ብሔራዊ ቡድኑ ዑመድ ኡክሪን በእሁዱ ጨዋታ የመጠቀም እድል አለው
ሰኔ 11, 2007

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የፊታችን እሁድ ከኬኒያ ብሔራዊ ቡድን ጋር ለቻን ዋንጫ ማጣሪያ ዝግጅት እያደረገ መሆኑ ይታወቃል። የቻን ውድድር የአፍሪካ እግር ኳስ ማህበር የአህጉሩን እግር ኳስ ለማሳደግ በአገር ውስጥ ሊጎች ብቻ በሚጫወቱ ተጫዋቾች መካከል የሚካሄድ የአገራት ውድድር ነው። በዚህ ውድድር ለመሳተፍ ዝግጅት ላይ ያለው ብሔራዊ ቡድናችን የኬኒያ አቻውን ባህር ዳር ላይ እና በኬኒያ ለሚያደርገው የደርሶ መልስ ጨዋታ 24 ተጫዋቾችን ይዞ ልምምድ እየሰራ ይገኛል። ነገር ግን ብሔራዊ ቡድኑን ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከተቀላቀሉት ተጫዋቾች መካከል ለግብጹ አሌክሳንድሪያ ሲጫወት የቆየውና ከወርሃዊ ደመወዝ ጋር በተያያዘ ውዝግብ ላይ የቆየው ዑመድ ኡክሪ ይገኝበታል።
Oumed Okri

ዑመድ ኡክሪ ከግብጹ ክለብ ጋር ያለውን አለመግባባት ወደ ፊፋ ይዞ በመቅረቡ እና ተጫዋቹን ለመጠቀም ፍላጎት ያለው ቅዱ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ ከፊፋ ጋር ባደረጉት ውይይት ተጫዋቹ ከግብጹ ክለብ ጋር ያለውን ውል እንዲያቋርጥ መደረጉን ከቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ከቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ በደረሰን መረጃ መሰረት ዑመድ ኡክሪ አሁን ወደ ፈለገው ክለብ መዘዋወር የሚችል ተጫዋች  ነው።  ተጫዋቹ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ በግል ተወያይተው ስምምነት ላይ መድረስ ከቻሉ የፈረሰኞቹ ንብረት ይሆናል።

በዚህም መሰረት ብሔራዊ ቡድኑ ከኬኒያ ጋር ለሚያደርገው የቻን ውድድር ማጣሪያ ተጫዋቹን መጠቀም ከፈለገ ከግብጹ ክለብ ነጻ መሆኑን የሚያረጋግጥ ደብዳቤ ከፊፋ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስለደረሰው ተጫዋቹን በእሁዱ ጨዋታ መጠቀም ይችላል ማለት ነው።  በዚህ ዙሪያ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን መረጃ ለማግኘት ሞክረን ያልተሳካልን ሲሆን በቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ በኩል ከክለቡ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ኤርሚያስ አሽኔ ጋር ባደረግነው የስልክ ቃለ ምልልስ ግን “ተጫዋቹን መጠቀም እንደምንችል ከፊፋ ግልባጭ ደብዳቤ ደርሶናል። የፊፋ ደብዳቤ ለፌዴሬሽኑም ደርሶታል። በጨዋታው ለመጠቀም አስመዝግቦ ከሆነ በእሁዱ ጨዋታ ለብሔራዊ ቡድኑ መሰለፍ ይችላል” ሲሉ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአሁኑ ሰዓት ጉዳት ላይ ከሚገኘው ጀማል ጣሰው ውጭ 23 ተጫዋቾችን ይዞ ልምምድ እየሰራ ሲሆን በቅርቡ በወጡ መረጃዎች እንደሚያሳየው ደግሞ አማካዩ እና በእሁዱ ጨዋታ አምበል ይሆናል ተብሎ የሚጠበቀው በሀይሉ አሰፋ ጉዳት ደርሶበታል ተብሏል።  በብሔራዊ ቡድኑ ዙሪያ የሚወጡ ወቅታዊ መረጃዎችን እንዳገኘን የምናቀርብ ይሆናል። የአጥቂ ችግር እንዳለበት የሚነገርበት ብሔራዊ ቡድናችን የኡመድ ኡክሪን ጉዳይ በፍጥነት ተከታትሎ አንድ ውሳኔ ላይ መድረስ የሚችል ይመስለናል።

ይርጋ አበበ
ለኢትዮ ፉትቦል

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
Mule V [979 days ago.]
 Oumed Oukri merebe wetari meret jegenna yehon striker new ! we can not forget Umed goal St.George with Zamalik ! Umecha Oumed Oukri our heroooooo

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!