ፌዴሬሽኑ የባህርዳሩ ጨዋታ መግቢያ ዋጋ ላይ ማሻሻያ አደረገ
ሰኔ 04, 2007


የኢትዮጵያ እግር ኳስ  ፌዴሬሽን ባህርዳር ላይ ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ  የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡደን ከሌሶቶ አቻው ጋር ለሚያደርገው ጨዋታ ተምኖት የነበረውን የመግቢያ ዋጋ ማሻሻያ አድርጓል።  ኢትዮ ፉትቦልን ጨምሮ የስፖርት ሚዲያዎች እንዲሁም የኳስ አፍቃሪው ህብረተሰብ ቀደም ሲል ተተምኖ የነበረውን ከ50 እስከ 700 መቶ ብር ይደርስ የነበርውን  የዋጋ ዝርዝር ውድነት በተመለከተ  ምክንያታዊ ትችታቸውን  ሲያቀርቡ መቆየታቸው ይታወሳል። ይህን ተከትሎ ይመስላል ፌዴሬሽኑ  በዋጋ ዝርዝሩ ላይ ከፍተኛ ማሻሻያ በማድረግ የኳስ አፍቃሪው ሕብረተሰብ በብዛት ወደ ስቴዲየም እንዲገባ የሚያደርግ አዲስ የዋጋ ተመን አውጥቷል።

አዲሱ የመግቢያ ዋጋ  ከ10 ብር የሚጀምር ሲሆን ጣራው 700 ብር ነው። ተመልካቹ በተጨማሪ እንደየ አቅሙ ትኬት ገዝቶ እንዲባ ባለ20፣50፣100 እና 200 ብር ትኬቶች እንደተዘጋጁለት ታውቋል።

ኢትዮ ፉትቦል ጨወታውን በቀጥታ ውጤት ስርጭት እና ኮሜንታሪ ለመዘገብ ጋዜጠኛ ፈለቀ ደምሴ ወደ ስፍራው የሚጓዝ ሲሆን የድረ ገጻችን ተከታታዮች ጨዋታውን ውጤት በቀጥታ በኢትዮ ፉትቦል እንድትከታተሉ ከወዲሁ እንጋብዛለን።

ኢትዮ ፉትቦል
 

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
Mali [986 days ago.]
 sel sport minim yemayawek hulla federation west tesegesego.....shame.....shame.....shame on you Junedin !

sami [986 days ago.]
 Aye Junedin Basha funny EFF president ha ha ha ha ha Ethiopia with Leseto 700 Birr ......50 Birr ha ha ha ha

ela [986 days ago.]
 good job!

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!