ዳዊት እስጢፋኖስ እና ኢትዮጵያ ቡና ሊለያዩ ነው
ሚያዚያ 30, 2007

ለሁለት ዓመታት ኢትዮጵያ ቡናን በአምበልነት መምራት የቻለው ዳዊት እሲጢፋኖስ ከክለቡ ጋር ሊለያይ መሆኑን ከክለቡ ያገኘነው መረጃ አመለከተ። ለክለቡ ቅርበት ያላቸው የኢትዮፉትቦል ዶትኮም ምንጮች እንደገለጹት ኢትዮጵያ ቡና ዳዊት እስጢፋኖስን ከክለቡ ሙሉ በሙሉ ሊያግደው መወሰኑ ተሰምቷል። መረጃውን ለዝግጅት ክፍላችን ያደረሱን የኢትዮፉትቦል ዶትኮም ምንጮች እንደገለጹት ክለቡ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው ተጫዋቹ በተጀመረው የውድድር ዓመት እያሳየ ያለው አቋም ጥሩ አለመሆንና በስነ ምግባር ጉድለት ምክንያት ነው።
Dawit Estifanos

ክለቡ ከዳሽን ቢራ ጋር በነበረው ጨዋታ ተጫዋቹ ተቀይሮ እንዲወጣ ሲጠየቅ ካሳየው የስፖርታዊ ጨዋነት ውጭ የሆነ ድርጊት ጀምሮ በተለያየ ጊዜ የክለቡን ሰላም እሰከማወክና በልምምድ ሜዳም እስካለመገኘት የደረሰ ድርጊት ፈጽሟል ሲል የክለቡ መረጃ ገልጿል። በዚህም ምክንያት ሌሎች ተጫዋቾችን ሊያስተምር በሚችልና ክለቡን ሊጠቅም በሚችል መልኩ ቅጣት መወሰኑን ያስታወቀው ክለቡ “ተጫዋቹን በዘላቂነት ከክለቡ ለመለየትም እንገደዳለን” ሲል አስታውቋል።

ዳዊት እሰጢፋኖስ ኢትዮጵያ ቡናን ከመቀላቀሉ በፊት በመብራት ሀይል እና ደደቢት ክለቦች ማሳለፉ ይታወሳል። በጉዳዩ ዙሪያ መልስ እንዲሰጠን ለዳዊት እስጢፋኖስ ያደረግነው የስልክ ሙከራ ሊሳካልን አልቻለም።

ካሳ ሀይሉ
ለኢትዮ ፉትቦል

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
Mule [987 days ago.]
 Mote biketta yansewalle yehe arekeyamme tejjame balege sede zergna techawache.

mike21 [987 days ago.]
 @Mule ante erasehe tejame negre nehe Davo setele norehe gena legena tebarere belehe afhene tekeftebetalhe. weleta bise.

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!