጉራዊ እና የውስጥ ውድድሮች ዋናውን ቡድን በአሰልጣኝነት እንዲመሩለት ሆላንዳዊው
አሰልጣኝ ማርቲን ኩፕማንን
አሰልጣኝ አድርጎ ቀጥሯል፡፡ በዚህም መሰረት ሆላንዳዊው አሰልጣኝ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ጋር የሁለት አመት የኮንትራት ስምምነት በዛሬው እለት የተፈራረሙ ሲሆን በመጪው ሀምሌ ወር ላይም ቡድናችን ቅዱስ ጊዮርጊስን በማሰልጠን ስራቸውን የሚጀምሩ ይሆናል፡፡

ማርቲን ኩፕማን የተወለዱት እ.ኤ.አ. በ1956 ጉልደርስ በተባለችው የሆላንድ ግዛት ውስጥ ሲሆን የተጨዋችነት ዘመናቸውንም በጎ ኤሄድ ኤግልስ፤ኤፍ ሲ ቲዌንቴ እና ኤስ ሲ ካምበር ተጫውተው አሳልፈዋል፡፡
Signing Cermony

ቅዱስ ጊዮርጊስ በቀሪው የውድድር ዘመን የሚቀሩትን የፕሪምየር ሊግ እና የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች በፋሲል ተካልኝ እየተመራ የሚጨርስ ሲሆን ኩፕመንም በመጪው ሀምሌ ወር ላይ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት የቅዱስ ጊዮርጊስ አሰልጣኝነት መንበርን የሚረከቡ ይሆናል፡፡

አሰልጣኝ ኩፕማን በአሰልጣኝነት ዘመናቸው በሀገራቸው እና በተለያዩ የውጭ ሀገራት ተዘዋውረው የሰሩ ሲሆን በተለይም በአፍሪካ የኮንጎውን ታላቅ ክለብ ኤኤስ ቪታ ክለብን ጭምር አሰልጥነዋል፡፡

የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ሆላንዳዊው ሬኒ ሂድኒክንም ደብረዘይት እየተገነባ ለሚገኘው የይድነቃቸው ተሰማ አካዳሚ ዳይሬክተር አድርጎ መቅጠሩ የሚታወስ ነው፡፡

የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ለአሰልጣኝ ማርቲን ኩፕማን መልካም የስራ ዘመን ይመኝላቸዋል፡፡

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!