አሸናፊዎቹ እና የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ
ግንቦት 17, 2007

ኢትዮፉትቦል ዶት ኮም የ2007 ዓ.ም.  የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሂደት እና ከ1990 ዓ.ም.  ጀምሮ  የሊጉን ዋንጫ ያነሱ ክለቦችን የሚዳስስ ዘገባና ምልከታ ለእግር ኳስ አፍቃሪው ለማድረስ ሁለት ጨዋታ እየቀራቸው የ2007  ዓ.ም. አሸናፊ የሆኑትን የቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ የተወሰኑ አመራሮች እና ተጫዋቾችን በማነጋገር ጀምሯል። ቃለ መጠይቁን ለማድረግ ለተባበሩን የክለቡ አባላት በሙሉ በኢትዮፉትቦል እንዲሁም በአንባቢያን ስም እናመስግናለን።                               

ክፍል አንድ

በፈለቀ ደምሴ እና ይርጋ አበበ

ጊዜው እንደ ኢትዮጵያውያን የዘመን አቆጣጠር 1928 ዓ.ም ነበር የአራዳ ሰፈር ልጆች አየለ አትናሼ ፤ተስፋዬ አበጋዝ፤ ጆርጅ ዱካስ፤ተስፋዬ አክሎግ፤ አፈወርቅ ገ/መስቀል ተስፋዬ መምሬ፤እና  ሌሎችም እድሜአቸው ከ11 እስከ 13 የሚደርሱ ህፃናት ተሰባስበው የመሰረቱትና የመጀመሪያ ግጥሚያቸውን ከማድረጋቸው በፊት በጎደለባቸው ልጅ ምክኒያት ወደ ቡድኑ የተቀላቀሉት እና ከሀገራቸው አልፈው ለአፍሪካ ኩራት የሆኑትን አቶ ይድነቃቸው ተሰማን በማካተት የተመሰረተው ቅድስ ጊዮርጊስ ክለብ   የአራዳዎቹ አራዳ ታዳጊዎች  ተሰባስበው በሰፈራቸው መጠሪያ ቡድናቸውን ቅዱስ ጊዮርጊስ በማለት የፈጠሩት ቡድን የአርመን ኮሚኒቲ አራራት ቡድን ጋር በመግጠም 2ለ0 በማሸነፍ በወቅቱ የነበረውን ተመልካች በማስደመም ጀመረ።

ይህ ከሆነ እነሆ ዘንድሮ 79 ዓመታትን ተሻግሮ 80ኛ ዓመቱን ሊደፍን ከአንድ እጅ ጣት ያልዘለለ ወራት ብቻ ቀርተውታል። የቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ እና እግር ኳስ ጨዋታ የአብሮነት ማስተሳሰሪያ አንድነት ውል ከወራት በኋላ 80 ዓመት ይደፍናል። ክለቡ 80ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ለማክበር እየተዘጋጀ ባለበት በዚህ ወቅት ደግሞ  14 ክለቦች ለአንድ ዋንጫ በሚፋለሙበት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ገና ሁለቱን ክለቦች ሳያገኙ የዋንጫውን ማረፊያ በቅሎ ቤት አካባቢ ከሚገኘው የፈረሰኞቹ ጽ/ቤት እንዲሆን አድርገውታል። ይህም ለክለቡ የምስረታ በዓል ልዩ ማድመቂያ እንደሆነ የክለቡ አሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታን ጨምሮ በርካታ የክለቡ ደጋፊዎችና የክለቡ ቤተሰቦች ይስማሙበታል። ኢትዮፉትቦል ዶትኮም የክለቡን  የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ ማንሳት አስመልከቶ ቦሌ አካባቢ በሚገኘው የክለቡ መለማመጃ ሜዳ ተገኝቶ ከአሰልጣኞች፣ከተጫዋቾች፣ ከቡድን መሪዎች እና ከደጋፊዎች ጋር ቆይታ አድርጎ ተመልሷል። የቃለ ምልልሳችንን ሙሉ ቃል ከዛሬ ጀምሮ በተከታታይ ለሶስት ቀናት ይዘን የምንቀርብ ይሆናል። 

ፋሲል ተካልኝ
Fasil Tarekegne

በ1990 ዓ.ም በጊዜው ስያሜው “የኢትዮጵያ አንደኛ ዲቪዝዮን ወይም በአሁኑ አጠራሩ ብሔራዊ ሊግ ሲወዳደርየከረመውና በመጨረሻም የዋንጫው ባለቤት በመሆን ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ያደገው ቅዱስ ጊዮርጊስ ከዋንጫው በተጨማሪ ሶስት የቡድኑ አባላትን ኮከብ አድርጎ አስመርጦ ነበር። በጊዜው ቡድኑን ያሰለጥን የነበረው አሰልጣኝ አስራት ኃይሌ ኮከብ አሰልጣኝ፣ 20 ጎሎችን ያስቆጠረው ስንታየሁ ጌታቸው ወይም ቆጬ ኮከብ ጎል አግቢ ሲሆኑ የወቅቱ የቡድኑ አማካይ መስመር ተጫዋች ፋሲል ተካልኝ ደግሞ ኮከብ ተጫዋች በመሆን ተመርጠው ነበር። ከተጫዋች ገብረመድህን ኃይሌን ከአሰልጣኝ ደግሞ አስራት ኃይሌን እንደሚያደንቅ የሚናገረው ፋሲል ተካልኝ በዚህ ዓመት ያስመዘገቡትን ስኬት አስመልክቶ የሰጠንን አስተያየት ከዚህ በታች አቅርበነዋል።

ቅዱስ ጊዮርጊስ ከዚያ ጊዜ በኋላ በፕሪሚየር ሊጉ በቆየባቸው 17 የውድድር ዓመታት 12 ጊዜ የሊጉን ዋንጫ ያነሳ ሲሆን በእነዚህ 12 የድል ዓመታት ውስጥ ደግሞ የቀድሞው ኮከብ ተጫዋች የአሁኑ የክለቡ ጊዜያዊ ዋና አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ አብሮ አለ። በተጫዋችነትና በምክል አሰልጣኝነት ዘመን የሊጉን ዋንጫ ማንሳት የቻለው ወጣቱ አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ ዘንድሮ ታላቁን ክለብ በተጠባባቂ ዋና አሰልጣኝነት ከዘሪሁን ሸንገታ ጋር እየመራ የዋንጫው ባለቤት ሆኗል። አሰልጣኝ ሆኖ ዋንጫ ማንሳት ያለው ተጽእኖ ከዚህ በፊት በተጫዋችነትና በምክትል አሰልጣኝነት የሊጉን ዋንጫ ደጋግሞ እንዳነሳ የሚናገረው አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ የዘንድሮው ዋንጫ ከሌሎች ጊዜያት ድሎች የተለየ እንደሆነ ይናገራል። ለዚህም የሚያቀርበው ምክንያት በዚህ ዓመት የተገኘው ድል እሱ እና ባልደረባው ዘሪሁን ሸንገታ ዋና አሰልጣኝ ሆነው እየሰሩ በመሆኑ ይህም ጫናዎች በይበልጥ በእነሱ ላይ ያረፈ በመሆኑ እንደሆነ ነው የሚናገረው። አጀማመሩ ጥሩ ያልነበረው ቅዱስ ጊዮርጊስ በሁለተኛው ዙር የሊጉ መርሃ ግብር በተከታታይ በማሸነፍ የዋንጫውን ጆሮ መጨበጥ ችሏል። ለዚህ ስኬቱ ያበቃው ደግሞ “ጠንካራ ስራ በመስራታችን ነው” ይላል ወጣቱ አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ። 

ብራዚላዊው አሰልጣኝ ዶ ሳንቶስ ከተሰናበቱ በኋላ ሁለቱ ወጣት አሰልጣኞች ቡድኑን መረከባቸው ይታወሳል። በዚህ ጊዜ ክለቡ ጠንካራ ተፎካካሪ እንዲሆንና ለዋንጫ እንዲበቃ የረዳቸው ምንድን ነው? ለሚለው ጥያቄ ሲመልስ

“ከዶ ሳንቶስ ስንብት በኋላ ያደረግናቸው ሁለት ተከታታይ ጨዋታዎች ላይ ያስመዘገብናቸው ስድስት ነጥቦች በቡድናችን ላይ የራስ መተማመን ሰጥቶናል ብዬ አምናለሁ። ከዚያ በኋላ ደግሞ ትኩረት አድርገን እንሰራ የነበረው በድክመቶቻችን ላይ ነበር ይህ ነው ለውጤት ያበቃን” ብሏል።

ስለ ኢንተርናሽናል ውድድር

በዚህ ዓመት ክለቡ በአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ ገና በመጀመሪያው ዙር በአልጄሪያው ኦልማን መሰናበቱ ይታወሳል። ነገር ግን በዚያ ጨዋታ ላይ የተመዘገበው ውጤት በሁለት መልኩ መታየት እንዳለበት ሲናገር “በመጀመሪያው ጨዋታ በጨዋታ ተበልጠን ተሸንፈናል። በመልሱ ባህር ዳር ላይ ያደረግነውን ጨዋታ ግን ከፍጹም የጨዋታ ብልጫ ጋር ማሸነፍ ችለን ነበር። ነገር ግን ከሜዳ ውጭ ባገባ በሚል ህግ ነው የወደቅነው” ይላል። ከዚህ በተጨማሪም ኦልማን ፈረሰኞቹን አሸንፎ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፍ የቻለው የሰሜን አፍሪካው ቡድን ወደ ምድብ ድልድሉ መግባቱ ተጋጣሚያቸው ጠንካራ እንደነበረ ያሳያል ብሎ እንደሚያምን ታግሯል።

ስለ ናትናኤል ዘለቀ

አሰልጣኝ ማሪያኖ ባሬቶ ዋልያዎቹን በሚያሰለጥኑበት ወቅት ወጣቱ ፈረሰኛ ናትናኤል ዘለቀ የዋልያዎቹን የተከላካይ አማካይ መስመር በቋሚነት መምራት ጀምሮ ነበር። ነገር ግን በአሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝና ዘሪሁን ሸንገታ የሚሰለጥነው ቅዱስ ጊዮርጊስ ናትናኤል ዘለቀን በቋሚነት አያጫውተውም። ምክንያቱ ምንድን ነው ተብሎ የተጠየቀው ፋሲል ተካልኝ

 “ጥያቄው በተደጋጋሚ ጊዜ ይነሳል። ነገር ግን መታወቅ ያለበት አንድ ነገር ከተወሰኑ ጨዋታዎች በኋላ ናትናኤል ጉልበቱ ላይ ጉዳት ደርሶበት ስለነበረ በሙሉ ሀይሉ አይደለም እየተጫወተ ያለው። ከቡድኑ ጋር የቆየው ቡድኑን ስለ ሚወድ ብቻ ነው እየተጫወተ ያለው እንጅ ሙሉ በሙሉ ጤነኛ ሆኖ አይደለም የሚጫወተው” ሲል ናትናኤል ዘለቀ ተቀያሪ ወንበር ላይ የተቀመጠበትን ምክንያት ተናግሯል። አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ አያይዞም “ናትናኤል ባለው ችሎታ እና ብቃት ሙሉ በሙሉ ጤነኛ ሆኖ መጫወት ከቻለ ለቀጣዮቹ አስር ዓመታት የአገራችን ምርጥ ተጫዋች መሆን የሚችል ልጅ ነው” ሲል ለወጣቱ አማካይ ተጫዋች ያለውን አድናቆት ገልጿል።

አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ ከወጣቱ አማካይ በተጨማሪ ለሁሉም ቡድኑ አባላት አድናቆቱን በመግለፅ በዚህ ዓመት በጥሩ ብቃት ላይ ሆነው የከረሙትን ኣማከዮቹን ተስፋዬ አለባቸው እና ምንተስኖት አዳነንም አድንቋል። ምንተስኖት አዳነ ከመሃል ሜዳ እየተነሳ በርካታ ጎሎችን ለክለቡ ያስቆጠረ ሲሆን “ማዕበል አረጋጊው” በሚል ቅጽል ስም የሚታወቀው ተስፋዬ አለባቸው በበኩሉ የቡድኑን ሚዛን በማስጠበቅ በኩል የሰራውን ስራ በርካታ የክለቡ ደጋፊዎች ያወድሳሉ። አሰልጣኝ ፋሲልም ይህንኑ ነው የተጋራው።

ስለ ክለብ የስራ አጋሩ ዘሪሁን ሸንገታ

“እኔና ዘርዬ ከአንድ እናት እና አባት አንወለድ እንጅ ወንድማማቾች ነን” የሚለው ፋሲል ተካልኝ ሁለቱ የቀድሞ የፈረሰኞቹ ተጫዋቾች ክለባቸውን ከምክትል አሰልጣኝነት ጀምሮ አሁን ቡድኑን በዋና አሰልጣኝነት እሰከመሩበት ጊዜ ድረስ ከሶስት ዓመታት በላይ በጣምራ እየሰሩ ይገኛሉ። በአገራችን ብዙ ያልተለመደውን በጋራ ተስማምቶ የመስራት ባህል በተመለከተ ላቀረብንለት ጥያቄ “ሁሉንም ነገር ተስማምተን እንሰራለን። እግር  ኳስ የተለያየ አስተሳሰብ የሚፈጥር ቢሆንም ለክለባችን የሚበጀውን ተስማምተን የምንሰራ በመሆኑ እና አብረን ማደጋችን ለስኬት አብቅቶናል” ብሏል።

ስለ ክለቡ ደጋፊዎችና የክለቡ አመራሮች

ክለቡ አስቸጋሪ ጊዜ ላይ በነበረበት ወቅት በእኛ ላይ እምነት አሳድሮ ከባዱን ኃላፊነት ስለሰጠን አመራሩን ላመሰግነው እወዳለሁ። የተሰጠንን አደራም በውጤት መልሰናል ብዬ አስባለሁ። ደጋፊዎቻችን የክለባችን ሀይል ናቸው። እኛም ከክለባችን የሚፈልጉትን አሸናፊነት እንዲያገኙ ስላደረግን ደስ ብሎኛል። ለዚህም እንኳን ደስ አላችሁ ልላችው እፈልጋለሁ።

ዘሪሁን ሸንገታ
Zerhun Shengeta

በኮተቤ ዩኒቨርስቲ የስፖርት ሳንይንስ ትምህርቱን እየተከታተለ ያለው እና ለኢንስትራክተር መንግስቱ ወርቁና ለአሰልጣኝ አስራት ኃይሌ አድናቆቱን የሚሰጠው አሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ በፈረሰኞቹ ደጋፊዎች ዘንድ በእጅጉ የሚወደድና የሚከበር አሰልጣኝ ነው። እግር ኳስን በተከላካይነት ተጫውቶ ያሳለፈው ወጣቱ አሰልጣኝ በዚህ ዓመት የተመዘገበውን ድል “ለ80ኛ ዓመት ክብረ በዓል ማድመቂያ የተሰጠ ገጸ በረከት ነው” ሲል ይገልጸዋል። ድሉ የፈጠረበትን ስሜት ሲገልጽም “አጀማመራችን ጥሩ ስላልነበረ ያንን አስተካክለን ዋንጫውን በማንሳታችን ትልቅ ደስታ ተሰምቶኛል” ብሏል። አሰልጣኝ ዘሪሁን “ምንም እንኳን አጀማመራችን ጥሩ ያልነበረ ቢሆንም ችግራችንን አስተካክለን ዋንጫውን እንደምናነሳው እርግጠኛ ነበርኩ። ምክንያቱም ክለባችን ምንጊዜም የሚያቅደው ዋንጫውን ለማንሳት ነው” ይላል።

የዓመቱ ኮከብ ተጫዋችና ፈታኝ ቡድን

ክለባችን ውስጥ ያሉ ሁሉም ተጫዋቾች ሁሉም ኮከቦች ናቸው የሚለው ዘሪሁን ሸንገታ “አንድ ተጫዋች የግድ መጥራት ካለብኝ በሀይሉ አሰፋ በምርጥ ብቃት ላይ ሆኖ የጨረሰ በመሆኑ የዓመቱ ኮከብ ነው ማለት እችላለሁ” ብሏል። ፈረሰኞቹን በመፈተን በኩል ሁሉም የፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ሲጫወቱ ጠንካራ ተጋጣሚ ሆነው እንደሚጫወቱ ገልጿል። በተለየ መልኩ ግን ባህር ዳር ላይ የአልጄሪያውን ኦልማን ሲገጥሙ ያስመዘገቡት ውጤት እና በፕሪሚየር ሊጉ ደግሞ ከንግድ ባንክ እና ከመከላከያ ጋር ሲጫወቱ የጣሏቸው ነጥቦች እንደሚያስቆጩት ተናግሯል። በግሉም ሲዳማ ቡና በዓመቱ የተሻለ ቡድን እንደነበረም ተናግሯል።

ከምክትል አሰልጣኝነት ወደ ዋና አሰልጣኝነት ስለሚደረግ ሽግግር

ዘሪሁን ሸንገታም ሆነ ፋሲል ተካልኝ የእግር ኳስ ህይወታቸው የተቆራኘው ከፈረሰኞቹ ጋር ነው። በርካታ አስተያየት ሰጪዎች ሁለቱን ወጣት አሰልጣኞች “ለምን ራሳቸውን በሌላ ክለብ ኃላፊነት አይፈትኑም? በምክትል አሰልጣኝነት ሊያረጁ ነው ወይ?” የሚል አስተያየት ይሰጣሉ። ይህንን ጥያቄ ለሁለቱም ወጣት አሰልጣኞች አቅርበንላቸው ሲመልሱ በአገሪቱ ውስጥ የትኛውንም ክለብ የማሰልጠን ልምዱም ሆነ ችሎታው ቢኖራቸውም ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ሆነው በርካታ ልምዶችን ስለሚያገኙ እና ክለቡም ለእነሱ ከዛም በላይ ነው በማለት ወደ ፊት የትኛውንም ክለብ ራሳቸውን ችለው ማሰልጠን ከፈለጉ ሙሉ አቅም እዳላቸው ሁለቱም ተናግረዋልች።

ስለ ስራ አጋሩ ፋሲል ተካልኝ

እኔ እና ፋሰል በእግር ኳስ አይደለም የተገናኘነው ከህፃንነታቸን ጀምሮ አብረን ነው ያደግነው ጎርቤታሞች ስለነበርን እኔ ቤት ምሳ ከበላን እነሱ ቤት እራት እንበላለን ከስፖርቱ ውጪ ፍፁም ወንድማማቾች ነን ስለምንግባባ እና ሰለምንተዋወቅ ለስራችን መቃናትም ትልቅ አስተወፅኦ አድርጎልናል።

ስለ ሊጉ ደረጃ እና ድላቸው በዚህ ዓመት የቅዱስ ጊዮርጊስ የዋንጫ ባለቤት የሆነው የሌሎች ክለቦች ድክመት እንጅ የቅዱስ ጊዮርጊስ ጥንካሬ አይደለም እየተባለ የሚነገር ቢሆንም ዘሪሁን ሸንገታ ግን በዚህ አይስማማም። እንዲያውም ለዘሪሁን 13ቱም የፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች ከፈረሰኞቹ ጋር ሲጫወቱ የመጨረሻ ሀይላቸውን ተጠቅመው እንደሚጫወቱ ነው የሚናገረው።

“ሁሉም ክለቦች ከእኛ ጋር ሲጫወቱ የሚያሳዩትን ብቃት ሁልጊዜም ቢያሳዩት ኖሮ የሊጉ ፉክክር ከፍ ይል ነበር” ይላል። በዚህም ምክንያት የዘንድሮው የሊጉ ዋንጫ የተገኘው በስራ እንጅ በሌሎች ድክመት ላይ ተንጠላጥሎ እንዳልሆነ ይናገራል። በቀጣዩ ዓመት ክለቡ ለሚኖርበት የአህጉራዊ ውድድር ጠንካራ ተፎካካሪ ሆኖ ለመቅረብም ዝግጅት እያደረጉ እንደሆነ ገልጿል።

ይቀጥላል!!!


ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
nigussie [936 days ago.]
 ምንጊዜም ስንጆ!!!!!!!! በርቱ

MIki Maraki [935 days ago.]
 You well said FASILE AND ZERESH ! MENGIZEM GIYORGIS VVVVVVVVVVVVV 12 TIMES CHAMPIONS ! VVVVVVVVVVVVVVVVVVVVVVV

Mule [935 days ago.]
 Tnx Ethio Sport ! St.George fc is our foot ball ambassador ! always St.George fc !

Yoni sanjawe [935 days ago.]
  Kortenebachuhale Fasile and zerihun ! wedefit telek coach tehonalachu .....Yemechachu

Mali [935 days ago.]
  Bulla Gellebba siyawera Sanjawe le 12 gna gize wanchawin belawe vvvvvvvvv yelem lella vvvvvvvvvvvvvvvvvvvv

samiflex [935 days ago.]
 zendero kokeb Behailu Tusa or Mentesenot nachew. next year St.George ye africa champions leag ashenafi yehonale .... lejochachin tarik yeseralu Aduuuuuuu .. .... Tussaaaaa ....... Menteeeeeeee ...... Kobbbbbbooooo ..... Zekiiiiiii ....... Alullaaaaaaa..... Robbyyyyyyyy...... Issaccccccccc ..... Deguuuuuu... .. .. Biyadegelgneeeeee .. .. .. Salaaaaaaaaa ....... Dawaaaaaaa ..... Fetsummmmm ...... Natiiiiiiii .....

Azeb [935 days ago.]
 Mengizem Giyorgis hulem champion yehager kurat ye hager keres yehon team VVVVVVVVVVVVVVVVVVVVV

abitisanjeye [935 days ago.]
  Ene yemigermegne were kenema yetbalew team new hulgize were becha new ende ? meche new le wancha yemifokakerew ? ere meche ? ketmeseret 40 amet honew gin wefe yelem badooooo bet yehon dureye team bulla gellebba dengay kenemma

Eyobe sanjawe [935 days ago.]
  Bulla Gellebba Were Kenema be-13 amet 1 gize wancha eybela ketema yerbeshal. shame on u Dengay kenema shame on u Bulla gellebba ! sanjawe 12 gize beletottale enanet be-kefet mekina yezorachubetin wancha. 12 gize beltenewalle. Sanjawe be kefet mekina ketemma yemizorewe ye africa champion sihon new ! what a difference between Bulla Gellebba and St.George fc !

jossy [935 days ago.]
 s.t george is more than a club

Million [935 days ago.]
 አይ ሼባው ለ80ኒያ አመት በሀገር ውስጥ ዋንጫ ይጎርራል። እድሜ ብቻ።

tamirat.muleta [746 days ago.]
 ቡዙ ግዜ የምናነሳችው ድክመቶች አሁንም አሉ ። ክትጯዋች ያሉስህተቶች። በትስጣችው ስልጠና መልክ እየሔዱ አይደለም ሲስለጥኑና ለጫውታ ሲስለፉ ያላችው የ አጬጨረስ ብቃታችውን ለህዝብ አያሳዩም ለምን? በ አስልጣኝ በኩል ያሉስህተቶች የ አስላለፍ ችጊር አሁንም ምንግዜም የምናነሳችው ችግሮች ናችው ።

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!