ኢንስትራክተር ዮሃንስ ሳህሌ ከፌዴሬሽኑ ጋር መስማማቱን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ
ሚያዚያ 20, 2007

አሰልጣኝ ማሪያኖ ባሬቶን ከዋልያዎቹ አሰልጣኝነታቸው ያሰናበተው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በምትካቸው የደደቢት እግር ኳስ ክለብ አሰልጣኝ የነበሩትን ኢንስትራክተር ዮሃንስ ሳህሌን መቅጠሩን ኢትዮፉትቦል ዶትኮም ቀደም ብሎ መዘገቡ ይታወሳል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለዝግጅት ክፍላችን በላከው መረጃ እንዳስታወቀው ኢንስትራክተር ዮሃንስ ሣህሌ ለቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት የዋልያዎቹ ዋና አሰልጣኝ ሆኖ መቀጠሩን አስታውቋል። 

እንደ ኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የህዝብ ግንኙነት ክፍል መረጃ አሰልጣኝ ዮሃንስ ሣህሌ በቀጣዩ ዓመት ለሚካሄደው አራተኛው “የቻን” ዋንጫ እና በ2017 ለሚካሄደው 31ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ብሔራዊ ቡድኑን ተሳታፊ የማድረግ ሀላፊነት እንደተጣለበት አስታውቋል። በአሰልጣኙ ቅጥርና የተሰጠውን ሀላፊነት በተመለከተ በቀጣዮቹ ቀናት ተጨማሪ መረጃዎችን ይዘን እንቀርባለን። 

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለአራተኛው የቻን ዋንጫ ለማለፍ ከኬኒያ ብሔራዊ ቡድን ጋር ሲደለደል ጋቦን ለምታስተናግደው ለ31ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ ደግሞ በምድብ አስር ከአልጄሪያ፣ ሲሼልስና ሌሴቶ ጋር መደልደሏ ይታወቃል። 

ካሳ ሀይሉ
ኢትዮ ፉትቦል 


ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!