አዳማ ከነማ ኢትዮጵያ ቡናን በማሸነፍ በጥንካሬው ቀጥሏል
መጋቢት 24, 2015

. የንግድ ባንክና የደደቢት ጨዋታም ይጠበቃል 

ትናንት ተካሂዶ በነበረው አንድ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና አሁንም ለተከታታይ አራተኛ ጊዜ በአዳማ ከነማ አንድ ለባዶ ተሸንፏል። ቡና በተከታታይ አራት ጊዜ ከመሸነፉም በላይ በአምስት ተከታታይ ጨዋታ ጎል ማስቆጠር ሳይችል ቀረቷል። 

Ethiopian Coffee lost 1nil to Adama City

በርካታ ተጫዋቸቹን በጉዳት ማሰለፍ ያልቻለው ኢትዮጵያ ቡና በተጋጣሚው ሙሉ ለሙሉ የጨዋታ ብልጫ የተወሰደበት ሲሆን የጎል ሙከራ በማድረግም አዳማ ከነማዎች የተሻሉ ሆነው አምሽተዋል። አልፎ አልፎ ብልጭ ድርግም የሚሉ የጎል ማባት ሙከራዎችን ማድረግ ቢችሉም አጥቂዎቹ ወደ ፍሬ መቀየር ባለመቻላቸው ክለቡ ለተከታታይ አምስተኛ ጊዜ ኳስና መረብ ማገናኘት ሳይችል ቀርቷል። 

ከአህመድ ረሽድ፣ ጋቶች ፓኖምና መስዑድ መሃመድ ውጭ ያሉት ተሰላፊዎች በእለቱ ጥሩ ሆነው ያልታዩ ሲሆን በተለይ ጎል ጠባቂው ጌቱ ተስፋዬ፣ መሀመድ ጀማል፣ ሳሙኤል ወንድሙ እና ዮናስ ገረመው አይነት ተጫዋቾች ለምን እንደተሰለፉ እንኳ የገባቸው አይመስልም ማለት ይቻላል። በዚህም በስታዲየም ተገኝተው የነበሩ በርካታ ደጋፊዎች በቡድናቸው ላይ ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ ታይተዋል። ለወጣቱ ተከላካይ አህመድ ረሽድ ደጋፊዎች አድናቆታቸውን ሲቸሩት ታይተዋል። 

ድሉን ተከትሎ አዳማ ከነማ የነጥብ ድምሩን 34 በማድረስ ከስድስት ተጨማሪ የጎል ክፍያ ጋር ሶስተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ኢትዮጵያ ቡና ደግሞ 28 ነጥብ ይዞ በባዶ የጎል ክፍያ ሰባተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። የዘንድሮው የቡና ውጤት ባለፈው ዓመት በተመሳሳይ ወቅት አስመዝግቦት ከነበረው ጋር ሲነጻጸር በእጅጉ ዝቅተኛ ሲሆን በዚህ ዓመት ማግኘት ከነበረበት 63 ነጥብ ከግማሽ በታች 28 ብቻ ማግኘቱ ደጋፊወችን በእጅጉ ያሳዘነ መሆኑን ለኢትዮፉትቦል ዶትኮም አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። 

ፕሪሚየር ሊጉ ዛሬም ቀጥሎ ሲውል አዲስ አበባ ላይ ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ከአርባምንጭ ከነማ ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶታል። ሁለቱ ቡድኖች በዓመቱ የመጀመሪያ ግንኙነታቸው አርባ ምንጭ ላይ አንድ እኩል መለያየታቸው የሚታወስ ሲሆን በዚያ ጨዋታ ዮርዳኖስ አባይ ለኤሌክትሪክ የአቻነቷን ግብ ማስቆጠሩ ይታወሳል። ኤሌክትሪክ በ21 ነጥብ 11ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ አርባምንጭ ከነማ ደግሞ በ29 ነጥብ ስድስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ካሳ ሀይሉ
ለኢትዮ ፉትቦል

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!