አሸናፊዎቹ እና የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ -ክፍል ሁለት-
ግንቦት 18, 2007

ክፍል ሁለት

ፈለቀ ደምሴ እና ይርጋ አበበ

ኢትዮፉትቦል ዶት ኮም የ2007 ዓ.ም.  የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሂደት እና ከ1990 ዓ.ም.  ጀምሮ  የሊጉን ዋንጫ ያነሱ ክለቦችን የሚዳስስ ዘገባና ምልከታ ለእግር ኳስ አፍቃሪው ለማድረስ ሁለት ጨዋታ እየቀራቸው የ2007  ዓ.ም. አሸናፊ የሆኑትን የቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ የተወሰኑ አመራሮች እና ተጫዋቾችን በማነጋገር ጀምሯል።  በክፍል አንድ  ጽሑፋችን የቅዱስ ጊዮርጊሶቹ ተጠባባቂ ዋና አሰልጣኞች ዘሪሁን ሸንገታ እና ፋሲል ተካልኝ ከዝግጅት ክፍላችን ጋር ያደረጉትን ቃለ ምልልስ ማቅረባችን ይታወሳል። ሁለቱ ወጣት አሰልጣኞች በመጀመሪያ የአሰልጣኝነት የሥራ ዘመናቸው ከክለባቸው ጋር የሊጉን ዋንጫ በማንሳታቸው መደሰታቸውን እንደገለጹ እና የክለቡ ሥራ አመራር ቦርድም በእነሱ ላይ እምነት በማሳደሩ እንዲሁም ታማኝ የክለቡ ደጋፊዎች ከጎናቸው ሆነው ስላበረታቷቸው ምስጋናቸውንና ደስታቸውን እንደገለጹ አስነብበን ነበር። በዛሬው ጽሑፋችን ደግሞ ከክለቡ ተጫዋቾች ጋር ያደረግነውን ቆይታ እናቀርባለን።

የጎል መስመሩ ታማኝ ወታደር ሮበርት ኦዶንካራ
Robert Onkara

የዑጋንዳው ብሔራዊ ቡድን እና የፈረሰኞቹ አንድ ቁጥር ሮበርት ኦዶንካራ ባለፉት አስር ዓመታት ውስጥ በፕሪሚየር ሊጉ ከታዩ ጠንካራ የጎል ዘበኞች ቀዳሚው ነው ማለት ይቻላል። ግዙፉ ዑጋንዳዊ  ከአንጋፋው ክለብ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ለአምስት ዓመታት እህል ውሃ ተቋድሷል የዋንጫ ጆሮዎችንም ጨብጧል። ስለ ውድድር ዓመቱ እና ክለቡ ስለተቀዳጀው 12ኛ የሊግ ዋንጫ የተሰማውን ስሜት ለአንባቢያን እንዲገልጽ ጥያቄ አቅርበንለት ነበር። ዑጋንዳዊው የጎል ዘብ ከአንደበቱ የወጣውን የዚህ ጽሑፍ አዘጋጆች ከዚህ በታች እንዲህ አቅርበውታል።

ከክለቡ ጋር ስላለው ትስስር


ከክለቡ ጋር ያለውን ዝምድና ሲገልጽ “ክለቡ ለእኔ ምርጥ ክለብ ነው ተስማምቶኛል። ለልጄም ሆነ ለባለቤቴም በክለቡ ያለኝ ቆይታ ተመችቷቸዋል” ሲል ተናግሯል። ሮበርት አያይዞም በተለይ የክለቡን ደጋፊዎች “አስደናቂ ናቸው አዲስ አበባም ሆነ ከአዲስ አበባ ውጭ ስንጫወት ቡድናቸውን ለመደገፍ ወደ ኋላ የማይሉ ናቸው” ብሏል።

ለግብ ጠባቂው ከቀረቡለት ጥያቄዎች መካከል በተለያዩ አገራት የጎል መስመራችንን ጠብቅልን የሚል ጥያቄ ያቀረቡ ክለቦች መኖራቸው ይነገራል። የአንተ መልስ ምንድን ነው? የሚል ነበር። ሮበርት ሲመልስም “የዝውውር ጭምጭምታዎች በየአቅጣጫው ከተለያዩ አገራት ይመጣሉ። ከደቡብ አፍሪካ ከሱዳን እንዲሁም ከሌሎች አገሮች ጥሪዎች ይመጣሉ። ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ውል አለኝ ወደ ፊት ግን የሚሆነውን አብረን እናያለን” ብሏል።

የዘንድሮው የቡድኑ አቋም እና ኮከብ ተጫዋች


በ24 ጨዋታዎች 51 ነጥቦችን በመሰብሰብ ለዋንጫ የሚያበቃውን የነጥብ ድምር ቀድሞ እነደሚበቃው ያወቀው ቅዱስ ጊዮርጊስ 12ኛውን የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ ካነሳ ቀናት ተቆጥረዋል። ለዚህ ክብር ያበቃቸው ደግሞ ጠንካራ ስራ መሆኑን በተለይም በሁለተኛው የውድድር አጋማሽ ክለቡ ያሳየው ብቃት አስገራሚ መሆኑን 30 ቁጥር ለባሹ የፈረሰኞቹ መተማመኛ የኋላ ደጀን ይናገራል። በሊጉ በርካታ ምርጥ ተጫዋቾች አሉ የሚለው ሮበርት ኦዶንካራ ነገር ግን የበሀይሉ አሰፋ ብቃት ከሁሉም የተለየ እንደሆነበት ተናግሯል።

ስለ ፍጹም ቅጣት ምት

ፍጹም ቅጣት ምቶችን የመያዝ ተሞክሮህ ደከም ይላል ተብሎ  ይነገራል ለዚህ አስተያየት ምን ትመልሳለህ  ተብሎ ሲጠየቅ  “ችግሬ ፔናሊቲ የማዳን ብቻ አይደለም። እንደማንኛውም በረኛ በርካታ ደካማ ጎኖች አሉኝ ላሻሽላቸው የሚገቡ። በዓለም ላይ የሚገኙ ሁሉም ምርጥ በረኞችም መቶ ፐርሰንት ትክክል ናቸው አይባልም። እኔም ላሻሽላቸው በሚገቡኝ ድክመቶቼ ላይ ጠንክሬ በመስራት ለማስተካከል እሰራለሁ። ምክንያቱም እግር ኳስ በራሱ ትምህርት ቤት ነው” ብሎ መልሷል።


ዝምተኛው አምበል ደጉ ደበበ
Degu Debebe

ስለ ድሉ

ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ለስምንተኛ ጊዜ ሻምፒዮን ዘንድሮ መሆንህ ነው። ከስምንቱ  ድል ላንተ በተለይ ልዩ ሆኖ የሚታወስህ ካለ የቱ ነው? ተብሎ ለተጠየቀው ጥያቄ ሲመልስ “ለእኔ የተለየ የምለው ዋንጫ የለም ነገር ግን የክለባችንን 80ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ለማክበር እየተዘጋጀን ባለንበት ወቅት ዋንጫውን ይዘን ወደ በዓሉ መቅረባችን የተለየ እንዲሆን ያደርገዋል” በማለት የዘንድሮውን የሊግ ክብር የሚያወድሰው አምበሉ ደጉ ደበበ ነው።

የአርባ ምንጭ ከተማ ተወላጁና አመለ ሸጋው አምበል ደጉ ደበበ የፈረሰኞቹ ደጋፊዎች ከሚያከብሯቸው ታማኝ ተጫዋቾቻቸው አንዱ ነው። በዚህ ዓመት ክለቡ በውድድር ዓመቱ አጀማመር ባሳየው ደካማ አቋም ለዋንጫ ክብር ላይበቃ ይችላል ብለህ ሰግተህ ነበር? የሚል ጥያቄ አቅርበንለት ሲመልስ “ቅዱስ ጊዮርጊስ አንጋፋ ክለብ ነው። በ80 ዓመት ታሪኩ የወሰደው ትምህርትም ከድክመት እንዴት መነሳትና ወደ አሸናፊነት መምጣት እንደሚቻል ስለሆነ ዘንድሮም የሊጉን ዋንጫ ላንበላ እንችላለን የሚል ስጋት አልነበረኝም” በማልት ተናግሯል። በዚህ ዓመት በፕሪሚየር ሊጉ ከተካፈሉ ተጫዋቾች መካከል የተሻለ እንቅስቃሴ ካሳዩ ተጫዋቾች  የክለብ አጋሩ በሀይሉ አሰፋ እንደሆነ የሚናገረው ደጉ ደበበ የወላይታ ድቻው አጥቂ ባዬ ገዛኸኝም በዓመቱ ጥሩ እንቅስቃሴ ካሳዩ ተጫዋቾች ይመደባል በማለት ይናገራል።

የማይመሳሰሉት መንትዮች
Tesfaye Alebachew

ግዙፍ ሰውነት እና ሀይልን ቀላቅሎ መጫወት መለያው የሆነው ተስፋዬ አለባቸው እና በሁለቱም መስመሮች ኳስን ይዞ በመሮጥ ለተከላካይ መስመር ተጫዋቾች ራስ ምታት የሆነው በሀይሉ አሰፋ በዚህ ዓመት ቅዱስ ጊዮርጊስ ላስመዘገበው ውጤት በግንባር ቀደምነት ከሚጠቀሱት ተጫዋቾች መካከል ይመደባሉ። ሁለቱም አጨዋወታቸው የተለያየ ባህሪያቸው ለየ ቅል የሆኑት የፈረሰኞቹ አማካዮች ሜዳ ላይ ያላቸውን ሁሉ ለክለባቸው ለመስጠት ወደ ኋላ ማለት አይችሉም። በሙሉ አቅማቸው የመጫወት ፍላጎትም እንዳላቸው ይነገራል። 12ኛውን የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ ክለቡ ማንሳቱን ካረጋገጠ ከሁለት ቀናት በኋላ ከዝግጅት ክፍላችን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ “ለደጋፊዎቻችን እና ለክለቡ አመራሮች የሚገባቸውን ውለታ የከፈለ ድል” ሲሉ ገልጸውታል።
Behailu Asefa

የሊጉን ኮከብ ተጫዋች ምረጡ ብትባሉ የእናንተን ድምጽ ማግኘት የሚችለው ተጫዋች ማን ነው? የሚል ጥያቄ ጠይቀናቸው ነበር። በቅድሚያ መልስ የሰጠው በሀይሉ አሰፋ ሲሆን “ለሃዋሳ ከነማ የሚጫወተው ሙሉጌታ ምህረት  እንደ ቀደሙት አመታት በዚህ ዓመትም ቡድኑን እየመራ እና በጥሩ ብቃት ሲጫወት ስለከረመ ለእኔ አሁንም ሙሉጌታ ጥሩ ተጫዋች ነው” ያለ ሲሆን ተስፋዬ አለባቸው ግን “በሀይሉ አሰፋ የዓመቱ ኮከብ መሆን ይችላል” ሲል የክለብ አጋሩ የዓመቱ ኮከብ መሆን የሚያስችል ብቃት እንዳለው ገልጿል።

በበርካታ የስፖርት መገናኛ ብዙሃን እና የስፖርት ቤተሰብ ዘንድ ኮከብ እንደሚሆን እየተነገረለት ያለው በሀይሉ አሰፋ “እኔ ኮከብ መባል አላማዬ አይደለም። የእኔ አላማ የነበረው ከክለቤ ጋር ዋንጫ ማንሳት ነበር ይህ ተሳክቶልኛል። ሌላው ትርፍ ነው። ነገር ግን ኮከብ ተብዬ ክለቤ ዋንጫ ባይበላ ምን ዋጋ አለው” በማለት ከግል ዝና እና ክብር ይልቅ የቡድን ውጤት መቅደም እንዳለበት ተናግሯል።  ከሁለቱ ተጨዋቾች ጋር ያደረግነውን ሰፊ ቃለ ምልልስ በሌላ ጊዜ የምንመለስበት ይሆናል።

ይቀጥላል!!!

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
jossy sanjaw [1002 days ago.]
 #B.A.7 IS STAR

Abiy Demissie [1002 days ago.]
 Rwanda Or Uganda??

Mali [1002 days ago.]
 Behailu and Tesefes ye-sanjeye jegennoch leboudenachu demmmmm new yesetachute ! enwedachuhalen ! mengizem Giyorgis !

Mule [1002 days ago.]
 Behailu Aseffa malet Arien Robben malet new ! jegenna kememme yehonech ye-sanjeye leje nech Tusssssssaaaaaaaaaaaaaaaaaa !

Yoni [1002 days ago.]
 Tusssssssaaaaaaaaaaaaa zendero Kokebbe new ! Behailu Dawit Meberatun yetkalin meret lejachin new

Yoni sanjawe [1002 days ago.]
  Tesfaye Kobbo .....Ethiopiawiwe Alonso or Ethiopiawiwwe Masherano ! zendero yemigerem akuam lay mehoneh sigermen national team alememereteh betam....betam yasaferalle ! coach yohanes ke-Tesfaye kobbo gar chiger alebeh ende ?????????? shame on you coach Yohanes !

sami [1002 days ago.]
  leke nesh Yoni Tesfaye Kobbo le-national team memeret yalebet kokeb yehon leje new

MIki Maraki [1002 days ago.]
  Tesfaye Kobbo aydelem 44 list west best 11 list west megebat yalebet ethiopiawiwe Masherano new ! Yohanes betam tasaferaleh ayneh yeshekelalle ende ? are u blind ???????????

Sule [1002 days ago.]
 shame on you coach Yohanes ! ayneh yeshekelalle ende ? ke- Tesfaye Kobbo gar chiger alebeh ende ? leju kezhi belay min aynet performance yasaye ???? shame on you Yohanes .......betam tasaferaleh !

Yoni sanjawe [1002 days ago.]
 Betam yasaferale ametun mulu meret akuame yasayen leje national team alememeret min yebalalle ? leju eko best 11 west enquan megebat yalebet leje new ! yasaferale ye Yohanes sra 44 techawache mereto Tesfaye Kobbon yezelewalle. ere aynefam sham new yohanes

Mule [1002 days ago.]
 " Tesfaye Kobbo malet ethiopiawiwe Masherano or Alonso new " esmamalehu yegebawale tesfesh

Tesfaye [1002 days ago.]
  ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =

Tesfaye [1002 days ago.]
 ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =ተስፋዬ አለባቸው = Masherano = Alonso =

babi [1002 days ago.]
 tadele mengesha is man of the yearrrrrrrr TADU #1

selamawit [1002 days ago.]
 አንዳንዶች ማዕበል አረጋጊው ይሉታል ...አንዳንዶች አባቴ ይሉታል ...ብዙዎቻችን በካምቦሎጆ በስሙ ዘምረንለታል ...በኢ/ፕ/ሊግ ዘንድሮ በተከላካይ አማካይ ቦታ ድንቅ ብቃቱን ያሳየው ተስፋዬ አለባቸው ( ቆቦ) ለብሄራዊ ቡድኑ አለመጠራቱ አስገርሞኛል ውሳኔው የአሰልጣኙ ቢሆንም ልጁ ያለበት አቋም ለብሄራዊ ቡድኑ የሚያስጠራው ነው ቆቦ ከጋቶችም ከአስራትም የተሻለ ልምድም የኳስ ችሎታም አለው እኔ ተስፋዬ አለባቸው ብሄራዊ ቡድኑ ላይ ተፅህኖ መፍጠር እንደሚችል አምናለሁ !

Mamish [1002 days ago.]
  Tesfaye Alebachew means simply Ethiopiawiwe Masherano !

Yoni sanjawe [1002 days ago.]
 Tesfaye Alebachewe Kobbo le-national team yeged meterat alebet semetehal yohanes ???!!!

sami [1002 days ago.]
 betam yasaferal ye coach yohanes sra ametun mulu goooooood performance siyasaye yeneberen leje le national team alemeterat min yebalalle ? ere shame new sham sham new yohanes.

Eyasu [1002 days ago.]
  @ sami i thiink ye waliyaw coach yohanes ke Tesfaye gar ye gele tseb saynorachew aykerem !

sami [1002 days ago.]
 free ena fare election aydelem Tesfaye Kobbo kaltettera ! Kobbbbbbbbboooooooooo le waliyawe yeged yasfelgale !

Mali [1002 days ago.]
  aynefam ye yohanes sra Nati ena Tesfaye kobbo le national team meterat alebachewe ! semetehal yohanes !

Yoni sanjawe [1002 days ago.]
 are you blind coach Yohanes ??? ametun mulu yet neberek Tesfaye Kobbo Yemehal medawe masherano yeserachewin jebedoch mayet yetsanehe ?!!!

beza [1002 days ago.]
 ere yoni semetawi atehugni erget new leju le national team meterat yegebawalle

Jo [1002 days ago.]
 Keep going St. George, kobo mingizam 1gna.

Naod [1002 days ago.]
 Tesfaye Alebachew le waliyawe yemetinal yasfelgale.

Babi [1002 days ago.]
 really am very sorry for Tesfaye Kobo. kezhi belay min aynet chilota yasaye le memeret ?! aye emeye ethiopia mech new free ena fare yehon election yemenayebesh ??????!!!!

Mule [1002 days ago.]
 betam yemigermew eko leju best 11 west megebat yemigebawe leje hono sale 44 techawache temereto ke 44 west alemenoru betam yasazenale yasaferalle.

yohannes Demissie [1001 days ago.]
 I am very happy, that we got our Cup.Regarding to National team please let give chance for couch and see what will com. We are not like........last year asking Dawit to play. shame for them

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!