በእሁዱ ጨዋታ የስታዲየም መግቢያ ዋጋ ካለፈው ሳምንት ልዩነት የለም ተባለ
ሰኔ 12, 2007

የፊታችን እሁድ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከኬኒያ አቻው ጋር በሚያደርጉት ጨዋታ የስታዲየም መግቢያ ዋጋ ባለፈው እሁድ ከነበረው የተለየ እንዳልሆነ ተገለጸ። ከአማራ መገናኛ ብዙሃን በደረሰን መረጃ መሰረት ጨዋታውን በስታዲየም ተገኝተው መመልከት የሚፈልጉ እግር ኳስ አፍቃሪያን የመግቢያ ዋጋው ያልተቀየረ መሆኑን እንዲያውቁት ተገልጿል። በዚህም መሰረት የመጨረሻ ዝቅተኛ ክፍያው አስር ብር ሲሆን ቀጣዮቹ ሃያ ሃምሳ መቶ ሁለት መቶ እና ሰባት መቶ ብር ናቸው።
Bahir Dar Ticket

ባለፈው እሁድ ተካሂዶ በነበረው ጨዋታ ስታዲየም ለመግባት በነበረው ትርምስ በርካታ ደጋፊዎች በቆረጡት ቲኬት ማስተናገድ ያልተቻለ መሆኑን ከክልሉ የደረሰን መረጃ አመልክቷል። የክልሉ ስርዓት አስከባሪ አካላትና የውድድር ኮሚቴዎች በቀጣዩ ጨዋታ ያለፈው ስህተት እንዳይደገምና ተመልካቾች በቆረጡት ቲኬት ዋጋ ቦታቸውን ይዘው እንዲከታተሉና ተገቢውን ስፖርታዊ ጨዋነት እንዲያሰፍኑ መልዕክት ተላልፏል። ዋልያዎቹና ሌሴቶ ሲጫወቱ አስር ብር ከፍለው ቲኬት የቆረጡ እና 700 ብር ከፍለው ቲኬት የቆረጡ ተመልካቾች በአንድ በር ገብተው ጨዋታ እንደተከታተሉ ሰምተናል።

በተያያዘ ዜና ባለፈው እሁድ በተካሄደው ጨዋታ ጋቶች ፓኖም ጎል ሲያገባ ስታዲየም የገቡ ተመልካቾች ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ ተገልጿል። ምክንያቱም ድርጊቱ የሚደገም ከሆነ ጨዋታውን የሚመሩ ኮሚሽነሮች በአገራችን ላይ የነጥብ ቅነሳ እንዲወሰን ከማድረጋቸውም በላይ ስታዲየሙ ሌላ ኢንተርናሽናል ጨዋታ እንዳያካሂድ ሊታገድ ሁሉ ይችላልና ነው። ተመልካቾችም ካለፈው ስህተታቸው ታርመው በቀጣዮቹ ጨዋታዎች ቡድናቸው ሲያገባ ደስታቸውን በጨዋነት መግለጽና ሲገባበትም ተስፋ እንዳይቆርጥ ማበረታታት እንጅ የስታዲየም አጥር ዘሎ መግባት ስፖርታዊ ጨዋነት አይደለም። በዚህ ዙሪያ ጥያቄ ያቀረብንላቸው የአማራ ክልል ስፖርት ኮሚሽነር አቶ ያየህ “የተፈጠረው ስህተት ከግንዛቤ ማነስ እንጅ ሆን ተብሎ ጨዋታን ለመረበሽና ተጋጣሚን ለማወክ አይደለም። ከዚህ በኋላ ድርጊቱ እንዳይደገምም በመገናኛ ብዙሃን መግለጫ አውጥተናል” ብለዋል።

ይርጋ አበበ
ለኢትዮ ፉትቦል

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
Mamush [979 days ago.]
 shame on you Ethiopia foot ball federation Dictator Junedin . only know collecting money nothing doing ... nothing knowing.

Yaredo [979 days ago.]
 coach Yohanes give chance for great player Mintesinot Adane ! his great super star midifilder and scorers !

MAHLET [977 days ago.]
 LOVE

KIBROM [976 days ago.]
 BETAM TEDESCHALEW GIN BE TV METAYET NEBEREBET YEBELET ENDIDESET . 10Q

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!