ዋልያዎቹ እሁድ ከኬንያ ጋር ለሚጠብቃቸው ጨዋታ ዛሬ ልምምዳቸውን ይጀምራሉ
ሰኔ 10, 2007

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ባለፈው እሁድ የሌሴቶ አቻውን ሁለት ለአንድ ካሸነፈ በኋላ የፊታችን እሁድ ደግሞ የጎረቤት አገር የኬኒያን ብሔራዊ ቡድን ለቻን ዋንጫ ማጣሪያ በባህር ዳር ስታዲየም  ያስተናግዳል።የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ወንድምኩን አላዩ ለዝግጅት ክፍላችን በስልክ እንዳስታወቁት የኬኒያ ብሔራዊ ቡድን የፊታችን እሁድ ከቀኑ ስምንት ሰዓት አዲስ አበባ ይገባ እና በዛው እለት ወደ ባህር ዳር በማምራት ለእሁዱ ጨዋታ ይዘጋጃል። የኬኒያ ብሔራዊ ቡድን እሁድ ከተጫወተ በኋላ በማግስቱ ሰኞ ወደ አገሩ የሚመለስ ይሆናል።

Walya


በዋልያዎቹ በኩል እስከ ዛሬ ድረስ ልምምድ እንዳልጀመሩ ያስታወቁት አቶ ወንድምኩን በቡድኑ ውስጥ የተጎዳ ተጫዋች መኖርና አለመኖሩን ዛር ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት በሚኖረው ልምድ እንደሚታወቅ ገልጸዋል። ከዚህ በተረፈ በቡድኑ ተጫዋቾች መካከል የማሸነፍ መንፈስ እንደሰፈነ ተናግረዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በባህር ዳር ጨዋታውን እያካሄደ ያለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከከተማው ነዋሪዎች ከፍተኛ አቀባበልና መልካም የእንግዳ አቀባበል እየተደረገለት መሆኑን ከባህር ዳር የደረሰን መረጃ አመልክቷል። ብሔራዊ ቡድኑ የሌሴቶ አቻውን በጋቶች ፓኖም እና ሳላሃዲን ሰይድ ጎሎች ሁለት ለአንድ ካሸነፈ በኋላ በተለይ በከተማው ነዋሪ ከፍተኛ መነቃቃት መፈጠሩን ዝግጅት ክፍላችን ያነጋገራቸው የከተማው ነዋዎች አስታውቀዋል። በእሁዱ ጨዋታም የተለመደው ጨዋና የአገር ፍቅር የተሞላበት ድጋፋቸውን እንደሚሰጡ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለአራተኛው የቻን ዋንጫ ለማለፍ ከኬኒያ አቻው ጋር በደርሶ መልስ የሚያስመዘግበው ውጤት ይወስነዋል። ብሄራዊ ቡድኑ በቻን ውድድር ለመጀመሪያ ጊዜ የተሳተፈው ከሁለት ዓመት በፊት በአሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው እየተመራ የሩዋንዳ አቻውን በደርሶ መልስ አንድ እኩል ተለያይቶ በመለያ ምት በማሸነፍ ነበር። 

ይርጋ አበበ
ለኢትዮ ፉትቦል

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
tedros fikadu [980 days ago.]
 melkam dil

Tesfahun [980 days ago.]
 Lemin komo new zare limimid yemijemerew? training eko ehud akumehew arb yemitasnesaw mekina ayidelem. please follow z training principles!!!!!!!!

Garo [979 days ago.]
 min gizem waliya dil le "WALIYAWOCHU"

Abebe [979 days ago.]
 wodachiwalehu

Desalegn Getaye [977 days ago.]
 በጣም ያስደስታል!

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!