ኢንተርናሽናል አልቢትር ሊዲያ ታፈሰ የፊፋን ፈተና በብቃት አለፈች
ግንቦት 11, 2007

ከአንድ ወር በኋላ በሰሜን አሜሪካዊቷ ካናዳ በሚካሄደው የሴቶች ዓለም ዋንጫ ላይ ውድድሮችን የመምራት እድል ከተሰጣቸው ዳኞች አንዷ ኢትዮጵያዊቷ ሊዲያ ታፈሰ መሆኗ ተረጋገጠ። ቀደም ሲል አልቢትሯ የአካል ብቃት ፈተናውን ማለፍ እንዳልቻለች በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ሲዘገብ የቆየ ቢሆንም ኢትዮፉትቦል ዶትኮም ግን ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው አካላት ባገኘው መረጃ ኢንተርናሽናል ዳኛ ሊዲያ ታፈሰ ግንቦት 11/2007 ዓ.ም የፊፋ ባለሙያዎች ፈተና ሊሰጧት እንደሆነ መዘገባችን ይታወሳል።
Lidia Tafesse

 ዛሬ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የህዝብ ግንኙነት ክፍል በደረሰን መረጃ መሰረት ኢንተርናሽናል ዳኛ ሊዲያ ታፈሰ ውድድሩን ለመምራት የሚያስችላትን ፈተና በብቃት ማለፍ ችላለች። የፌዴሬሽኑ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ወንድምኩን አላዩ በስልክ እንደገለጹልን “ሊዲያ ፈተናውን በብቃት ማለፍ ችላለች። በዚህም መሰረት ከአንድ ወር በኋላ ካናዳ ላይ የሚካሄደውን የሴቶች ዓለም ዋንጫ የመዳኘት እድል ከተሰጣቸው ከአንድ እጅ እጣት በታች የሆኑ የአህጉሪቱ ዳኞች አንዷ ኢትዮጵያዊቷ ሊዲያ ታፈሰ ትሆናለች ማለት ነው።

በዚህ አጋጣሚ ዝግጅት ክፍላችን ኢንተርናሽናል ዳኛ ሊዲያ ታፈሰ የፊፋን ፈተና በብቃት በማለፏ የተሰማንን ደስታ እየገለጽን በውድድሩ መልካም ጊዜ እንድታሳልፍ መልካም ምኞታችንን እንገልጻለን።

ፈለቀ ደምሴ
ለኢትዮ ፉትቦል

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
Fikere21 [955 days ago.]
 Lydia Tafese 4th official col. vs mex 0:0 34min

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!