የ2007 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ቅኝት
ግንቦት 28, 2007

የ2007 ዓ.ም የፕሪሚየር ሊግ ውድድር መጠናቀቁን ተከትሎ ኢትዮፉትቦል ዶትኮም የዓመቱን ውድድር ሙያዊ ምልከታ እንደሚያቀርብ ቃል መግባታችን ይታወሳል። ቃል በገባነው መሰረት ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት ከእናንተ ከአንባቢያን የሚደርሱንን ሃሳቦች በማካተት ሙያዊ ዳሰሳ ለማቅረብ ወደድን። በምልከታችንም በውድድር ዓመቱ የተከሰቱትን አብይ ክስተቶች በማንሳት   መሻሻል ያለባቸው እንዲሻሻሉ ሊደገፉ የሚገባቸው ካሉ ደግሞ እንዲበረታቱ ሙያዊ አስተያየታችንን እናቀርባለን።

የክለቦች በትር በአሰልጣኞች ላይ የበረታበት የውድድር አመት

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 14 ክለቦች ብቻ የሚወዳደሩ ቢሆንም በዚህ የውድድር ዓመት ከወልድያ ከነማው ንጉሴ ዓለሙ እስከ ኤሌክትሪኩ አጥናፉ ዓለሙ ድረስ በዓመት ውስጥ በርካታ አሰልጣኞች ለስንብት ተዳርገዋል። በዚህ የውድድር ዓመት አሰልጣኛቸውን ያላሰናበቱ ክለቦች ሰባት ብቻ ሲሆኑ እነሱም ወደ ብሔራዊ ሊጉ የወረደው ሙገር ሲሚንቶ፣ ከብሔራዊ ሊጉ በዚህ ዓመት አድጎ አስገራሚ ብቃት ያሳየው አዳማ ከነማ፣ ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ አቋሙ እየወረደ የሄደው ሲዳማ ቡና፣ ወላይታ ድቻ፣ አርባ ምንጭ ከነማ፣ መከላከያ እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ናቸው። ይህም በሊጉ ከሚወዳደሩ ክለቦች ግማሾቹ አሰልጣኞቻቸውን ያሰናበቱ ሆነዋል።

ሊጉ በአራት ክልሎች ማለትም አዲስ አበባ ስድስት ክለቦች፣ አማራ ክልል ሁለት፣ ኦሮሚያ ሁለት እና ደቡብ ክልል አራት ክለቦች የተዋቀረ ሲሆን በውድድር ዓመቱ አሰልጣኛቸውን ያላሰናበቱ የአዲስ አበባ ክለቦች ሁለት ብቻ ናቸው። የአማራ ክልል ክለቦች ሁለት ብቻ ቢሆኑም ሁለቱም አሰልጣኛቸውን ሲያሰናብቱ የኦሮሚያዎቹ ደግሞ አሰልጣኞቻቸውን አላሰናበቱም። በዱብ ክልሎች አንዱ ክለብ ብቻ ነው አሰልጣኙን ያሰናበተው።

ቀዳሚዎቹ አሰልጣኞች በሰሩት ስራ ጠብ የሚል ነገር በማጣታቸው ለማሰናበት ከተገደዱት ክለቦች መካከል ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ደደቢት እና ሀዋሳ ከነማ በአዲሶቹ አሰልጣኞች የሚፈልጉትን ነጥብ ሲያገኙ ኢትዮጵያ ቡና እና ወልድያ ከነማ ደግሞ ከቀዳሚዎቹ በምንም ያልተሻለ ውጤት አግኝተዋል። በአንጻራዊነት ማሻሻል ያሳዩት ደግሞ ኤሌክትሪክ እና ዳሽን ቢራ ከፕሪሚየር ሊጉ አለመውረዳቸው እንደ ስኬት ሊቆጠር ይችላል።

ቅዱስ ጊዮርጊስ ብራዚላዊውን አሰልጣኝ ዶ ሳንቶስን ካሰናበተ በኋላ በቀድሞ ተጫዋቾቹና ምክትል አሰልጣኞቹ ዘሪሁን ሸንገታ እና ፋሲል ተካልኝ እየተመራ ለድል ሲበቃ ደደቢት በበኩሉ ንጉሴ ደስታን ካሰናበተ በኋላ በኢንስትራክተር ዮሃንስ ሳህሌ እየተመራ ጥሩ ውጤት አስመዝግቦ በዓመቱ መጨረሻ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቅ ችሏል። የውድድር ዓመቱ ከመጀመሩ በፊት 10 ሚሊዮን ብር ለተጫዋቾች ዝውውር በመመደብ ወደ ውድድር የገባውና በሊጉ ከፍተኛ ውጤት ያመጣል ተብሎ ተጠብቆ የነበረው ሃዋሳ ከነማ የመጀመሪያውን ዙር ያጠናቀቀው በደረጃው ግርጌ 13ኛ ላይ ሆኖ ነበር። አሰልጣኝ ውበቱ አባተን ከቀጠረ በኋላ ግን በተከታታይ ታላላቆቹን ሲዳማ ቡና፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ኢትዮጵያ ቡና እና  ደደቢት በሙሉ በማሸነፍ በ33 ነጥብ 10ኛ ደረጃ ላይ ሆኖ ዓመቱን ማጠናቀቅ ችሏል። ሀዋሳ ከነማ በሁለተኛው ዙር ያሸነፋቸው ታላላቆቹ ክለቦች በሙሉ ከቡና በስተቀር በመጀመሪያው ዙር ሀዋሳ ከነማን ያሸነፉ ነበሩ።  የእነዚህ ሶስት ክለቦች አሰልጣኝ ቀያሪ በእጅጉ ስኬታማ ነበር ማለት ይቻላል ያልነውም ለዚህ ነው።

የውድድር ዓመቱ ሊጠናቀቅ ሁለት ጨዋታዎች ብቻ ሲቀሩት ከቦታቸው የተነሱት የኤሌክትሪኩ አሰልጣኝ አጥናፉ ዓለሙ በዓመቱ መጨረሻ የተሰናበቱ አሰልጣኝ ሆነዋል። አሰልጣኝ አጥናፉ ዓለሙ የውድድር ዓመቱ እንደተጀመረ ጥሩ ውጤት ማስመዝገብ ቢችሉም በውድድር ዓመቱ አጋማሽ በተለይም ወደ ወሳኝ ምዕራፍ በሚሸጋገርበት ወቅት ግን ውጤት ርቋቸው ክለባቸውም ወራጅ ቀጠና ውስጥ መግባቱ ይታወሳል። በቀሪዎቹ ሁለት ጨዋታዎች ሀላፊነቱን የተረከቡት ምክትላቸው አቶ ብርሃኑ ሁለቱን የደቡብ ኢትዮጵያ ክለቦች ሀዋሳ ከነማን እና ወላይታ ድቻን በማሸነፍ በሊጉ መቆየት የሚያስችላቸውን ውጤት ማግኘት ችለዋል። ዳሽን ቢራም ሳምሶን አየለን ካሰናበተ በኋላ በወጣቱ አሰልጣኝ ካሊድ መሃመድ እየተመራ ላለመውረድ ያደረገውን ጥረት በድል በማጠናቀቁ የአሰልጣኙ ቅያሪ በመጠኑም ቢሆን ውጤታማ አድርጎታል ማለት ይቻላል። የሁለቱ ክለቦች አሰልጣኝ ቅያሪ ዓላማውም ከሊጉ ላለመውረድ በመሆኑ ለክለቦቹ እንደ ትልቅ ስኬት ሊቆጠር ይችላል።

በሌላ በኩል የአሰልጣኝ ስንብት አድርገው የሚፈልጉትን ስኬት ማግኘት ያልቻሉት የሰሜን ኢትዮጵያ ተወካዮቹ ወልድያ ከነማዎች እና ኢትዮጵያ ቡና ናቸው። ወልድያ ከነማ አሰልጣኝ ንጉሴ ዓለሙን ያሰናበቷቸው በውድድር ዓመቱ መባቻ ላይ ቢሆንም በምትካቸው ክለቡን የተረከቡት አቶ ሰብስቤ ይባስ ክለቡን ከመውረድ መታደግ ሳይችሉ ቀርተዋል። ቡና ደግሞ አሰልጣኝ ጥላሁን መንገሻን በውድድር ዓመቱ ወሳኝ ወቅት ላይ ቢያሰናብትም የጥላሁንን ወንበር የተቀመጠበት አሰልጣኝ አንዋር ያሲን ስኬታማ ሲሆን አልታየም። በተከታታይ ባደረጋቸው አምስት ጨዋታዎችም ክለቡ ሲሸነፍ የታየ ሲሆን በውድድር ዓመቱ መዝጊያ ላይም ሰባተኛ ደረጃን በመያዝ ከአርባ ምንጭ ከነማ፣ ከሲዳማ ቡና፣ አዳማ ከነማ፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ደደቢት እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ዝቅ ብሎ አጠናቋል። የሁለቱ ክለቦች አሰልጣኝ ቅያሪም ስኬታማ ነው ማለት አይቻልም።

ታማኞቹ ደጋፊዎች

በውጭ አገር የውድድር ዓመቱ ሲጠናቀቅ ለኮከብ ተጫዋቾች፣ አሰልጣኞችና ዳኞች ብቻ ሳይሆን ለኮከብ ደጋፊዎችም ሽልማት ይሰጣል። ይህ ባህል በአገራችን የተለመደ አይደለም። ምናልባት ፌዴሬሽኑ በቀጣዮቹ ዓመታት ይህንን ባህል ተግባራዊ ቢያደርግ በስታዲየም ውስጥ የሚነሱ ስድቦችንና ሽኩቻዎችን ለማጥፋት እገዛ ሊያደርግ ይችላል የሚል እምነት አለን። በአገራችን ከሚታዩ ጠንካራ ደጋፊዎች መካከል በተለይ በአዲስ አበባ ስታዲየም የኢትዮጵያ ቡና እና የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች ልዩ የስታዲየም ውበቶች ናቸው። የሁለቱ ታላላቅ ክለቦች ደጋፊዎች ለስታዲየሙ ብቻ ሳይሆን ለእግር ኳስም ውበት ናቸው ማለት ይቻላል።
CoffeeFamilyRun

በዚህ የውድድር ዓመት ግን በተለይ የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች ለክለባቸው ያሳዩትን ድጋፍ በየትኛውም መመዘኛ የዓመቱ ምርጥ ደጋፊዎች ቢባሉ የሚገባቸው ይመስለናል። ቡድናቸው ከምዕራብ ኢትዮጵያ እስከ ምዕራብ አፍሪካ ተጉዞ ተጫዋቾችን ቢያስፈርምም ዓመቱን ሙሉ በተደጋጋሚ ሽንፈት እና ወጥ ባልሆነ አቋም ቢከርምም ደጋፊዎቹ ግን ተጫዋቾቻቸውን ከመንቀፍ ይልቅ ክለባቸውን እያንዳንዱ ጨዋታ ላይ በመገኘት በጽናት ሲደግፉ ከርመዋል። ይህ ደግሞ ለአንድ የእግር ኳስ ቡድን ትልቁ ሀብቱ እና ውጤቱ ነው።

ኢትዮጵያ ቡና የውድድር ዓመቱ እንደተጀመረ አምስት ተጫዋቾቹ በቀይ ካርድ ከሜዳ ሲሰናበቱ እና የውድድር ዓመቱ ሊጠናቀቅ ወራት ሲቀረው ደግሞ ተጨማሪ አምስት ተጫዋቾቹ በአመለ ብልሹነት ከክለቡ ሲሰናበቱ ደጋፊዎቹ ግን ዓመቱን ሙሉ በጽናት ቡድናቸውን እየደገፉ ዘልቀዋል። ይህ ደግሞ ደጋፊዎቹን የሚያስመሰግናቸው ነው። የደጋፊዎቹ ታማኝነት የተለካው ስታዲየም ገብተው በመደገፋቸው ብቻ አይደለም። የደጋፊዎቹ ታላቅነት የታየው ክለቡ ለሚያስገነባው የተጫዋቾች መኖሪያ ካምፕ ግንባታ የገቢ ማሰባሰቢያ የጎዳና ላይ ሩጫ ሲጠራቸው በአንድ ሳምንት ውስጥ ስምንት ሺህ ካናቴራ በ150 ብር በመግዛትና ለውድድሩ ማድመቂያ ለክለቡ ከሀበሻ ቢራ የተበረከተለትን ቢራ በመግዛት በድምሩ ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ማስገባታቸው ሌላው ማሳያ ሆኗል።

በዚህ አጋጣሚ የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች የዓመቱ ምርጥ ደጋፊዎች ሊባሉ ይገባቸዋል ስንል የአዳማ ከነማ፣ የወላይታ ድቻ፣ የአርባ ምንጭ ከነማ እንዲሁም የሻምፒዮኑ ቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች ለቡድናቸው ይሰጡት የነበረውን ያልተቋረጠ ድጋፍ ዘንግተነው አይደለም። የፈረሰኞቹ ደጋፊዎች ለቡድናቸው ሲሰጡት የነበረው ድጋፍ ዋንጫ እስካነሱበት ጊዜ ድረስ የዘለቀና ለቡድኑም ውጤት ማማር ከፍተኛ አስተዋጽዎ ያደረገ ነበር። የአዳማ ከነማ፣ የወላይታ ድቻ እንዲሁም የአርባ ምንጭ ከነማ ደጋፊዎች ለክለቦቻቸው ባሳዩት ያልተቋረጠ ድጋፍ ጨዋታዎችን  በይበልጥ በማድመቅ ተጠባቂና ፉክክር የበዛባቸው ጨዋታዎች በፕሪሚየር ሊጉ እንዲበረክቱ እያደረጉ ነው። ለዚህም ሊደነቁና ሊበረታቱ ይገባል እንላለን።

ይቀጥላል!!!

ይርጋ አበበ
ኢትዮ ፉትቦልethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
Dani Sanjawe [992 days ago.]
 እንደ ቡላ ገለባ መረንና ስድ ጋጠወጥ ባለጌ ደጋፊ ኢትዮጵያ ውስጥ የለም ስታዲየሙን የስድብ መንደር ካደረጉት ቆይተዋል ! ይመስለኛል በቡድናቸው ተስፋ ቆርጠዋል በየአመቱ ጨጓራቸው ደም ብዛታቸው ራስ ምታታቸው እንደጨመረ ነው በሚደግፉት ቲም ! በየ 13 አመት 1 ጊዜ ዋንጫ የሚበላ ቡድን ተስፋ ስላስቆረጣቸው ዘወትር ስታዲየሙን በስድብና በድንጋይ የጦርነት ሜዳ እንዳደረጉት ነው ! በጣም የሚገርመውና የሚያሳዝነው ነገራቸው ሁልጊዜ ለሽንፈታቸው ፌዴሬሽኑን.... ዳኛውን .....ሳሩን ... ዝናቡን ..... ፀሃዩን..... መፈረጃቸው ማሳበባቸው ነው ! እኔ ግርም የሚለኝ ታዲያ እንዴት ሆኖ ነው የ 12 ጊዜ ሻምፒዮኑ ቅዱስ ጊዮርጊስን ተፎካካሪ ነን የሚሉት ??? Pls ተመልከቱ የዘንድሮ ሊግ ቴብልን ?! መፎካከር ማለት በቡላ ገለባ እና በሳንጃው መሃል 21 ነጥብ ጋፕ መተው ነው እንዴ ??? ሃሃሃሃሃሃሃሃ ሳኩባችሁ ቡላ ገለባዎች.... ሳኩባችሁ ወሬ ከነማዎች .... እባካችሁ ውስጣችሁን ፈትሹ ስራ ሰርታችሁ ተፎካከሩ !

Tesfaye [992 days ago.]
  I think discipline should be credited much more than other issues when fans are considered.Taking that into account,Eth.coffee fans should not be crowned.They were calling names & insulting honourable people in the stadium.

Alba Ssi [991 days ago.]
 ኢትዮ ፉትቦሎች አሪፍ ስራ ነው እየሰራችሁ ያላችሁት። በዚሁ ቀጥሉ።

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!