ኢትዮጵያዊው ያያ ቱሬ
ሰኔ 09, 2007

በዚህ ርዕስ ስር ለመጻፍ ስዘጋጅ “ገና ምኑ ተይዞ ነው ይህንን ያህል ማንቆለጳጰስ? ልጁን ሊያጠፋው ነው እንዴ?” የሚል ሃሳብ በአንባቢያን ላይ ሊነሳ ይችላል። ነገር ግን በአንድ ነገር አምናለሁ “የሚሰራን ሰው ለማበረታታት የሚመዘንበትን ኪሎ መጨመር ይገባል” ብዬ። ለዚህም ነው የዛሬውን የዝግጅት ክፍላችን ተስፈኛ ወጣት “ኢትዮጵያዊው ያያ ቱሬ” ብዬ እንድገልጸው የተነሳሳሁት። ወደ ፊት ተጫዋቹን ቃለ መጠይቅ በማድረግ ሰፊ ዳሰሳ የምናቀርብ መሆኑን እየገለጽን ለዛሬው ግን በርካታ እግር ኳስ አፍቃሪያን ስለ “ጋቶች ፓኖም የምታውቁትን አካፍሉን” ብለው በጠየቁን መሰረት ከክለቡ ያገኘነውን መረጃ ከዚህ በታች በአጭሩ አቅርበነዋል መልካም ንባብ።
Gatoch panom Number 19

ትውልድ እና ወደ ቡና ጉዞ

ትውልድ እና እድገቱ ጋምቤላ ክልል ጋምቤላ ከተማ ነው። በጋምቤላ ታዳጊ ፕሮጄክት ተጫውቶ ያደገ ሲሆን የአሁኑን ክለቡን ኢትዮጵያ ቡናን የተቀላቀለው በ2004 ዓ.ም ዝዋይ ላይ ተካሂዶ በነበረው የክልሎች ውድድር ላይ በአሰልጣኝ ስዩም አባተ መልማይነት ነበር። በወቅቱ ክለቡን ሲቀላቀል ከክልሉ ልጅና አብሮ አደግ ጓደኛው ቶክ ጀምስ ጋር ሲሆን በቀጥታ ዋናውን ቡድን አልተቀላቀሉም። ከቡና ጋር ባሳለፈው የመጀመሪያ ዓመት ቆይታው መጫወት የቻለው ለተስፋ ቡድን ሲሆን በቀጣዩ ዓመት ግን አሰልጣኝ ጸጋዬ ኪዳነማሪያም በልጁ ላይ ከፍተኛ እምነት በማሳደራቸው “በቢጫ ቴሴራ” ዋናውን ቡድን መቀላቀል ቻለ። ቢጫ ቴሴራ ማለት ተጫዋቹ ለአሳዳጊ ክለቡ ለሶስት ዓመታት የሚያቆየውን ስምምነት የሚያደርግበት አስገዳጅ ውል ነው።

የቢጫ ቴሴራ ውሉን በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ ያጠናቀቀው ወጣቱ የጋምቤላ ፍሬ በውድድር ዓመቱ መባቻ ከክለቡ ጋር የሚያቆየውን አዲስ የሶስት ዓመታት ኮንትራት ተፈራርሟል። በአዲሱ ኮንትራቱም ለፊርማ ሰባት መቶ ሺህ ብር የተከፈለው መሆኑን የሚገልጸው የክለቡ መረጃ ኢትዮጵያ ቡና ለተጫዋቾች በሚከፍለው የደመወዝ አከፋፈል ስርዓት መሰረትም የመጀመሪያ ተከፋል ከሚባሉት የቡድኑ ተጫዋቾች አንዱ ጋቶች መሆኑን ይገልጻል። ይህም ማለት በወር የ3500 ብር ተከፋይ ነው ማለት ነው። አዲሱ ኮንትራቱ የሚጠናቀቀው በ2009 ዓ.ም መሆኑንም ከክለቡ ያገኘነው መረጃ አመልክቷል።

 

ባህሪ

በርካታ እግር ኳስ ተጫዋቾች ተፈጥሯዊ ባህሪያቸው ተፈጥሯዊ ችሎታቸውን ይሸፍንባቸውና ማበብ ሳይጀምሩ በእምቡጡ ይቀራሉ። በዚህ በኩል የጋቶች ፓኖም ግላዊ ባህሪ ምን እንደሚመስል ለማወቅ ባደረግነው ጥረት ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው ከቡድን አጋሮቹ ጋር ተስማሚ ሲሆን በስራ ላይ ቀልድ የሚባል ነገር አያውቅም። የልምምድ ሰዓት ከማክበር ጀምሮ በአጠቃላይ እግር ኳስ የሚፈልገውን ፕሮፌሽናሊዝም ባህሪ ያሟላ ተጫዋች መሆኑን የክለቡ የህዝብ ግንኙነት ክፍል ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ ደሳለኝ ለኢትዮፉትቦል ዶትኮም በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ ከሜዳ ውጭም ቢሆን ለአጉል መጥፎ ባህሪያት ያልተጋለጠ መሆኑን የሚናገሩት አቶ ሙሉጌታ ቀደም ባሉት ጊዜያት ግን ጨዋታ ላይ ስሜታዊነት ይፈታተነው እንደነበረ ከመናገር አልተቆጠቡም። ይህ ግልፍተኛነት ባህሪውም በዚህ ዓመት ክለቡ ከአርባ ምንጭ ከነማ ጋር ሲጫወት በቀይ ካርድ ከሜዳ እንዲወጣ አድርጎት እንደነበረም ይታወሳል። በአጠቃላይ ግን በስራው ላይ ብቻ ሙሉ ትኩረት አድርጎ የሚሰራ ተጫዋች መሆኑን ነው አቶ ሙሉጌታ ለዝግጅት ክፍላችን በስልክ የገለጹልን። ለዚህም በዚህ የውድድር ዓመት አብዛኛውን ጊዜ በተለይም በውድድር ዓመቱ የመጨረሻ ሳምንታት ቡድኑን በአምበልነት በመምራት ገና በወጣትነቱ ኃላፊነትን መወጣት የቻለ እንደሆነ አቶ ሙሉጌታ ተናግረዋል።

ጋቶች በብሔራዊ ቡድን


ገና ከ17 ዓመት በታች ባለው ብሔራዊ ቡድን ጀምሮ መጫወት የቻለው ጋቶች በሴካፋ ውድድርም አገሩን ወክሎ መጫወት ችሏል። ለተወሰነ ጊዜ ከብሔራዊ ቡድን ምርጫ ውጭ ሆኖ የቆየ ቢሆንም በአሰልጣኝ ማሪያኖ ባሬቶ እና ዮሃንስ ሳህሌ አማካኝነት እንደገና አገራዊ ጥሪ ቀርቦለታል። በተለይ በዮሃንስ ሳህሌ የመሚመራው የዋልያዎቹ ስብስብ የመሃል ሜዳውን ማገር በወጣቱ ጋቶች ፓኖም ላይ የመሰረተ መስሏል።
Gatoch Panom

ለብሔራዊ ቡድኑ መጫወት ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ከትናንት በስቲያ ለመጀመሪያ ጊዜ ኳስና መረብን ማገናኘት የቻለ ሲሆን በተለይ ያስቆጠራት ጎል ልጁ ወደ ፊት ብሩህ ጊዜያት እንደሚጠብቁት ምልክት የሰጠች ነበረች ተብሎላታል። ተጫዋቹን በስልክ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ስላልተሳካ በጎሏ የተሰማውን ስሜት በዚህ ጽሁፍ ማካተት አልቻልንም።

ከላይ የተጠቀሱትን ጠንካራ ጎኖቹን ስንመለከትም ይህ ልጅ ወደ ፊት ጠንክሮ ከሰራ ኢትዮጵያዊው ያያ ቱሬ የማይሆንበት ምክንያት የለም ብለን እናስባለን። ለዚህም የጋቶች ተስፋ ሰጭ እንቅስቃሴ ለክለቡ ኢትዮጵያ ቡናም ሆነ ለአገሩ የሚኖረው የወደፊት ወሳኝነት የጎላ መሆኑን መገመት አይከብድም።

ልክ እንደ ጋቶች ሁሉ በርካታ ወጣት ተጫዋቾች በየክልሉና እና በአዲስ አበባ የተለያዩ ሜዳዎች ላይ ይገኛሉ። እነዚህ ተጫዋቾች ከያሉበት ፈልጎ ማግኘትና የጨዋታ እድል መስጠት ደግሞ በእግር ኳሱ ላይ እንጀራ የሚቆርሱ ባለሙያዎችም ሆኑ የጋዜጠኞች ድርሻ ነውና ሁሉም ድርሻውን ይወጣ። በጋቶች የእግር ኳስ ህይወት ላይ ግን አንጋፋው አሰልጣኝ ስዩም አባተ ትልቁን የመሰረት ድንጋይ የጣሉ አሰልጣኝ ናቸውና ወጣት አሰልጣኞች የስዩምን መንገድ ተከትላችሁ የጋቶችን ታናናሾች አድናችሁ ያዙ።

በይርጋ አበበ
ለኢትዮ ፉትቦል

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
Gizegeta [948 days ago.]
  ጋቶች ፓኖም if he want be come professional player this is the time to leave unprofessional backward amater club. no need to stay with this club. wake up ጋቶች ፓኖም goooooo another club !

Babi [948 days ago.]
  i agreed by Gizegeta comment. now ጋቶች ፓኖም class is high thats why go dedebit, Bank,Dasheen or ELPA

jaimi [948 days ago.]
  @ Ethiosport:- sel leju betam tegano new yekerebew. leju 1 goal agebeto yehen hulu were maweratachu fare aydelem. we will see him .....

Tesfesh G/Mariyam [948 days ago.]
  Gacho good player 2008 be Dedebit maliya enayewalen aykerem.

Hana [948 days ago.]
 Gatoch has been playing Great club ,Great Fan i.e Ethiopia Buna !!!! He is proud of being buna player . Buna is the best club in Ethiopia .

Yoni [947 days ago.]
 @ Hana....you are very funny ! dont lie your self ! what you said ? " Bulla Gellebba is best club in Ethiopia " ha ha ha ha i can not stop laughing .... we know Bulla Gellebba adegegne new ....be Sedeb.......be Dengay Werwera.....be Service sebera.....ha ha ha ! be 13 amet 1 gize champion yemihon team eydegefesh Bulla Gellebba best club in Ethiopia seteyi ataferime ?!!! dont worry ጋቶች ፓኖም soon he will show you which one is best club in Ethiopia ! ha ha ha ha

samifelex [947 days ago.]
 ጋቶች ፓኖም ምን እዳ አለበት እዚህ ሲኦል የሆነ ተራ አልቧልተኛ ክለብ የሚቆየው እስከዛሬም ድረስ ችሏቸው መቆየቱ ይገርማል ! ልጁ የባነነ ነው ምን ማድረግ እንዳለበት ያውቃል ! ወርቃማ ጊዜውን በደስታ በፌሽታ በዋንጫ ማድመቅ ይፈልጋል አማተር በሆነ ተራ ቲም ውስጥ እድሜውን መፕፍጀት አይፈልግም እነ ሳላሃዲን... ሽመልስ..... ኡመድ ..... አበባው .... አዲስ ..... ጌታነህ ...... የት የት ክለብ ተጫውተው ፕሮፌሽናል እንደሆኑ ይገባዋል ያውቀዋልም ! በጓደኛው ቶክ ጀምስ ላይም Bulla Gellebba ያደረሰበትን ግፍ አይረሳውም ! ጋቶች ፓኖም ቶሎ ብለህ አምልጥ ከዚህ ሲኦል ከሆን ክለብ !

Mule [947 days ago.]
 ጋቶች ፓኖም Yasazenal arief techawache new gin metefo club west new yemichawetew. Dedebit or St.George fc bigebba 100% sure professional techawache yehonale ! ጋቶች ፓኖም neka bel !

Mule [947 days ago.]
 @ ላሲ :- ልጁን የሚጠቅም ነገር እኮ ነው የተናገርነው ምን ክፋት ተናገርን ? ልጁ ትልቅ ደረጃ ላይ እንዲደርስ ለብሔራዊ ቡድናችንም ወሳኝ ተጫዋች እንዲሆን ጊዜው አሁን ነው ወደ ትልቅ ክለብ የሚሄድበት ምክንያቱም አሁን ልጁ ክላስ ያለው ተጫዋች እየሆነ ስለሆነ ክላስ ያለው ክለብ ውስጥ ማለትም ኢንተርናሽናል መድረክ ላይ የሚሳተፉ ክለቦች ውስጥ ቢገባ ፕሮፌሽናል ተጫዋች የመሆን እድሉም more ይሰፋል !

samifelex [947 days ago.]
  @ ላሲ ፕሮፌሽናል ያልሆነ ሰላም የሌለው ተራ ቲም ክለብ ውስጥ እድሜውን መፍጀት አይፈልግም እነ ሳላሃዲን .... ሽመልስ ..... ኡመድ .... አበባው ...... አዲስ ..... ጌታነህ ....... የት የት ክለብ ተጫውተው ፕሮፌሽናል እንደሆኑ አይቶታል ! thats all no doubet.

TG [947 days ago.]
  Tnx ethio sport arief zegeba new bertu. ጋቶች ፓኖም ye wedefitu ye waliya tesfa new. but he is playing in poor club Ethiopia coffee.

AMAHA AMBACHEW [855 days ago.]
 ጋቶች ምርጥ የኢትዮጵያ ልጅ ነው ።ግን ቅዱስ ጊዎርጊስ ቢጫወት ደስይላል ye hagere lij gatoch

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!