ባህር ዳር ስታዲየም ዙሪያ ከፍተኛ ቁጥር ባለው ተመልካች በጠዋቱ እየተጨናነቀ ነው።
ሰኔ 07, 2007

ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ  በኢትዮጵያና በሌሴቶ መካከል በዛሬው እለት የሚደረገው ጨዋታ ለመከታተል ከጠዋቱ 1ሰአት ጀምሮ በርካታ የባህር ዳር ከተማ እና አካባቢዋ ነዋሪ ህዝብ ትኬት ለመግዛት እየጎረፈ ነው። 
long line to buy tickets for the game


የረጃጅም  ሰልፎች በስቴዲየሙ ዙሪያ እይታ የባህርዳርን ድባብ ገና ከጠዋቱ ቀይሮታል። የክልሉ ስፖርት ኮሚሽን ለከተማዋና ለአካባቢው ነዋሪ ህዝብ ጨዋታውን በስታዲየም ተገኝቶ ብሔራዊ ቡድኑን እንዲደግፍ ቅስቀሳ ሲያደርግ መቆየቱ ታውቋል። በሌላ በኩል  በርካታ የኢትዮጵያ እግር ኳስ አፍቃሪው ህብረተሰብ ጨዋታውን ለመከታተል ከተለያዩ ክልሎች ወደ ባህርዳር መግባታቸውን አላቋረጡም ከጎንደር፣ከወሎና ከአዲስ አበባ በባስ እና በአይሮፕላን ወደከተማዋ እየገባ ያለው ተመልካ ዛሬም አላቋረጠም። በርካታ ባሶች በኢትዮጵያ ባንዲራ አሸብርቀው የከተማውን መሃል እያቋረጡ ወደማረፊያቸው ስፍራቸው ሲጓዙ ለከተማዋ ውበትን እያላበሱ ነው። 

50ሺ ሰው ይይዛል ተብሎ የሚታሰበው የባሕር ዳር  እስታዲየም ገና ከጠዋቱ እየጎረፈ ካለው የተመልካች ቁጥር ብዛት ጋር ሲነጻጸር ሁሉንም ተመልካች ለማስተናገድ የሚበቃው አይመስልም። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የትኬት ዋጋ ማስተካከያ ካደረገ በኋላ ለጨዋታው 61ሺ ትኬት አዘጋጅቶ  ወደ ስፍራው መላኩም ታውቋል። 

በስፍራው የሚገኙ ጋዜጠኞች በስታዲየሙ ዙሪያ እየታየ ያለውን ከፍተኛ ጭንቅንቅ ያስከተለውን የሰልፍ መፋረስ በማስታወል ተጨማሪ ስነስርአት አስከባሪዎች ወደስፍራው እንዲመደቡ ለሚመለከታቸው የፌዴሬሽኑ አመራሮች በመጠቆም ወደ ስፍራው በቂ ስነስረአት አስከባሪ እንደሚደብ አድርገዋል። 

ጨዋታው 10ሰአት ላይ ይከናወናል። ኢትዮ ፉትቦል በስፍራው በሚገኘው ዘጋቢያችን ፈለቀ ደምሴ አማካኝነት  የጨዋታውን ድባብ ከባህር ዳር እየተከታተለ በቀጥታ በፎቶ የታገዘ ዘገባ ማቅረባችንን እንቀጥላለን። አዳዲስ ፎቶግራፎችን ለማየት ዋና ገጹን ይጎብኙ። ጨዋታው 10 ሰአት ላይ እንደተጀመረም   የጨዋታውን ውጤት  በቀጥታ ስርጭት የምንዘግብ ስለሚሆን የጨዋታውን ውጤት በኢትዮ ፉትቦል እንድትከታተሉ እንጋብዛለን ።

ፈለቀ ደምሴ 
ለኢትዮ ፉትቦል

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!