ዮሐንስ ሳህሌ : በነፃነት መስራትን በተመለከተ ፌዴሬሽኑ እስካሁን እያደረገ ያለው ጥሩ ነው፡፡
ግንቦት 25, 2007

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በትናንትናው እለት በኢንተር ኮንቲኔንታል ሆቴል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን በተመለከተ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ በዚህ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይም ከፌዴሬሽኑ በኩል የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል እና የብሔራዊ ቡድኑ የቡድን መሪ አቶ ዮሴፍ ተስፋዬ እንዲሁም  ሦስቱ የብሔራዊ ቡድን አሰልጣኞች ዋና አሰልጣኝ ኢንስትራክተር ዮሐንስ ሳህሌ ረዳት አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ የበረኞች አሰልጣኝ አሊ ረዲ ተገኝተዋል፡፡ 
Press Conference About The Walya's

በዚህ መግለጫ ላይ የተለያዩ ጥያቄዎች ተነስተዋል፡፡ ከዚህም መካከል ስለ አሰልጣኞች ነፃነት ስላልተመረጡ እና ስለተመረጡ ተጫዋቾች፣ ከውጪ ስለተመረጡ ተጫዎቾች፣ በተጣበቡ የልምምድ ጊዜ ወደ ውድድር መግባት ስለሚኖረው ተጽዕኖ፣ ስለተዘጋጀው የወዳጅነት ጨዋታ፣ በተከታታይ ስለሚደረጉ ውድድሮችች ጫና፣ ስለኮቺንግ ስታፍ ያለመሟላት  ፣የፊዚካል እና የሳይኮሎጂ አሰልጣኝ አለመመደቡ፣ ምክትል አሰልጣኙ ፋሲል ተካልኝ ስላለበት ተደራቢቢ ስራ  እና ሌሎች በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን አሰልጣኞቹ እና የፌዴሬሽኑ ተወካይ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ ለዛሬ ዋና ዋና ያልነውን እንደሚከተለው አቅርበነዋል፡፡ 

አቶ ዮሴፍ ተስፋዬ

ፌዴሬሽኑ ለብሄራዊ ቡድኑ እያደረገ ስላለው እገዛ ሲያስረዱ፡-   ፌዴሬሽኑ ለብሔራዊ ቡድን በሙሉ ሀይሉ እገዛ እያደረገ ነው፡፡ ከዛምቢያ ብሔራዊ ቡድን ጋር የወዳጅነት ጨዋታ አመቻችተናል በድርድርም የ10 ሰው የአይሮፕላን ትኬት ወጪ ብቻ ችለን ሊመጡ ተስማምተዋል፡፡ የታንዛኒያ ብሔራዊ ቡድን ለራሳቸው ዝግጅት ስለሚመጡ ያለምንም ወጪ ከእነሱ ጋር ውድድር እንዲደረግ ተስማምተናል በማለት ለብሔራዊ ቡድኑ ጥቅም ሲባል በክረምቱ ዝናብ እና የአዲስ አበባ ስታዲየምም እጅጉን የተጐዳ ስለሆነ ለካፍ ውድድሩ ወደ ባህርዳር እንዲዛወር የጠየቅን በመሆኑ ባህርዳር ላይ ሊደረግ እንደሚችል አስረድተዋል፡፡

አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ

በነፃነት  መስራትን በተመለከተ፡-  ፌዴሬሽኑ እስካሁን እያደረገ ያለው  ጥሩ ነው ወደፊት ደግሞ የጎደሉ ነገሮች በሂደት ይስተካከላሉ፡፡  ፌዴሬሽኑ የተጫዋቾችን ምርጫ በተመለከተ ሁሉም አሰልጣኝ ሆነ ግለሰብ የራሱ የሆነ አመለካከት አለው፡፡ አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው የራሱ ሚስተር ባሪያቶም የራሱ እኔም ኢንስትራክተር ዮሐንስ ሳህሌም የራሴ የሆነ አመለካከት አለኝ፡፡ በእናንተ በጋዜጠኞች መካከል እንኳን አንዱ የአርሰናል ተጫዋች ቢወድ ሌላው ላይወድ ይችላል፡፡  

 ስላልተመረጡ እና ስለተመረጡ ተጫዋቾች:-  በዚሁ በአሰልጣኝነት ቦታ ላይም የተቀመጠ አሰልጣኝ የራሱ በሆነ የአጨዋወት መንገድ ይበጀኛል ያለውን ነው የሚመርጠው፡፡ በቦታው ላይ ያለሁት ደግሞ እኔ ነኝ፡፡ የሚመለከተውም እኔን ነው፡፡ አንዱ ዳዊት እስጢፋኖስ ሌላው ተስፋዬ አለባቸውን ደግሞ ሌላው ናትናኤል ዘለቀ ለምን አልመረጥክም ይለኛል፡፡ እኔ ሁሉንም አዳልቼ አይደለም ያልመረጥኳቸው፡፡ ከኔ የአጨዋወት ጋር የሚሄዱልኝን ተጫዋቾች ነው የመረጥኩት ከዛ ውጪ እከሌን እከሌን ቢሉኝ ሁሉም ለራሱ የታየውን ስለሚመርጥ ችግር የለውም፡፡ ግን ለጊዜው ቦታው ላይ ያለሁት እኔ ስለሆንኩ ለኔ የሚስማማኝን መርጫለሁ፡፡ 

የተጫዋቾችን ስነምግባር በተመለከተ፦ ሜዳ ላይ የሚፈጠሩ ስህተቶችን እደሁኔታው ልቀበል እችላለሁ ስነምግባርን በተመለከተ ግን የሀገር እና የባንዲራ ጉዳይ ስለሆነ ልንደራደር አንችልም አሁን እንኳን ለብሄራዊ ቡድን ተጠርቶ በጊዜው የማይገባ ካለ እራሱን አዳገለለ ነው የሚቆጠረው።
 
ዝግጅትን በተመለከተ፦ 44 ተጫዋቾችን መርጠን በመያዝ  የርስ በርስ ውድድር በማድረግ 23 ተጫዋቾችን አስቀርተናል። የጊዜ መጣበብ ቢኖርም ምንም ሳንሞክር ከመቅረት ይሻላል ብለን የወዳጅነት ጨዋታ ማድረግን መርጠናል።

ከውጪ የሚመጡ ተጫዋቾች በተመለከተ፦ 5 ብቻ የሆኑበት ምክንያት በአበባው፣ በአሚን እና በዮሱፍ ቦታ ሀገር ውሰጥ ባሉ ተጫዋቾች መተካት እንችላለን በሚል ነው። የጠራናቸው የአጥቂ መስመር ተጫዋቾች ሲሆኑ እነሱን የሚተካ የለንም እንደተመለከታችሁት በሊጉ ኮኮብ ግብ አግቢ ሆነው የጨረሱት የውጪ ተጫዋቾች ናቸው። ስለዚህ መሸፈን ባልቻልንባቸው ቦታ ብቻ ነው ጥሪ ያደረግነው።  

ረዳት አሰልጣኞችን በተመለከተ፦  ሁለት ምክትል አሰልጣኞች እና የተሟላ የህክምና ቡድን አለን ለጊዜው ይህ በቂ ነው። ባለን ጠባብ ግዜ  የሳይኮሎጂ እና የፊዚካል አሰልጣኝ መጥቶ ውጤታማ ይሆናል ብዪ አላስብም።  

ለሚዲያው መረጃ መስጠትን በተመለከተ   አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ሲመልሱ  ሁሉንም በአንድ ላይ ለማግኘት እና በተጨማሪም ከዋሊያዎቹ ስፖንሰር ከዋሊያ ቢራ ጋር ፌዴሬሽኑ ባለው ስምምነት መሠረት ፕሬስ ኮንፈረንሶቹን በሙሉ ከስፖንሰሩ ጋር በማቀናጀት እንዲሰራ ከስምምነት ላይ ተደርሷል ብለዋል። በዚህ ጥያቄ ላይ ተጨማሪ ማብራሪያ የሰጡት የፌዴሬሽኑ ተወካይ አቶ ዮሴፍም በየጨዋታው ማብቂያ ላይ ፕሬስ ኮንፈረንስ አሰልጣኞቹ እንደሚሰጡና  ከዚህ ውጪም ላሉ መረጃዎች በህዝብ ግንኙነቱ በኩል በየጊዜው ፌዴሬሽኑ መረጃ እንደሚሰጥ ተናግረዋል፡፡

ፋሲል ተካልኝ

ምክትል አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝም ትናትና ከክለብህ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ሻፒዮን ሆነህ ደስታህን አጣጥመህ ሳትጨርስ  በማግስቱ ወደ ብሄራዊ ቡድን መጥተሃል ከፊት ደግሞ ክለብህ የጥሎ ማለፍ ውድድር ይጠብቅሀል እና ይሄን እንዴት ታስታርቀዋለህ ተብሎ ለተጠየቀው ጥያቄ ሲመልስ፦ ትናትና ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር የነበረኝ ደስታ ትናትና አልቋል። ዛሬ የማስበው ብሄራዊ ቡድኑ ከሌሴቶ ቡድን ጋር ስለሚያደርገው ጨዋታ ብቻ ነው። ሌላውን ጊዜው ሲደርስ የምናየው ይሆናል በማለት መልሷል።

በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ለፌዴሬሽኑ ተወካይ እና ለአሰልጣኞቹ የተለያዩ ጥያቄዎች የቀረቡ ሲሆን ይህንን የሚያስተባብሩት የፌዴሬሽኑ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ወንድምኩን አላዩ ጥያቄዎች ሳይመለሱ እንዳይዘለሉ በመከታተል ፕሮግራሙን በጥሩ አግባብ መርተውታል፡፡ እኚህ ባለሙያ ወደፌዴሬሽኑ ከመጡ በኋላ ለረጅም አመታት በጋዜጠኝነትና በፌዴሬሽኑ ያለውን የመረጃ ልውውጥ ችግር በጥሩ ሁኔታ ቀርፈውታል፡፡ ለእያንዳንዱ ጋዜጠኛ በእየለቱ በኢሜል መረጃ ይልካሉ ሲጠየቁም ባግባቡ ይመልሳሉ ይህ እንደ አንድ በጎ ነገር የሚታይ ሲሆን ወደፊት ከዚህም በላይ ተሻሽሎ ሚዲያው ለህብረተሰቡ በቀላሉ መረጃ የሚደርስበት መንገድ እንደሚፈጠር ፌዴሬሽኑ መስራት አለበት፡፡ 

ፈለቀ ደምሴ 
ለኢትዮ ፉትቦል

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
Mule [992 days ago.]
 Shame on you Yohanes ! Dawit telaleh ende ?! Dawitin endet abereh ke-Tesfaye ena ke-Nati gar tedebalkewalehe ?! shame on you ! Tesfaye and Nati they are best ! they are great great defending midfielders i hope you will regret.

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!