ዋሊያዎች በ80ሺህ ህዝብ ድጋፍ በመታገዝ ሌሴቶን 2ለ1 አሸነፉ
ሰኔ 07, 2007

የባህር ዳር ስታዲየም ጢም ብሎ በመሙላት ከ80ሺህ በላይ ህዝብ በመያዝ ለጨዋታው ትልቅ ድባብ ሰጥቶታል። ሰሞኑን ዘንቦ የማያቅ ዝናብም በመዝነብ ህዘቡ ላይ ስጋት ከመፍጠሩም በላይ ደጋፊውን ተፈታትኖታል።
Heavy rain was falling at the stadium

 በመጨረሻው ውጤት በጋቶች ፓኖም እና በሳላዲን ሰይድ ጎሎች አስደሳች ማካካሻ በማግኘቱ የባህር ዳር ስታዲየም በዝማሬና እና በጩኽት ሲንቀለቀል ላየ እጅጉን በጣም አስደሳች ነበር።
Celebration

የኢትዮጵያና የሌሴቶ ጨዋታ ከመጀመሩ በፊት አስገራሚ ክስተት ሙሽሮች ከነልብሳቸው ከአጃቢዎቻቸው ጋር በስታዲየሙ በመታደማቸው አለምሽ ዛሬ ነው ዛሬ ተብሎ ከተመልካቹ አስደሳች አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
Wedding at the stadium

የሌሴቶ አሰልጣኝ ሴቴቴ ማቴቴ ከጨዋታው  በፊት ቡድኔ በአማተር ተጫዋቾች የተገነባ ስለሆነ በጠባብ ልዩነት ልንሸነፍ እንችላለን ለማሸነፍ ግን አስቸጋሪ ቢሆንም የድል ነገር አይታወቅም በማለት መናገራቸውን  የሰሙት አሰልጠኝ ዮሀንስ ሳህሌ ይህ ደካማ የሳይኮሎጂ ጨዋታ ነው። እኛ ምንም ሳያዘናጋን ለማሸነፍ ነው የምንጫወተው በማለት መልስ ሰጥተው ነበር። ይህንንም አሳክተው ወጥተዋል። 

የሌሴቶ ብሄራዊ ቡድን በመጀመሪያው 45 ደቂቃ የጨዋታ ክፍለ  ጊዜ  በ41ኛው ደቂቃ ላይ በ14 ቁጥሩ ቦትኩዋና  አማካኝነት ጨዋታውን እንዲመራ ያስቻለውን ጎል በማስቆጠር በሜዳውና በደጋፊው ፊት የሚጫወተውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጫና ውስጥ ከተውት ነበር። ምንም እንኳን ዝናብ እየጣለ  በሜዳቸው  እየተመሩለነበሩትን ዋለያዎች  ጨዋታውን ከባድ ቢያደርገውም አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ኡመድንና ጌታነህን ከረፍት መልስ ከሜዳ አስወጥተው በምትካቸው ባዬ ገዛሕኝንና ራምኬሎን በማስገባት ወደፊት ተጭነው በመጫወት የማጥቃት ጨዋታውን ጉልበት ሰጥተውታል። የተጫዋቾች ቅያሬውን ተከትሎ  የኢትዮጵያ ቡናው አማካኝ ተጫዋች ጋቶች ፓኖም በ68ኛው ደቂቃ ላይ ከርጎሬ  ሳጥን ውጪ አክርሮ የመታት ኳስ ግብ ሆና በመቆጠርዋ ዝናብ ሲቀጠቅጠው የነበረውን  80ሺህ ህዝብ ስሜቱን መቆጣጠር አቅቶት ወደሜዳ እስከመግባት አድርሶታል። 
Saladin Seid Scored the second goal


ዋሊያዎች አቻ የአደረገቻቸውን ጐል ካስቆጠሩ ከ10 ደቂቃ በኋላ ሳላዲን ሰይድ ሁለተኛውንና የማሸነፊያውን ጎል ግሩም ግብ በማስቆጠሩ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን 2ለ1 እንዲያሸንፍ ረድቶታል። ከጨዋታው በኋላ ለጋዜጠኞች አስተያየታቸውን የሰጡት አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ ባልተጠበቀ ሁኔታ 80ሺ  የሚጠጋ ህዝብ በስታዲየም መገኘቱና ድባቡ በተወሰኑ ልምድ በሌላቸው ተጫዋቾቼ ላይ የተወሰኑ  አለመረጋጋትን ፈጥሮባቸው ነበር ብለዋል።  የሌሴቶ አሰልጣኝ ሴቴቴ ማቴቴ በጨዋታው ማብቂያ ላይ ስለጨዋታው አስተያየት ይሰጣሉ ተብሎ ሲጠበቅ ተጫዋቾቻቸውን ተከትለው ስቴዲየሙን ለቀው  ሄደዋል።

የዛሬውን ጨዋታ በስታዲየሙ ተገኝተው ጨዋታውን ከተከታተሉት ተመልካቾች በተጨማሪ በአዲስ አባባና አካባቢዋ በሚሰራጩ የኤፍ ኤም ራዲዮዎች እንዲሁም በመላው ሀገሪቱ በሚተላለፉ ሬድዮ   ጣቢያዎች ጨዋታው በቀጥታ ሲተላለፍ ነበር። የኢትዮ ፉትቦል ድረ ገጽ ፣የበፌሰቡክ እና ትዊተር ማህበራዊ ገጾችም በሀገር ውስጥና እና በውጪ ለሚገኙ ከ40ሺ በላይ ለሚሆኑ የእግር ኳስ አፍቃሪዎች ጨዋታውን  በቀጥታ ውጤት ስርጭት እንዲሁም ኮሜንታሪና ቀጥታ ፎቶ ዘገባ በማቅረብ    ለኢትዮጵያን እግር ኳስ መስፋፋትና እድገት ኢትዮ ፉትቦል ዶት ኮም የበኩሏን ድርሻ  ተወጥታልች። 

ፈለቀ ደምሴ ከባህር ዳር
ለኢትዮ ፉትቦል


ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
Selam251 [915 days ago.]
 Yemejemeriaew agamash budnachin tiru alneberem. Ke ereft behuala gen ETV eskemiyakarewu yayehut tiru enkesekase new. Gena bezu mesrat yetebekebenal. Beterefe. 80,000 hezeb fit mechawet bertat enji ferhat mwfter yelebetem. Bertu bertu

Selam251 [915 days ago.]
 Yemejemeriaew agamash budnachin tiru alneberem. Ke ereft behuala gen ETV eskemiyakarewu yayehut tiru enkesekase new. Gena bezu mesrat yetebekebenal. Beterefe. 80,000 hezeb fit mechawet bertat enji ferhat mwfter yelebetem. Bertu bertu

pop star [915 days ago.]
 yamerale 2 le 1 ..Glory Glory Waleyas

Melaku [915 days ago.]
 we missed our hero player Adane Girma ! if Adu is there every thing is easy for Waliya ! long live for Aduuuuuuuuuuuuuuuuuu ! aduuuuuuuuuuuuuuuuuu we missed you plssssssssssss come back ?!!!

Mulualem [914 days ago.]
 Wow

kurat [914 days ago.]
 በጣም ደሥ ብሎናል እዚህ ድባይ እምንገኛው ኢትዮጵያውያን ድል ለዋልያ

kurat [914 days ago.]
 በጣም ደሥ ብሎናል እዚህ ድባይ እምንገኛው ኢትዮጵያውያን ድል ለዋልያ

ኩራት [914 days ago.]
 በጣም ደሥ ብሎኛል ከነቤተስቤ እንዲሁም ድባይ እሚገኝ ኢትዮጵያውያን በሙለ እንክዋን ደስ አላቹ መልካም ዕድል ለዋልያ

ROBEL [914 days ago.]
 The scor is good. con tinious!

fitsum tamirat [912 days ago.]
 right team on the right place i like you (bertu bertu bertu)

Garo [912 days ago.]
 the good playing situation started now in Ethiopia. i wish a good luck for our team "WALIYA"

tesfaye mulugeta [912 days ago.]
 betam des blognal,gn gena bzu mesrat ytebekal.bertu bertu,mrt ye Ethiopia egr kuwas budn mehon ychlal.dl lewalyawochu!!!

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!