አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ ጥሪ ካደረጉላቸው 44ት ተጫዋቾች 24ቱን አስቀሩ
ግንቦት 26, 2007

አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ ለብሄራዊ ቡድን ከዚህ በፊት ጥሪ ካደረጉላቸው 44 በሀገር ውስጥ ከሚጫወቱ ተጨዋቾች  24ቱን ብቻ ማስቀረታቸውን አስታወቁ።  በሌላ በኩል ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ምንጮች እንደደረሰን መረጃ ከሆነ ጥሪ ከተደረገላቸው በውጪ ሀገር በፕሮፌሽናልነት ከሚጫወቱ ተጨዋቾች ውስጥ ኡመድ ኡክሪና ሽመልስ በቀለ ነገ አዲስ አበባ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል። ሳላዲን ሰይድ ለሚጫወትበት ክለብ ግንቦት 29ኝ  ቀን ጨዋታ ስላለበት ለወዳጅነት ጨዋታው እንደማይደርስ ቢታወቅም ከሲሸልስ ጋር ለሚደረገው ጨዋታ ይመጣል ተብሎ የይጠበቃል። ጌታነህ ከበደ ለሚጫወትበት ክለብ ተደራራቢ ጨዋታዎች እያደረገ ቢሆንም  ለሲሸልሱ ጨዋታ እንዲመጣ በፌዴሬሽኑ በኩል ጥረት እየተደረገ ነው ተብሏል።ዋሊድ አታ በጉዳት  ምክንያት እንደማይመጣ  ከወዲሁ ታውቋል። 

ከዋልያዎቹ ጋር የወዳጅነት ጨዋታ ለማድረግ የዛምቢያ ብሄራዊ ቡድን አርብ ግንቦት 28 ቀን አ.አ ይገባል። ጨዋታው እሁድ ሰኔ 30, 2007 ዓ.ም.  በአዲስ አበባ ስታድየም ይካሄዳል።

 አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ ለብሄራዊ ቡድን የመረጧቸው 24ት ተጫዋቾች ዝርዝር የሚከተለው ነው:-

በረኞች
1. ታሪክ ጌትነት     ደደቢት
2. ጀማል ጣሰው      መከላከያ
3. አቤል ማሞ         ሙገር ሲሚንቶ

ተከላካዮች
4. ስዩም ተስፋዬ         ደደቢት
5. ሞገስ ታደሰ             ሲዳማ ቡና
6. አስቻለው ታመነ      ደደቢት
7. ሙጂብ ቃሲም        ሐዋሳ ከነማ
8. ተካልኝ ደጀኔ          ደደቢት
9. ዘካሪያስ ቱጂ           ቅ/ጊዮርጊስ
10. ሳላዲን ቤቸጊቾ      ቅ/ጊዮርጊስ
11. ግርማ በቀለ           ሐዋሳ ከነማ
12. በረከት ቦጋለ          አርባ  ምንጭ ከነማ

የመሃል ሜዳ ተጨዋቾች
13. ራምኬል ሎክ          ኤሌትሪክ
14. አስቻለው ግርማ       ኢትዮጵያ ቡና
15. ብሩክ ቃልቦሬ          ወላይታ ዲቻ
16. ጋቶች ፖኖም          ኢትዮጵያ ቡና
17. ምንተስኖት አዳነ     ቅ/ጊዮርጊስ
18. በኃይሉ አሰፋ          ቅ/ጊዮርጊስ
19. ፍሬው ሰለሞን         መከላከያ
20. አፍሬም አሻሞ         ንግድ ባንክ

አጥቂዎች
21. ባዬ ገዛህኝ           ወላይታ ዲቻ
22. ኤፍሬም ቀሪ        ሙገር ሲሚንቶ
23. ዮናታን ከበደ        አዳማ ከነማ
24. ቢኒያም አሰፋ       ኢትዮጵያ ቡና

ፈለቀ ደምሴ
ለኢትዮ ፉትቦል

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
Dani Sanjawe [926 days ago.]
 በጣም ያሳፍራል የኮቹ ስራ አመቱን ሙሉ ምርጥ ብቃት ሲያሳይ የነበረን ጀግና ተጫዋች ኢትዮጵያዊውን ማሼራኖ ተስፋዬ አለባቸውን ( ቆቦ ) ኣለመምረጡ በጣም ያሳፍራል ያሳዝናልም ! ቆይ ተስፋዬ አለባቸው ( ቆቦ ) ለመመረጥ ከዚህ በላይ ምን አይነት ፐርፎርማንስ ያሳይህ ? አስማተኛ አይደለም አስማት እንዳያሳይህ !!! በጣም የሚያሳፍረው ከ 44 እጩ ውስጥ የሱ ስም አለመኖሩ ነው በጣም ያሳፍራል ..... በጣም ያሳፍራል ቤስት 11 ውስጥ መግባት የሚገባው ልጅ መሆኑ ግልፅ ነው ልጁ ምርጥ የአማካይ ተከላካይ ነው !

genanaw [926 days ago.]
 Good start! Lets help each other for better national team result.

mesfin [926 days ago.]
 አሰልጣኙ እንደው እልህ ልጋባ እኔ አውቃላሁ ካላሉ በስተቀር ተስፋዬ አለባቸው ለብሄራዊ ቡድን ሊመረጥ የማይችልበት ምንም በቂ ምክንት የላቸውም.

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!