የዋሊያዎቹ ሁለተኛ ድል በባህርዳር እስቴዲየም
ሰኔ 16, 2007

በ2016 ላይ ሩዋንዳ ላይ ለሚደረገው የሀገር ውስጥ ሊግ ተጫዋቾችን ብቻ የሚያካትተው የቻን ውድድር ከኬንያ አቻው ጋር የመጀመሪያ የማጣሪያ ጨዋታውን ያደረገው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሙሉ የጫወታ ብልጫ ጋር በአስቻለው ግርማ እና በጋቶም ፓኖም ጎሎች 2ለ0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ በባህርዳር ስቴዲየም ሁለተኛ ድሉን አስመዝገቧል።

ሰኔ 7 ቀን 2007 አ/ም ባለፈው ሳምንት ከሌሴቶ አቻው ጋር ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በባህርዳር ስቴዲየም ሲያከናውን ከረፍት በፊ ት ብለጫ ተውሰደበት የዋለያዎቹ ስብስብ በኬኒው ግጥሚያ ጨዋታው ከተጀመረበት ደቂቃ ጀምሮ ቁጭ ብድግ ባሰኘ አጭር ቅብብል በተደጋጋሚ ተጋጣሚውን ሲያስጨንቅ የነበረ ሲሆን  በመልሶ ማጥቃት በመጠቀም የኬንያ አጥቂዎች 21ኛው ደቂቃ ላይ በግሩም አስተላለፍ ወደግብ የላኳት ኳስ ወደመረብ ተቀላቀልች ሲባል አስቻለው ታመነ ደርሶ አድኗታል። 22ኛው ደቂቃ ላይ በቀኝ ክንፍ በሃይሉ አሰፋ ቱሳ ለራምኬሎ ኬሎ ያቀበለውን ራምኬሎ ፍጹም ቅጣት ምት ውስጥ ይገኝ ለነበረው ቢኒያም አሰፋ በግሩም ሁኔታ ያሻገረለትን ቢኒያም ወደጎል የላካትን ኳስ ገበች ተብሎ ሲጠበቅ በረኛው ተደርቦ ቢያወጣትም አስቻለው ግርማ  በሚገርም ፍጥነት ደርሶ ወደጎል ቀይሯታል።  

በ34ኛው ደቂቃ ፍሬው ሰለሞን ምንተስኖት አዳነን ቀይሮ ገብቷል። ከረፍት መልስ እስከ 75ኛው ደቂቃ ያለግብ በዋሊያዎቹ የጨዋታ የበላይነት የቀጠለው ጨዋታ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የተሰጠውን ፍጹም ቅጣት ምት ጋቶች ፓኖም አስቆጥሮ  የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለሁለተኛ ጊዜ አስተናግዶ ውጤታማ ለሆነው ግዙፉ የባህር ዳር ስታዲየም ድምቀትን አጎናጽፎታል። 79ኛው ደቂቃ ላይ ኬንያዎች  በመልሶ ማጥቃት ጨዋታ ያገኙትን ፍጹም ቅጣት ምት 17 ቁጥሩ ኬቨሊን ኩማኒ በቀኝ በኩል ወደግብ ቢልካትም በማይታመን ሁኔታ የዋሊያዎቹ ግብ ጠባቂ ታሪክ ጌትነት ተወርውሮ አድኗታል።
Tarik tnet Saved Penalty


የጨዋታው መጠናቀቅ የዳኛው ፊሽካ ሲያበስር በስቴዲየሙ የተገኘው ተመልካች ጭፈራና ዝማሬ በጣም የሚማርክ ነበር።

ባለፈው ሳምንት በተሰጡ አስተያየቶች ምክናይት ይመስላል በጥበቃ በኩል ከፍተኛ መሻሻል ታይቷል። በትኬት አሻሻጥም በኩል ካለፈው ሳምንት በተሻለ ሰላማዊና የተረጋጋ በመሆኑ ተመልካቹ ያለግርግርና እና ያለወከባ እንዲስተናገድ  ተደርጓል አነዳንድ ፀጥታ አስከባሪዎች ይውስዱት የነበረው ከልክ ያለፈ የሀይል አጠቃቀም ለወደፊቱ በሀላፊዎቹ በኩል ታይቶ ቢታረም ጥሩ ነው። በለቱ የነበረው  ቅንጅት ከሞላ ጎደል የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ተሳክቶለታል ማለት ይቻላል።

ከጨዋታው በኋላ የቡድኑ መሪ እና የፌዴሽኑ የስራ አስፈጻሚ አባል አቶ ዮሴፍ ተስፋዬ የነበሩብንን ችግሮች ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በመነጋገር ቀርፈናል። ለተጫዋቾቻችን ማክሰኞ አዲስ አበባ ላይ ቃል የተገባንላቸውን ሽልማት እንሰጣለን።  አሮብ ወደ አዋሳ ገብተን ለመልሱ ጨዋታ ልምምድ  ስለምንጀምር ከሰኔ 18 ጀምሮ ለሚደረግ ጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ተጫዋቾች ወደየክለባቸው በመሄድ   ጨዋታቸውን እንደጠናቀቁ ወደብሔራዊ ቡድኑ ተመልሰው ይቀላቀላሉ በማለት ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው  ጥያቄ መልስ ሰጥተዋል።  እዚህ ላይ አቶ ዮሴፍ ተስፋዬ  በተከታታይ በሚሰጡ ጋዜጣዊ መግለጫዎች ላይ የሚሰጡት መልስ አሳማኝ ጥሩ እና ቀናነት ያለው በመሆኑ ምሰጋና ይገባቸዋል ።

ዋና አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ ከጨዋታው በኋላ እንደተናገሩት እኛ የተሻልን ስለነበርን አሸንፈናል። እንታማበት የነበረውን ክፍተቶች አስተካክለናል። ቅንጅት የለውም ክፍተት አለው የሚባሉት ነገሮችን በማስተካከል በብዛት የጎል እድሎችን ሞክረን ከተቃራኒው ቡድን የተሻልንም ስለነበርን አሸንፈን ወጥተናል። ለወደፊቱ የበለጠ የተሻለ ቡድን ለመስራት ሌሎች ልጆችንም እያየን እንመርጣለን። አካል ብቃትን በተመለከተ ከኬንያዎች የተሻልን ነበርን። የኬንያ ቡድንን በተመለከተ የተለያዩ መረጃዎችን የሰጡን ጋዜጠኞች እናመሰግናለን።  ተካልኝና አስቻለውን ለመጀመሪያ ጊዜ አሰልፈን አመርቂ ውጤት አግኝተንባቸዋል። በመልሱ ጨዋታ  እንደ አዲስ ጨዋታ ተዘጋጅተን ውጤቱን ለማስጠበቅ እንጫወታለን በማለት ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄዎች መልስ ሰጥተዋል።

 በሌላ በኩል የኬንያው አሰልጣኝ ቦብ ዊሊያምስ የባህርዳር እሰቴዲየም ታደሚ ድጋፍ አስጣጥ እና የተመልካቹ ቁጥር መብዛት በጣም ልዩ ነበር በማልት  በመልሱ ጨዋታ ውጤቱን እንቀለብሰዋለን ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!