ገንዘብ በመስራት እንጂ በመቆጠብ ብቻ ውጤታማ አይኮንም
ሰኔ 17, 2007

ፈለቀ ደንሴ 

የአለም ህዝብ ከዳር እስከ ዳር የሚያገናኝ እና የሚያስተሳስር ትልቅ ሀይል የሆነው እግር ኳስ ዛሬ ዛሬ ትልቅ የሥራ እና የንግድ መስክ እየሆነ ለሀገሮች የኢኮኖሚ ጠቀሜታ ሀያል እየሆነ ነው፡፡ 

በሀገራችን ኢትዮጵያ ግን እለት ተእለት እያደገ የሚመጣው ህዝቡ ለእግር ኳስ ያለው ፍቅር ብቻ ነው፡፡ እግር ኳስን ወደ ንግድ በመለወጥ የሚሰሩ ክለቦችም ሆኑ ፌዴሬሽኖች መቶ በመቶ የሉም ማለት ይቻላል፡፡ 

ይህ ጉዳይ ብዙዎቹ ለአመታት ሀሳብ የሰጡበት ጉዳይ ቢሆንም አንድም አካል ይህን ለመለወጥ አንድ እርምጃ ወደፊት ሲሄድ አላስተዋልንም፡፡ ክለቦች በኪሳራ ፌዴሬሽኖች በኪሳራ በመንግስት እና በድርጅቶች እገዛ መጓዛቸውን አምነው ተቀብለው እየተጓዙ ነው፡፡ ይህ ሀሳብ በውስጤ ሲመላለስ የነበረ ቢሆንም የሌሴቶው እና የኬኒያው የባህር ዳር ጨዋታ ላይ ያስተዋልኩት ጉዳይ በጣም የሚያንገበግብ እና የሚስቆጭ ነበር፡፡ በእነዚህ ሁለት ጨዋታዎች በባህርዳር ከተማ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ገንዘቦችን አጥቷል ለማለት የሚያስደፍር ሁኔታ በሌሴቶው ጨዋታ በተሳሳተ ግምት 61ሺህ ትኬት ብቻ በማሳተሙ ወደ 45ሺህ ሰው በነፃ ስለገባ በግምት ከግማሽ ሚሊዮን ብር አጥቷል፡፡ በስቴዲየሙ ለታደመው 100ሺ ተመልካች እና  የከተማው ነዋሪ ጥቂት ነጋዴዎች ማሊያዎች እና ቁሳቁሶችን ከቻይና በማምጣት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ብሮችን አጋብሰዋል፡፡

 ከጨዋታው በኋላ በስቴዲየሙ ውስጥ በውጤቱ የተደሰቱ ነጋዴዎች ማሊያዎችን በነፃ ሲያድሉ አስተውለናል፡፡

Walya Jersey on Sale at the street of Bahirdar

Walya Jersey on Sale at the street of Bahirdar

Walya Jersey on Sale at the street of Bahirdar


  በርካታ የገቢ እድሎች ያባከነው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ግን በተከታታይ ሁለት ጊዜ በማሸነፍ ሚሊዮኖችን ያስፈነደቁ ተጨዋቾችን እና የቡድኑን አባላት ከሁለት ወር በላይ በልምምድ እና አስጨናቂ የሆነ የህዝብ ጫና ተሸክመው ውጤታማ ያደረጉትን ተጫዋቾች የሁለት ወር ደመወዛቸውን የማይሸፍን ገንዘብ ለመሸለም ተገዷል፡፡ እዚህ ላይ ሁሉም ተጫዋቾች ሀገራዊ ግዴታቸውን መወጣት ዝግጁ እና ፈቃደኛ ናቸው ቢሆንም ማበረታቻ ወሳኝ እና የውጤት ቁልፍ መሆኑን ማወቅ እና ጥንቃቄ ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡ ፌዴሬሽኑም በርካታ የሚታዩ እና የማይታዩ ወጪዎች እዳለበት ቢታወቅም በእግር ኳሱ ፌዴሬሽን ውስጥ ያሉ የሥራ አስፈፃሚ አባላት የተወሰኑት የተለያዩ እውቀት እና ልምድ ያላቸው ስለሆኑ ገንዘብ ቆጥበው ከመንቀሳቀስ የተሻለ ገንዘብ በማስገኘት ከባለሀብቶች ጋር በመነጋገር እና የተለያዩ ገቢዎችን በመፍጠር አቅማቸውን ማጠናከር ካልቻሉ የተጀመረውን ድል ማስቀጠል ይቻላል ማለት የዋህነት ነው፡፡ 

አንድ ሰው የዘጠኝ እና የአስር ሰው ሥራ ሸፍኖ እንዲሰራ ማድረግ አንድ አሰልጣኝ የሦስት እና የአራት ባለሙያዎችን ሥራ እየሰራ ከቀጠለ ከሰሜን እና ከምዕራብ አፍሪካ ሀገራት ጋር ለመፎካከር የማይቻል ነው፡፡ 

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በትናትናው እለት  በካፒታል ሆቴል በሰጠው ሽልማት ላይ ብዙዎች ሲያጉረመርሙ ተመልክተናል፡፡ ለምሳሌ በአንድ የሥራ መስክ የተቀጠረ ሰራተኛ ቀን ከሌሊት የተለያዩ ስራዎችን ደርቦ እየሰራ ፌዴሬሽን 2000 ብር መሸለም በጣም ይከብዳል፡፡ ሌሎች ከፍተኛ ግልጋሎት የሰጡ ባለድርሻ አካላትን ገንዘብ ባይሸለሙ እንኳን ሰርተፍኬት መስጠት እና ማመስገን ተገቢ ነበር፡፡ ለምሳሌ አንዲት እንስት ጋዜጠኛ ምንም እንኳን ሥራዋ ቢሆንም 1 ሳምንት ባህርዳር ከቡድኑ ጋር በመቆየት እያንዳንዱን የብሔራዊ ቡድኑን እንቅስቃሴ በመከታተል ለምትሰራበት ድርጅት እና ለሁሉም የሚዲያ አካላት ዜናዎችን ከማቀበል በተጨማሪ አመቱን በሙሉ የታዳጊ የሴቶች የብሔራዊ ሊግ ውጤቶችን ሳይቀር በሙሉ በተሟላ ሁኔታ በመከታተል በመስራት መወዳደስ ብርቅ በሆነበት የሚዲያ ባለሙያዎች ሳይቀር ከበሬታ ሲሰጣት አስተውለናል በተሰጣቸው 10 ሺህ ብር ላይ 27 ሺህ ብር በመጨመር ለተጫዋቾቹ የሰጡት የቡድኑ መሪ አቶ ዮሴፍ በግላቸው ባህር ዳር ላጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አድናቆጣቸውን ቸረዋታል ቢያንስ ባይሸልም እነኳን ፌዴሬሽኑ ከዚህ  የምስጋና ሰርተፍኬት ይሰጣል ብለን ገምተን ነበር አልሆነም፡፡ የፌዴሬሽኑ አመራሮች በትርፍ ጊዜያቸው ተደራራቢ ሥራ ላይ ሆነው ስለሆነ አገልግሎት የሚሰጡት ማርኬቲንግ ክፍሉን በማጠናከር ገንዘብ ላይ ጠንክረው መስራት አለባቸው እንጂ ገንዘብ በመቆጠብ አሸናፊ መሆን አይቻልም። ለዛሬ ይበቃል ወደፊት በሰፊው እመለስበታለሁ።  

ethiofootball.com
 
 
ዜናውን፣ ጽሑፉን ከወደዱት የፌስቡክ ገጾ ላይ ሼር ያድርጉት
 
 
Your Comment /አስተያየት *   Required
     
Name:
 
Email:
 
 
 
 
Comment:
* Amharic keyboard
   
 
     
     
 
Copyright© 2014 Ethiofootball.com All rights reserved!