ዋልያዎቹ ልምምዳቸውን በቀን ሁለት ጊዜ እያከናወኑ ነው
ሰኔ 03, 2007

በአሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ የሚመሩት ዋልያዎቹ የፊታችን እሁድ ከሌሴቶ ጋር ለሚያደርጉት ጨዋታ ማረፊያቸውን በታላቁ ግራንድ ሪዞርት እና ሰፓ አድርገው በቀን ሁለት ጊዜ ልምምድ እየሰሩ መሆኑን ከባህርዳር የደረሰን መረጃ አመለከተ። አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ ከአማራ ክልል መገናኛ ብዙሃን ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ “ስለተጋጣሚያችን መጠነኛ መረጃ አግኝተናል። ዝግጅታችንንም በሚገባ እየሰራን ነው። በእግር ኳስ ወዳዱ የባህርዳር ከተማ ህዝብ ፊት ስለምንጫወት የሜዳ አድቫንቴጃችንን አስጠብቀን ለማሸነፍ እንጫወታለን” ሲል የገለጸ ሲሆን በውጭ አገር የሚጫወቱ ተጫዋቾች ከሳላዲን ሰይድ በስተቀር ተጠቃለው መግባታቸውንም ተናግሯ።
 
በተያያዘ ዜና የዋልያዎቹ ተጋጣሚዎች የሌሴቶ ብሄራዊ ቡድን ነገ አዲስ አበባ እንደሚገባ እና በባህርዳር የሚያርፍበት ሆቴል ዛሬ ከሰዓት እንደሚታወቅ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴደሬሽን የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ወንድምኩን አላዩ ለዝግጅት ክፍላችን ገልጸዋል። የዋልያዎቹ ቁጥር አንድ የፊት መስመር ተሰላፊ ሳላዲን ሰይድ ነገ አዲስ አበባ ገብቶ ቡድኑን እንደሚቀላቀል ይጠበቃል።
 
ይርጋ አበበ 
ለኢትየ ፉትቦል


ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!