ኢትዮጵያ ቡና የጎዳና ሩጫ ሊያካሂድ ነው
ሚያዚያ 21, 2007

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ለቡ አካባቢ የተጫዋቾች መኖሪያ ካምፕ ግንባታ እያካሄደ ያለው ኢትዮጵያ ቡና እግር ኳስ ክለብ ለካምፑ ግንበታ የገቢ ማሰባሰቢያ የጎዳና ላይ ሩጫ የፊታችን እሁድ እንደሚያካሂድ ገለጸ። ሩጫው ስምንት ኪሎ ሜትር እንደሚሸፍንና የመሮጫ ቲሸርቱ ዋጋም 150 ብር እንደሚሸጥ የክለቡ ማርኬቲንግ ክፍል ሀላፊ አቶ ኢሳያስ ታፈሰ ለኢትዮፉትቦል ዶትኮም ተናግረዋል። አቶ ኢሳያስ አያይዘውም በሩጫ ውድድሩ ክለቡ ከሁለት ነጥብ አምስት ሚሊዮን ብር ያላነሰ ገንዘብ ለመሰብሰብ ማቀዱን ተናግረዋል። 
Buna Annual Family Race


ሜዳ ላይ ነጥብ መሰብሰብ የተሳነው ኢትዮጵያ ቡና ከሜዳ ውጭ ይህንን ያህል ገንዘብ በአንድ የሩጫ ውድድር ለማግኘት ማቀዱ ደጋፊዎቹ ላይ ያለውን እምነት ያሳያል ተብሏል። ለካምፑ ግንባታ ከስምንት ሚሊዮን ብር በላይ እንደሚያስፈልግ የታወቀ ሲሆን ግንበታው ከተጀመረ ሁለተኛ ዓመቱ ላይ ሲገኝ እስካሁን ባለው ሂደት ከቀጠለ አንድ ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ሊጠናቀቅ እንደሚችል ይጠበቃል። 

የፊታችን እሁድ በሚካሄደው የጎዳና ላይ ሩጫ ከስምንት ሺህ ተሳታፊ በላይ እንደሚገኝ አቶ ኢሳያስ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ቡና አሁን እየተጠቀመበት ያለው የተጫዋቾች መኖሪያ ካምፕ ከግለሰብ በወር 18 ሺህ ብር የተከራየው መሆኑ ይታወቃል። በካምፑ ግንባታና በጎዳና ሩጫው ዙሪያ ተጨማሪ መረጃዎችን ይዘን እንመጣለን።  


ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!