ዛሬ ከኬንያ ጋር ለሚደረገው ጨዋታ 11ንዱን ቋሚ ተሰላፊ ተጫዋቾች አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ አሳወቁ
ሰኔ 14, 2007

ዛሬ ጠዋት ባህርዳር ላይ 18ንቱት ተጫዋቾች በማስከተል ለጋዜጠኞች የዛሬውን ከኬንያ ጋር ለሚደረገው ጨዋታ የሚከተሉትን አጨዋወት  በተመለከተ አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ መብራሪያ ሰጥተዋል።  4-4-2  አሰላለፍ እንደሚኖራቸውና  ለዛሬው ጨዋታ የሚጠቀሙዋቸውን 11ንድ ተጫዋቾች አሳውቀዋል። 
bahir dare

የ11ንዱ ተጫዋቾች ዝርዝር እንደሚከተለው ነው፦

በረኛ
1. ታሪክ ጌትነት     
 
ተከላካዮች
2. ስዩም ተስፋዬ         
3. አስቻለው ታመነ          
4. ተካልኝ ደጀኔ              
5. ሳላዲን ቤርጊቾ     

 
የመሀል ሜዳ አማካኝ ተጫዋቾች

6. ጋቶች ፖኖም           
7. ምንተስኖት አዳነ     
8. በኃይሉ አሰፋ                  
9. አስቻለው ግርማ

አጥቂዎች
10. ራምኬል ሎክ            
11. ቢኒያም አሰፋ       

በሌላ በኩል ባህር ዳር ከተማ እና ስታዲየም ዙሪያ ባለፈው ሳምንት የነበረው የተመልካች ድባብ ቀንሷል። ይኽም የሆነበት ምክንያት በቂ ቅስቀሳ ባለመደረጉ ይመስላል። በስታዲዮሙ ዙሪያ ከተሰባሰበው ተመልካች ቁጥር ይልቅ የነጋዴው ቁጥር በዝቶ ታይቷል። በዚህ በኩል በስፍራው በመገኘት ያየነውን ሁኔታ ለፌዴሬሽኑ ባለስልጣናት ነግረናል። ከክልሉ ስፖርት ኮሚሽን ጋር በመነጋገር በቀሪው ሰአት ቅስቀሳ  እንዲደረግ እንደሚያደርጉ እንጠብቃለን።  

ፈለቀ ደምሴ ከባህር ዳር 
ለኢትዮ ፉትቦል

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
Dejen [976 days ago.]
 Zarie mashenef alebachew. Bertu merejachihu eyederesen new. Kechalachihu email adirgu. Good luck!

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!