ዋሊያዎቹ ዛሬ ማምሻውን በካፒታል ሆቴል በተደረገ ስነስርአት የገንዘብ ሽልማት ተበረከተላቸው
ሰኔ 16, 2007

ዋሊያዎቹ በእግር ኳስ ፌዴሬሽኑ ቃል ተገብቶላቸው የነበረውን  የገንዘብ ሽልማት አገኙ። የገንዘብ ሽልማቱ አሰጣጥ ስነስርአት ዛሬ ማምሻውን በካፒታል ሆቴል ተከናውኗል። የገንዘብ ሽልማቱ በየደረጃው የተሰጠ ሲሆን ላቅ ያለውን የ25ሺ ብር ሽልማት የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ አግኝተዋል።

Walya Award Cermony


ም/አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ 15 ሺ፣
የበረኛ አሰልጣኝ አሊ ረዲ 10ሺ፣

በብሔራዊ ቡድኑ በተጫዋችነት ለተካተቱ ተጫዋቾች የተሰጠው የገንዘብ ሽልማት ከፍተኛው 20ሺ ዝቅተኛው 7ሺ  ሆኗል። ከ90 ደቂቃ በላይ የተጫወቱ ተጫዋቾች 20ሺ ብር ሲያገኙ፣ ከ45 እስከ 90ደቂቃ የተጫወቱ ተጫዋቾች 15ሺ ብር አግኝተዋል፣ ከ45ደቂቃ በታች ለተጫወቱ ተጫዋቾች 10ሺ ብር እንዲሁም በተጠባባቂነት ለተመረጡ ተጫዋቾች ለእያንዳንዳቸው 7ሺ ብር  ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
 
የገንዘብ ሽልማቱ ቡድኑን በተለያየ ሁኔታ አብረው ሲያግዙ የቆዩ የቡድኑ አባላትን ያካተተ ነበር በዚሁም መሰረት፦

የቡድኑ ሀኪም  ዶር አያሌው ጥላሁን 7ሺ፣
የቡድኑ ወጌሻ በሃይሉ አበራ 6ሺ፣
የቡድን መሪው አቶ ዮሴፍ ተስፋዬ 10ሺ፣
የትጥቅ ያዢ አቶ ዳንኤል 2ሺ፣
የቡድኑ ሹፌር አቶ ዘውዱ የ2ሺ ብር የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

በሽልማቱ ስነስርአት ላይ ለየት ያለ ክስተት የነበረው በፌዴሬሽኑ የ10ሺ ብር ተሸላሚ የነበሩት አቶ ዮሴፍ ተስፋዬ ፌዴሬሽኑ ያበረከተላቸው 10ሺ ብር ላይ 27ሺ ብር በመጨመር ለቡድኑ አባላት በሙሉ ለእያንዳንዳቸው የአንድ አንድ ሺ ብር የገንዘብ ስጦታ ማበርከታቸው ነበር። 

በሽልማት አሰጣጡ ስነስርአት ላይ የመግቢያ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚደንት አቶ ጁነዲን በሽአኽ በገባነው ቃል መሰረት የፌዴሬሽኑን አቅም ባገናዘበ ሁኔታ የዛሬውን ሽልማት አዘጋጅተናል። ሥራችንን በጋራ ጀምረናል በድል ለማጠናቀቅ ብዙ ረጅም ጉዞ ይጠብቀናል።  በሚዲያ በኩል መልካም እገዛና ለቡድኑ መጠናከር የሚረዱ አስተያየቶችን በመስጠት ከቡድኑ ጋር እንዲቆሙም ጠይቀዋል። 

ፈለቀ ደምሴ
ለኢትዮ ፉትቦል

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
Dear Readers: The views expressed on our comment pages under are the personal views of individual contributors and ethiofootball.com bears no responsibility for what readers post and is not liable for any form of impersonation. also note that while we value your feedback we may block inappropriate comment.
desalegn lamboro [906 days ago.]
 Wwwwwwww betam asdesach zena tabaraku betame dase belanale

zola [905 days ago.]
 bewtatu betam tedschalw bionm bektay meznagat endynor mezgajet yasfelgal bektayem le aferica wancha meders ygebanal walyawocun bertuln belelun10Q......

 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!