የባህርዳሩ የዋሊያዎቹ ጨዋታ አስገራሚ የመግቢያ ዋጋ ውሳኔ
ሰኔ 02, 2007

የአዲስ አበባ ስታዲየም ከነበረበት ተደራራቢ ጨዋታ እና ክረምት መግባቱን በማገናዘብ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴረሽን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በመጪው እሁድ ከሌሴቶ አቻው ጋር የሚያደርገውን ጨዋታ ወደ ባህርዳር  አዲሱ ስታዲየም ማዘዋወሩን ሲያሳውቅ  የእግር ኳስ አፍቃሪው ሕብረተሰብ እንዲሁም የስፖርት ሚዲያዎች ሃሳቡን ደግፈውት እንደነበር ይታወቃል።
The Walyas Training Session at Addis Ababa Stadium

ጨዋታው የሚካሄድበትን ስታዲየም ወደ ባህርዳር መዞር     ተከትሎ የእግር ኳስ ፌዴሬሽኑ  የስታዲየም የመግቢያ ዋጋውን ውሳኔ ሲያሳልፍ የአካባቢውን ህዝብ የኢኮኖሚክ  አቅም እና የስታዲየሙን ሰው የመያዝ አቅም ያገናዘበ ይሆናል የሚል የኳስ አፍቃሪውም ሆነ የስፖርት ሚዲያው ባለሞያዎች  የሚጠብቁት ጉዳይ ነበር።

ነግር ግን ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የወጡ ዜናዎች እንደሚያስረዱት  ከሆነ በታሪክ ተደርጎ የማያውቅ ትልቅ ክፍያ ከ50 እስከ 700 መቶ  ብር  የሚደርስ የመግቢያ ዋጋ መወሰኑ ታውቋል። ከዋጋው ውድነት አንጻር ፌዴሬሽኑ እንደዚህ አይነት ውሳኔ ላይ ሲደርስ ተገቢውን ጥናት አድርጎበታል ወይ የሚል ጥያቄ  እንድናነሳ ያስገድደናል። ምክንያቱም ምንም እንኳን በየትኛውም ክልል የሚገኝ ኢትዮጵያዊ  ብሄራዊ ቡድኑ ሲጫወት ጨዋታውን በስታዲየም ተገኝቶ ለማየት እንደሚጓጓ ቢታወቅም የኢኮኖሚክ አቅሙ ከቦታ ቦታ እንደሚለያይ ግልጽ ነው። በመሆኑም የባህር ዳር ከተማ ነዋሪ እንዲሁም የአካባቢው ህዝብ አሁን ፌዴሬሽኑ  ያወጣውን የመግቢያ ዋጋ አቅሙ ፈቅዶና ፈታ ብሎ ጨዋታውን በእስታዲየሙ በብዛት ተገኝቶ   ይመለከታል ብለን ለማሰብ ይከብደናል። የባህር ዳርና የአካባቢው  ህዝብ የሐገር ፍቅሩ ጠንቶበት ቡድኑንን ለመደገፍ  የተጠየቀውን ክፍያ ከፍሎ ቢገባ እንኳን  ከ50ብር እስከ 700ብር የመግቢያ ዋጋ  መጠየቅ ተገቢና ተመጣጣኝ ነው ለማለት ያስቸግራል። እንደዚህ ከፍ ያለ የመግቢያ ዋጋ ለአዲስ አበባ ተመልካችም እንኳን ቢሆን እጅን ያዝ ሊያደርግ የሚችል  ነው።   

በመሆኑም ፌዴሬሽኑ በቅድሚያ ትኩረት መስጠት ያለበት ገንዘብ መሰብሰቡ ላይ ሳይሆን ብሄራዊ ቡድኑ ከምድቡ ለማለፍ የሚያደርገውን ጨዋታ እንዴት አድርጎ መደገፍ እንዳለበት ነው።  በዚህ ረገድ ለቡድኑ ውጤት ማማር የደጋፊው በብዛት በስታዲየሙ ተገኝቶ ቡድኑን  መደገፍ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው። ፌዴሬሽኑ ሊሰበስበው ያሰበውን ገንዘብ ወደፊት ቡድኑ ውጤታማ እየሆነ ሲመጣና አስደሳች ጊዜያትን መፍጠር ከተቻለ በኋላ ቢያደርገው ጥሩ ነው አንላለን።

ፈለቀ ደምሴ
ለኢትዮ ፉትቦል

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
Mamo [988 days ago.]
 Stupid Federation .....Stupid Junedine Bashah !

katanga [988 days ago.]
 shame

Selam251 [988 days ago.]
 For me personally the 700 birr is ok. But the 50 birr should go down to at least 10 birr to satisfy all kind of people.

Sewent [988 days ago.]
 Betame Teru New Gene Salriw ?

ela [987 days ago.]
 sham on eff!

kullo [985 days ago.]
 It is amazing! The EFF declares that they are incapable of leading the Ethiopian soccer dvt. Shame!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!1

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!