የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አንድ ተስተካካይ ጨዋታ ዛሬ ይካሄዳል
ሚያዚያ 21, 2007

በቀድሞው የመከላከያ የመሃል ሜዳ ተጫዋች ተክለወልድ ፈቃዱ ድንገተኛ ህልፈተ ህይዎት ምክንያት ለሌላ ጊዜ ተላልፎ የነበረው የደደቢትና የመከላከያ ጨዋታ ዛሬ ይካሄዳል። የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ የሚካሄደው ከቀኑ አስር ሰዓት መሆኑን ፌዴሬሽኑ ያደረሰን መረጃ ያመለክታል። 
Dedebit Vs Defence

አሰልጣኛቸውን ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሳልፈው የሰጡት ደደቢቶች ያለፉትን ጨዋታዎች በድል ማጠናነቀቅ የቻሉ ሲሆን መከላከያዎች በበኩላቸው በተከታታይ ጨዋታዎች ሽንፈት አስተናግደዋል። ደደቢት ባለፈው ቅዳሜ ኢትዮጵያ ቡናን ሶስት ለባዶ ሲያሸንፍ መከላከያ ደግሞ በሀዋሳ ከነማ ሁለት ለአንድ ተሸንፎ እንደነበር አይዘነጋም። 

መከላከያ በ19 ጨዋታ 26 ነጥብ ሲይዝ ደደቢት በ28 ነጥብ 6ተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ መሸናነፍ ከታየበት የደረጃ ለውጥ ያስከትላል።  


ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!