ጀማል ጣሰው በጉዳት በነገው ጨዋታ ተሰላፊ አይሆንም
ሰኔ 06, 2007

የኢትዮፉትቦል ዶት ኮም ዘጋቢያችን ከባህርዳር ባደረሰን መረጃ መሰረት ነገ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሌሴቶ አቻው ጋር ለሚያደርገው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የመጨረሻዎቹን 18 ተጫዋቾች አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ ይፋ አድርገዋል። ድረ ገጻችንም የተጫዋቾቹን ሙሉ ስም ዝርዝር ማቅረቡ ይታወሳል። አሰልጣኝ ዮሃንስ በነገው ጨዋታ ሊሰለፉ ይችላሉ ብሎ ይፋ ካደረጋቸው 18 ተጫዋቾች መካከል የቀድሞው ቁጥር አንድ ጀማል ጣሰው በስብስቡ ውስጥ አለመካተቱ ታውቋል።
Jemal Tasew

በመከላከያ ክለብ በቋሚነት ይሰለፍ የነበረው ጀማል ጣሰው በነገው ጨዋታ የማይሰለፍበትን ምክንያት የተጠየቀው ጎልማሳው አሰልጣኝ “ለሁለት ሳምንታት ሊቆይ የሚችል ከባድ ጉዳት እንዳጋጠመው” ዘጋቢያችን ፈለቀ ደምሴ ከባህር ዳር ያደረሰን መረጃ አመልክቷል። የጀማልን አለመኖር ተከትሎ በነገው ጨዋታ የዋልያውን በር ይጠብቃል ተብሎ የሚጠበቀው ወጣቱ የሙገር ሲሚንቶው አቤል ማሞ እንደሚሆን ይገመታል።

ኢትዮፉትቦል ዶትኮም ለሁለቱም ቡድኖች መልካም ጨዋታን እየተመኘ ድል ለዋልያው እንዲሆን ይመኛል።

ይርጋ አበበ
ለኢትዮ ፉትቦል

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
Mule [984 days ago.]
 First of all nooooooo Goal keeper in Ethiopia ! who care Jamal ?! we saw him his kung fu karate man ...... No need this fake keeper ! better we will see youth አቤል ማሞ !!!

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!