ሰበር ዜና: የኢት.እግ.ኳስ.ፌዴ ቴክኒክ ኮሚቴ ነገ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ምርጫውን ያሳውቃል።
ሚያዚያ 16, 2007

ዛሬ ማምሻውን  ከሰላሳ ደቂቃ በፊት በተጠናቀቀው የኢት.እግ.ኳስ.ፌዴ ቴክኒክ ኮሚቴና ጊዜያዊ ኮሚቴው በጋራ ባደረጉት ስብሰባ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድንን  እንዲያሰለጥኑ   ከዚህ ቀደም ቀርበው ከነበሩ የሀገር ውስጥ እጩ ተወዳዳሪ አሰልጣኞች በተጨማሪ   ሌሎች እጩዎችን  አካቶ የአሰልጣኝ ምርጫ ግምገማውን ሲያኪያሂድ አምሽቶ  የመጨረሻዎቹን  አራት  አሰልጣኞች መርጦ የዛሬ ስብሰባውን ጨርሶ ተበትኗል። 
The Walias

በዚሁም መሰረት አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ፣ ፋሲል ተካልኝ ፣ ጸጋዬ ኪዳነማርያም እንዲሁም ዮሃንስ ሳህሌ ለመጨረሻው ምርጫ ማለፋቸው ታውቋል። የቴክኒክ ኮሚቴው ነገ በሚያደርገው ቀጣይ ስብሰባ ከአራቱ እጩ አሰልጣኞች አንዱን የአሰልጣኝነት ቦታውን እንዲረከብ ለፌዴሬሽኑ ምርጫውን ያሳውቃል ተብሎ ይጠበቃል።   ከቀረቡት እጩዎች መሃል በአሁኑ ሰአት ደደቢትን እያሰለጠኑ የሚገኙት አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ በምርጫው የተሻለ እድል እንደሚኖራቸው ከፍተኛ ግምት አለ።


ፈለቀ ደምሴ
ኢትዮ ፉትቦል

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
Esayas [1001 days ago.]
 Sewnit bishaw yetal isu nebr mehon yenbrbet.......respact to sewint

መንግስቱ ከጂንካ [74 days ago.]
 ማንም ይመረጥ ግን በአፈፃፀም አስደስቱ!

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!