በተለያየ መንገድ እየሄዱ ያሉት አዳማ ከነማ እና ኢትዮጵያ ቡና
ግንቦት 04, 2007

ሁለቱም በርካታ ደጋፊ ያለቸው ክለቦች ናቸው።የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ ሲካሄድ እጅግ በርካታ ህዝብ በስታዲየም ተገኝቶ የሚመለከታቸው ክለቦች ናቸው። በተለይም ቡና በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ያነሳውን የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ ሲያነሳ የቡድኑ አሰልጣኝ የነበረው ውበቱ አባተ ትውልድና እድገቱ አዳማ ከተማ መሆኑ የቡናዎችንና የአዳማዎችን ቁርኝት ያጠናክረዋል። ይህ ሁሉ ግጥምጥሞሽ ያለው የሁለቱ ክለቦች ግንኙነት በዚህ ዓመት ግን በሜዳ ላይ ውጤት የተቃራኒ አቅጣጫ ተጓዦች አድርጓቸዋል። ቡናዎች ወደ ታች አዳማዎች ወደ ላይ።
Adama vs Coffee

ሁለቱ ክለቦች በዚህ ዓመት ለመጀመሪያ ጊዜ የተገናኙት በፕሪሚየር ሊጉ ሰባተኛ ሳምንት ሲሆን በውጤቱም ሶስት እኩል ተለያይተዋል። በዚያ ጨዋታ የአዳማው አበበ ቢቂላ ስታዲየም መተንፈሻ እስኪያጥረው በሁለቱ ቡድን ደጋፊዎች የተሞላ ሲሆን የሁለቱ ክለብ ግብ ጠባቂዎችም በቃኝ እስኪሉ ድረስ በጎል የተንበሸበሹበት ጨዋታ ነበር። በቡና በኩል ቢኒያም አሰፋና አስቻለው ግርማ በአዳማ በኩል ደግሞ በረከት አዲሱ እና ታከለ አለማየሁ ነግሰው የታዩበት እለትም ነበር። በተለይ ታከለ ዓለማየሁ ተጎድቶ እስከወጣበት ደቂቃ ድረስ የእለቱ ልዩነት ፈጣሪ ሆኖ ነበር የዋለው።

ከዚያ ጨዋታ በኋላ በድጋሚ የተገናኙት በሊጉ 20ኛ ሳምንት መርሃ ግብር አዲስ አበባ ስታዲየም ላይ ነበር። የአዲስ አበባው ጨዋታ ግን እንደ አዳማው የበርካታ ደጋፊዎችን ትኩረት እና ቀልብ ማሳብ እለቻለም። ለዚህ ደግሞ ብቸኛውና ትልቁ ምክንያት የኢትዮጵያ ቡና ውጤት ደጋፊዎቹን ስላላስደሰተ ነው።በቅርቡ ከዳሽን ቢራ ወደ አዳማ ከነማ የተዘዋወረውና የጎሉን መስመር ፈልጎ ለማግኘት ያልተቸገረው ዮናታን ከበደ የእለቱን ብቸኛ ጎል አስቆጥሮ አዳማ ከነማን አሸናፊ ማድረግ እንደቻለ ይታወሳል። ከዚህ ጨዋታ ቀደም ብሎ እና ከዚያ በዲህ ባሉት ተከታታይ ጨዋታዎች ሁለቱ ክለቦች ፍጹም በተቃራኒ መስመር እየተጓዙ ይገኛሉ።

አዳማ ከነማ በተከታታይ ካደረጋቸው አምስት ጨዋታዎች ሙሉ ሶስት ነጥብ በማግኘት 15 ነጥቦችን ሲሰበስብ በአንጻሩ ኢትዮጵያ ቡና በአምስት ተከታታይ ጨዋታዎች በመሸነፍ በሊጉ መጥፎ ሪከርድ አስመዝግቧል። አዳማ በተከታታይ ስድስት ጨዋታዎች ጎል ሲያስቆጥር ቡና በበኩሉ በስድስት ጨዋታዎች አንድም ጎል ማስቆጠር አልቻለም። አዳማ ከነማ በሜዳው ካደረጋቸው 13 ጨዋታዎች አንድም ጊዜ ያልተሸነፈ ብቸኛ የሊጉ ክለብ ሲሆን ቡና ግን በተከታታይ ሶስት ጨዋታዎችን በአዲስ አበባ ስታዲየም በመሸነፍ ተስተካካይ አላገኘም። የተጠቀሱት ነጥቦች የቡናንና የአዳማን የጉዞ አቅጣጫ የሚያሳዩ ናቸው። በሁለት ተቃራኒ አቅጣጫ እየተጓዙ ያሉ ክለቦች።&


ይርጋ አበበ
ለኢትዮ ፉትቦል

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
ሁመር [561 days ago.]
  ጤ

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!